ታሪክን ወደ ሁዋላና ወደፊት

ያልተበረዘውን የኢትዮጵያ ታሪክ የሚያነብ ሰው ፥ መጀመርያ የሚመጣለት ስሜት “ wtf ? ምን ጉድ ነው ?” የሚል ነው ፤ ለምሳሌ ነገስታት አንድ ልማድ ነበራቸው ፤ልክ ዙፋን ላይ ሲወጡ ልጆቻቸውን እና ወንድሞቻቸውን ሰብስበው ከመዲናቸው jራቅ ያለ ማጎርያ ቦታ ያስቀምጧቸዋል፤ የማጎርያው መልክአምድርማንበብ ይቀጥሉ…

ሕዝባዊ ሥነ-ቃሎቻችንን በጨረፍታ

የኛ ሕዝብ ሲከፋውም ሆነ ሲደሰት ሥነ-ቃሎችን ተጠቅሞ ብሶቱን፣ ችግሩንና ደስታውን ይገልፃል። ጉልበት ኖሮት በትር ባይወዘውዝም፣ ዘገር ባይነቀንቅምና ጠመንጃ ባይወድርም፣ ተንኳሹን፣ በዳዩን ወይም አጥቂውን ወገን በሥነ-ቃል ያለፍራቻ ያወግዛል። ይሄን ሲያደርግ እታሰራለሁ፣ እገረፋለሁ ወይም እሰቀላለሁ የሚል የፍራቻ ስሜት ልቡ ውስጥ ሽው የሚልበትምማንበብ ይቀጥሉ…

አንዳንዱ መፅሐፍ …

ልድገመውና …ከአንድ ክፍለዘመን በፊት በፈረንጆቹ 1936 አንዲት ማርጋሬት ሜሸል የተባለች አሜሪካዊት ጋዜጠኛ እግሯን ወለም ብሏት አልጋ ላይ ዋለች …ታዲያ ስብራቷን እያዳመጠች ከማለቃቀስ ይልቅ በደጉ ጊዜ አእምሮዋ ውስጥ የተጠራቀመውን የአገሯን የእርስ በርስ ጦርነት ታሪክ መፃፍ ጀመረች … እንዲሁ በደረቁ ሳይሆን እንደኛውማንበብ ይቀጥሉ…

የሽግግር መንግሥቱ ትውስታ በጥቂቱ (1983-1987)

ትናንት በለጠፍኩት አንድ ጽሑፍ ግንቦት 19/1983 በለንደን ስለተከፈተው ኮንፈረንስ ተናግሬ ነበር። እስቲ አሁን ደግሞ የለንደን ኮንፈረንስ ቀጥተኛ ውጤት ስለነበረው የያኔው የኢትዮጵያ የሽግግር መንግሥት እናውጋ። ከግንቦት 19-20/1983 በተካሄደው የለንደን ኮንፈረንስ ላይ ዋነኛ ተሳታፊ የነበሩት አዲስ አበባን ጨምሮ አብዛኛውን የሀገሪቱን ክፍል የተቆጣጠረውማንበብ ይቀጥሉ…

EPDA – በመጨረሻው ሰዓት የተገኘ አደገኛ ድርጅት

የደርግ መንግሥትን ለመደምሰስ ሲታገሉ የነበሩ ከደርዘን በላይ የሚሆኑ ድርጅቶች ነበሩ። ኢህአዴግ፣ ኦነግ እና ኢህአፓን የመሳሰሉት የታጠቀ ሰራዊት አስከትተው ሲዋጉ ነበር። አንዳንዶቹ ግን ሰራዊት ሳይኖራቸው በደርግ መንግሥት ላይ አደገኛ ፕሮፓጋንዳዎችንና ስውር የውስጥ ጥቃቶችን ሲያካሂዱ ነበር። ከነዚህም ውስጥ በብዙዎች ዘንድ ልዩ ትዝታንማንበብ ይቀጥሉ…

ከአበታር ወደ አባተ

አንዳንዴ የአማርኛ ዘፈን ቪዲዮ ሳይ ብዙ ነገር ይገርመኛል፤ የአማርኛ ሙዚቃ ቪድዮ ከማየትሽ በፊት ጃንጥላ መያዝ ይኖርብሻል ፥ ዝናብ የሌለው የፍቅረኞች ትእይንት ጥቂት ነው፤ በገሀዱ አለም ያገራችን ሰማይ ያሻሮ ብረት ምጣድ ማለት ነው፤ የብብታችን ላብ ካዲሳባ ሰማይ የተሻለ ያካፋል፤ ታድያ ዳይሬክተሮችማንበብ ይቀጥሉ…

የሰንበት ትዝታዎች

ለመጀመርያ ጊዜ ሲኒማ የገባሁት አስራንደኛ ክፍል ሳለሁ ይመስለኛል፤ እሁድ ቀን ደብረማርቆስ ውስጥ ነው፤ ብቸኛው ሲኒማ ቤት ተከፍቶ ካስራምስት የማንበልጥ ሰዎች ታድመናል፤ ፊልሙን በቴክኒክ የሚቆጣጠረው ሰውየ የጤና እህል ማለቴ እክል ገጥሞት አልመጣም፤ ስለዚህ፥ የሲኒማ ቤቱ ዘበኛ ጋሽ ይትባረክ ሰውየውን ተክተው ለመስራትማንበብ ይቀጥሉ…

እንዳይደም፤ እንዳይራዘም!

በሁለተኛው ያለም ጦርነት ጀርመን ኔዘርላንድን ወረረች። ወራሪም ተወራሪም ነጭ ናቸው። የሁለቱም አገሮች ካንድ ኩሬ የተቀዱ ቋንቋዎች ይናገራሉ። ሂትለር ግድ አለው? ኔዘርላንድ በሰማይ በምድር አጣድፎ ጨመደዳት። ለአራት አመታት ገደማ በቆየ የናዚ ጀርመን ጥጋብ የወለደው አገዛዝ ብዙ ሰዎች በጥይትና በረሀብ አለቁ። ከሰማንያማንበብ ይቀጥሉ…

“ኢትዮጵያ ደግሞ… አጉል ትመፃደቃለች!”

ይሄ ለስራ የመጣሁበት አፍሪካዊ ሃገር የእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ነበር። መቼ እለት ነው… የዚህ አገር ዜጋ ከሆኑ የስራ ባልደረቦቼ ጋር ሻይ-ቡና ስንል የ‹‹በቃ›› ወይም ” #No More›› ንቅናቄ በወሬ ወሬ ተነሳና ብዙ ነገር ሲያስመዝዘን አመሸ። በዚያ ሰሞን የበቃ ንቅናቄ ጀማሪዎቹ ኢትዮጵያዊያንማንበብ ይቀጥሉ…

ድል ምርኮና ምህረት

በአጼ ዮሀንስ አራተኛ ዘመነ መንግስት የጎጃሙ ንጉስ ተክለሀይማኖት እና የሸዋው ንጉስ ምኒልክ በመሬትና በንብረት ተጣልተው ሰራዊት አስከትተው እምባቦ በሚባለው ስፍራ ተገናኝተው ተሸካሸኩ፤ በጦርነቱ ምኒልክ እና አጋሮቻቸው በለስ ቀናቸው፤ ንጉስ ተክለሃይማኖት ብዙ ቦታ ቆስለው ተማረኩ፤ ምኒልክ በጦርነቱ ማግስት የግል ሀኪማቸውን በማዘዝማንበብ ይቀጥሉ…

ከሚካኤል ስሁል እስከ ደብረጺዮን

ዘመን የማይቀይረው የትግሬ ልሒቃን ደመኛነት… የትግሬ ልሒቃን ጭካኔ ውርሳቸው ነው። ኢ-ሰብአዊነት ውርሳቸው ነው። ዝርፊያ ውርሳቸው ነው። ፀረ ኢትዮጵያዊነትና ባንዳነት ውርሳቸው ነው። ክህደት ውርሳቸው ነው። እነዚህና ሌሎች የክፋትና የጥፋት የውርስ ታሪካቸውን አሁንም ለማስቀጠል እየተንደፋደፉ ነው። “ታሪክ ራሱን ይደግማል!” ይባል የለ? የትግሬማንበብ ይቀጥሉ…

“አይ ምፅዋ”

በዕለቱ (የካቲት 9/1982) የ6ኛው ነበልባል ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ የነበሩት ብ/ጀኔራል ተሾመ ተሰማ ከጠዋቱ 1፡30 ላይ በምፅዋ ከተማ ርዕሰ ምድርዕ በተባለ አካባቢ የተወሰኑ የጦር መኮንኖችንና ባለሌላ ማዕረግተኞችን ሰብስበው ንግግር አደረጉ። ንግግራቸውም … “እኔ የሚፈለግብኝን አደራ ተወጥቻለሁ። ከጥር 30 ቀን 1982ማንበብ ይቀጥሉ…

ትውስታ ስለ ጀግናው አበበ ቢቂላ

የታሪካዊዎቹ ጥቅምት 10 እና ጥቅምት 11 52ኛ ዓመት እና 56ኛ ዓመት ‹‹ማሞ›› ‹‹አቤት አበበ›› ‹‹እኔ ሩጫውን አልጨርሰም ላቋርጥ ነው›› ‹‹ምን! አዝናለሁ›› ‹‹ማሞ አደራህን እንድታሸንፍ፣ ከኛ ማለፍ የለበትም›› ‹‹እሺ አቤ›› ‹‹አደራ›› ዕለቱ እሑድ ጥቅምት 10 ቀን 1961 ዓ.ም. ከሃምሳ ሁለት ዓመትማንበብ ይቀጥሉ…

የባንዲራው ጦርነት!! (ዝክረ ኢታሎ ቫሳሎ)

…ድርጊቱ የተከሠተው በጋና አክራ በተዘጋጀው በአራተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ጫወታ ላይ ነው። 3ኛውን የአፍሪካ ዋንጫን ያሸነፈችው ኢትዮጵያ ከጋና ጋር እየተጫወተች ነበር። በወቅቱ የኢትዮጵያ ልኡካን ቡድን ወደ ጋና ከገቡበት ጊዜ ጀምሮ ብዙ በደሎች ሲደርስባቸው ስለነበር በመጥፎ ስሜት ነበር ወደ ሜዳ የገቡት። በጨዋታውማንበብ ይቀጥሉ…

እራሱን ያስተማረው ምሁር

ብዙዎቻችን አንድን ሰው የተማረ ነው የምንለው ወይም ደግሞ እውቀቱን የምንለካው በቆጠራቸው ክፍሎች አለያም በድግሪ፣በማስትሬት እና ዶክትሬት ደረጃው ነው።ነገር ግን እምብዛም በአለማዊ ትምህርት ሳይገፉ ጥበብን የታደሉ እንዲሁም እውቀትን በማንበብ ብዛት ያዳበሩ በየአገሩ ብዙ ሰዎች አሉ። ቢልጌትስ እና የፌስቡክ ባለቤት ማርክ የጀመሩትንማንበብ ይቀጥሉ…

ከነጋሪት ጉሰማ፤ወደ ጉማ

ኢትዮጵያ ዘመም ስትልና ስትቃና የኖረች አገር ናት፤ በነዋሪዎቿ መካከል ያለው አንድነት ባንዱ ዘመን ይታመማል፤ በሌላው ዘመን ይታከማል። ዛሬ ጋብ ባለ ጦርነት እና መልኩ ባልታወቀ መጭ ዘመን መሀል ቆመናል፤ ተደባበረናል፤ ተጠማምደናል ፤ “ እንገንጠል” “ ይገንጠሉ “ የሚሉ የቃላት ልውውጦች አየሩንማንበብ ይቀጥሉ…

ታሪክን የሁዋሊት

በአገሮች መካከል የሚፈጠረውን ግኑኝነት የሚወስኑት ሶሰት ነገሮች ናቸው፤ ያገሮች አቅም፥ ያጊዜው ሁኔታ ፥ እና የመሪዎች ችሎታ፤ ከአድዋ ድል በሁዋላ ኢትዮጵያ የረባ ንብረት ሳታፈራ፤ዳማ ፈረሷን በታንክ ሳትቀይር ተዘናግታ ቆየች ፤ ጣልያን በሞሶሎኒ መሪነት ሁለተኛውን ወረራ ፈጸመች ፤ ያገራችን እናትና አባት አርበኞችማንበብ ይቀጥሉ…

“What did i do to you?”(ምን አደረኳችሁ?)

“…..ወቅቱ እ.ኤ.አ 1986 ላይ ነው! የአሜሪካ ደህንነት ተቋም የሆነው “CIA” ከሰሜን አፍሪካዋ ሃገር ሊብያ ከሳተላይት እና ኤሌክትሮኒክ ሰርቪላንስ የሚሰበሰቡ የተለያዩ ሚስጥራዊ መልእክቶችን እየቃረመ ነው። ከነዚህ ሚስጥራዊ መልእክቶች ውስጥ ለአሜሪካ የደህንነት ስጋት የሚሆን ነገር ከተገኘ ይመረመራል። የዛን ቀን “CIA” 397 የተለያዩማንበብ ይቀጥሉ…

Finite and Infinite games

አንድ “James Carse” የሚባል ሼባ “Finite and Infinite games” በሚል ርዕስ የፃፈውን ፀዴ መፅሃፍ ሰሞኑን እያነበብኩ ነው። የሚያነሳቸው ሃሳቦች እና ዓለምን የሚያይበት መነፅር ደስ ይላል! ገና መፅህፉን ስትጀምረው ምን ይላል መሰለህ? እዚህች ዓለም ላይ ጦርነትም በለው፣ ስፖርትም በለው፣ ህይወትም በለው፣ማንበብ ይቀጥሉ…

የመጨረሻው እራት፣ ዳ ቬንቺ፣ ክርስቶስ እና ይሁዳ

ሊዮናርዶ ዳ ቬንቺ እንዲሁም ሥራ በማዘግየት የሚችለው የለም፤ በተለይ “የመጨረሻው እራት” የሥዕል ሥራውን አዘገየው አይገልፀውም – አደረበት እንጂ። ሥዕሉን ለመጨረስ ዓመታት ፈጅተውበታል። እርግጥ በዚህ ማንም ዳ ቬንቺን የሚወቅስ የለም። እንደእሱ መሳል ካልቻልክ አዘገየህ ብልህ ልትወቅሰው እንዴት ይቻልሃል ! በዳ ቬንቺማንበብ ይቀጥሉ…

The Last Supper (የመጨረሻው እራት)

የአንድ ወዳጄ የ”እንኳን ለፀሎተ ሃሙስ አደረሳችሁ” መልዕክት Leonardo Da Vinci የተባለው ስነ ጥበበኛ ‘The Last Supper’ ብሎ ለዓለም ባበረከተው ዝነኛ የጥበብ ስራው ዙሪያ ይችን አጭር መጣጥፍ እንድፅፍ ገፋፍቶኛል። ዳ ቬንቺ ይህንን ኢየሱስ እና ደቀ መዛሙርቱ በአንድነት ማዕድ ላይ የታዩባት የመጨረሻዋንማንበብ ይቀጥሉ…

ቅዱስ ቁርኣን በአማርኛ ሲተረጎም (1961)

ቅዱስ ቁርኣን በአማርኛ እንዲተረጎም ትዕዛዝ ያስተላለፉት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሤ ነበሩ። ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሤ ትእዛዙን ያስተላለፉት ሐምሌ 18/1958 በተጻፈ ደብዳቤ ነበር። የንጉሡን ደብዳቤ በመንተራሰስ ስራው እንዲጀመር ያደረጉት ደግሞ በወቅቱ የትምህርት ሚኒስትር የነበሩት ዶ/ር ምናሴ ሃይሌ ናቸው። ዶ/ር ምናሴ በተርጓሚነት የመረጡት ከአል-አዝሃርማንበብ ይቀጥሉ…

እምየ ካስትሮ (ካስትሮ ነጭ ሰው!)

ካስትሮ ተወልዶ ባይልክ ወታደር የአልሸባብ ነበሩ ድሬና ሃረር!! ‹‹ከሚኒሊክ ጥቁር ሰው›› እኩል የምትወደውና የምታከብረው ሰው ጥራ ብትሉኝ የኩባው ፊደል ካስትሮ ማለቴ አይቀርም! ‹‹ካስትሮ ነጭ ሰው›› እኔ ኢትዮጲያ ላይ ያንን የማድረግ ስልጣን ቢኖረኝ ኖሮ … እምየ ሚኒሊክ በፈረስ በክብር በቆሙበት አደባባይማንበብ ይቀጥሉ…

ታሪክን ወደ ፊት

ከምናምን አመታት በፊት በቀዳማዊ ሀይለሥላሴ እና በጎጃሙ ገዥ ራስ ሃይሉ መሀል ሃይለኛ የስልጣን ትግል ይካሄድ ነበር ፤ ራስ ሃይሉ ከብዝበዛና ከውርስ የተገኘ መአት ብር ነበረው ፤ ተፈሪ ከጎጄው ጋር ሲወዳደር እልም ያለ ችስታ ነበር ማለት ይቻላል ፤ በዚያ ላይ ተፌማንበብ ይቀጥሉ…

ታሪክን የሁዋሊት

በዘመነ የጁ በ1837 ዓም ግብፆች በገዳሪፍ በኩል ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ዘልቀው ገብተው ነበር፤ በጊዜው የደምቢያ ገዥ በነበሩት ደጃዝማች ክንፉ የተመራ የኢትዮጵያ ጦር ወራሪዎችን በመደምሰስ ድል ተቀዳጅቱዋል ፤ እንጦኒዮስ ደአባዲ የተባለ መንገደኛ መዝግቦ ያስቀመጠው የጥንት ግጥም ስለጦርነቱ የሚከተለውን ይተርካል፤ ‘የረጀባ ተዝካርማንበብ ይቀጥሉ…

ታሪክን የሁዋሊት 2

ዘመነ መሳፍንት በሚባለው የየጁዎች መንግስት ወቅት እንዲህ ሆነ፤ ራስ አሊ የተባለ ጎፈሬ መስፍን አገሪቱን ይመራ ነበር፤ ከእሱ በታች፤ ደጃች ውቤ የተባለ ባለሹርባ መስፍን፤ ከስሜን እስከ ምፅዋ ያለውን ግዛት ያስገብራል። የሆነ ጊዜ ላይ ውቤ ደጃዝማችነቱ አላረካው አለ፤ ደጁን ብቻ ሳይሆን ሙሉውንማንበብ ይቀጥሉ…

ትዝታየ በፎቶ ዙርያ

በልጅነቴ ትዝ ከሚሉኝ መፈክሮች አንዱ “ያልሰራ አይብላ” የሚል ነው። ስራ ብሄራዊ ሀይማኖት ሆኖ ነበር። ይሄ ደግሞ በጊዜው ፎቶ አነሳስ ላይ ሳይቀር ይንፀባረቃል ፤ አንድ ሰው ፎቶ ሲነሳ የሆነ ሰርቶ ማሳያ ነገር ፎቶው ውስጥ ማካተት ነበረበት፤ የቤት እመቤት ከሆነች ጥጥ እየፈተለችማንበብ ይቀጥሉ…

ስለ ፎቶ (ክፍል አንድ)

ልጅ እያለሁ ፎቶ ብርቅ ነበር ፤ ከእናቴ ጋራ የሆነ ግብዣ እሄዳለሁ፤ የቤት እመቤቲቱ ቡናው እስኪፈላ ከግድግዳው ላይ መስኮት የሚያህል ባለፍሬም ፎቶ መስቀያ አውርዳ በዳንቴል ወልወል አድርጋ ትጋብዘናለች። በፎቶው ውስጥ ሚስት ጥበብ ቀሚስ ለብሳ ፤ገብረክርስቶስ ጫማ አድርጋ ቁጢጥ ብላ ትታያለች ፤ማንበብ ይቀጥሉ…

የግል ስሜትና ብሄራዊ ምልክት

ባገራችን ህዝብ ከገዥ ጋር ተማክሮ የመረጠው ብሄራዊ ምልክት ኖሮ አያውቅም ፤ ያገር ገዥዎች የሆነ የስልጣን ምልክት ይመርጣሉ፤ ያ ምልክት በውድም ሆነ በግድ ብሄራዊ ምልክት ሆኖ ይቀራል ፤ገዥው አምራቹን ህዝብ( ገበሬውን፤አንጣሪውንና ነጋዴውን) አማክሮ የመረጠው ምልክት መኖሩን የሚያስረዳ ታሪክ ካለ አቅርብልኝ! የእድሜማንበብ ይቀጥሉ…

መንዲስ

ፈረንጆች አለመጠን ረጅምና ግዙፍ የሆነን ሰው Giant ብለው ይጠሩታል ። “ጋይንት” ብሎ እሚያነበው ስለማይጠፋ “ጃየንት” – /jai·uhnt መሆኑን አስታውሼ ልለፍ። በአማርኛ መንዲስ የሚል አቻ አለው። በታሪካንችን ዝነኛው መንዲስ ከታች ፎቶው ላይ ያለው ይመስለኛል። ይህ ሰማይ- ጠቀስ ሰውየ፤ መጀመርያ የቤኒሻንጉሉ ጌታማንበብ ይቀጥሉ…

የዛኔውና የዛሬው ጷግሜ 5 አንድ ናቸዉን?

ጷግሜ 5 በኢትዬጽያ ታሪክ ዉስጥ የራስዋ ድርሻ ኢንዲኖራት ካደረጉ ክስተቶች መሃል የ1966ቱ የኢትዮጵያ አብዮት አንዱ ነበር። ምንም እንኳን ንጉሱም የካቲት 19/1966 ለተነሳባቸው ህዝባዊ አመፅ መፍትሄ ይሆናል በሚል ስልት የጠቅላይ ሚንስትር አክሊሉ ሀብተወልድን ካብኔ አፍርሰው በእንዳልካቸው መኮንን የሚመራ አዲስ ካቢኔ በተማሪዎችናማንበብ ይቀጥሉ…

ሃሳብ አትሞትም(ሶስት ታሪኮች)

በመካከለኛው ዘመን በመላው አውሮፓ መንግስት የነበረችው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ናት። ቤተክርስቲያን አምባገነን ነበረች። በሃይማኖት ስም ታስራለች ፣ ታሰቃያለች ፣ ትገድላለች። ሳይንስ ተቀባይነት ያለው ከሃይማኖቱ አስተምህሮ ጋር ስሙም ሲሆን ብቻ ነው። ከዚያ በተረፈ አዳዲስ ሃሳቦች ብቅ ካሉ መልሳ ትቀብራቸዋለች። ሶስት ታሪኮችን እንይ፦ማንበብ ይቀጥሉ…

ድንቁርና ይጥፋ ዕውቀት ይስፋ

“~~~ድንቁርና ይጥፋ ዕውቀት ይስፋ ይህ ነው የኢትዮጲያ ተስፋ~~~~ “ ማንኛውም ሰው እናት ሀገሩ ባስገኘችለት ፣ ሊቃውንት አባቶች አዘጋጅተው ባቆዩለት ፊደል ተምሮ ማንበብና መፃፍ ተቀዳሚ ተግባሩ ይሆናል። መምህራንም የፊደላትን ሥነ ባህርይ ማስረዳት ይጠበቅባቸዋል። ይህም በየጊዜው ለሚነሳው ብሔራዊ ትውልድ እራሱን ክዶ ሌላውንማንበብ ይቀጥሉ…

ሙገሳ ለሞጋሳ

በ1571 ገደማ በልዑል ፋሲለደስ እና በቦረን ኦሮሞ የገዳ ሰራዊት መካከል ጎጃም ውስጥ ጦርነት ተደረገ፤ ቦረኖች አሸንፈው ልዑል ፋሲል በጦር ሜዳ ላይ ወደቀ፤አሸናፊው የኦሮሞ አባዱላ ፤ ሱስንዮስ የተባለውን የልዑሉን ልጅ አገኘው። በጥንታዊት ኢትዮጵያ በጦርሜዳ የተሸነፈን ምርኮኛ ትንሽ ትልቅ ሳይሉ መረሸን ብርቅማንበብ ይቀጥሉ…

ማፍረስ እንደ ባህል

(የመትከል ባህል የሌለው ሕዝብ እንትከል ስትለው አወዳደቁን እየተለመ ይስቃል) — ስሜነህ አያለሁ እና ቢኒያም ሲሳይ የፃፉት፣ «what is in a term? A historical and linguistic examination of the revolutionary terminology:yiwdem, “let it be demolished, down with,” 1974-1977» የሚል ወረቀት አለ።ማንበብ ይቀጥሉ…

“ግሪን ካርድ” 

ከማይሰበረው እፍታ!… የአሜሪካ ኑሮዬን ትቼ ወደ ኢትዮጵያ ከተመለስኩና ኢንቨስትመንት ከጀመርኩ በኋላ፣ ለስራ ጉዳይም ሆነ ቤተሰብ ለመጠየቅ በተደጋጋሚ ወደ አሜሪካ እመላለስ ነበር። ሁሌም አሜሪካ ደርሼ ከአውሮፕላን እንደወረድኩ በኢሚግሬሽን ሰራተኞችና በጸጥታ ሃይሎች የሚደረግልኝ አቀባበል በጥርጣሬ የተሞላ ነበር። ከአሜሪካ የወጣሁበትን ጊዜ ከፓስፖርቴ ላይማንበብ ይቀጥሉ…

የባህርዳሩ ክስተት – “የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ” ወይስ ሌላ?

መንደርደሪያ ሰኔ 15 በባህርዳር የተከሰተውን ሁኔታ ተከትሎ እያነጋግሩ ካሉ ጉዳዮች መካከል አንዱ ክስተቱ ምን ተብሎ መጠራት አለበት የሚለው ነው። ሁኔታውን ‹‹መፈንቅለ-መንግሥት›› ብለው የጠሩትና ቃሉን ለመጀመሪያ ጊዜ በደምበኛ(ሜይንስተሪም) ሚዲያ የተጠቀሙት በመንግሥት ሚዲያ የመጀመሪውን መግለጫ የሰጡት የጠቅላይ ሚኒስትሩ አፈቀላጤ ንጉሡ ጥላሁን ናቸው።ማንበብ ይቀጥሉ…

ሕሩይ ሚናስ

በኢትዮጵያ ሥነ ጽሑፍ ውስጥ ታላቅ ቦታ ከያዙ ሰዎች አንዱ ነው። እስካሁን ካነበብኳቸው የአማርኛ መጽሐፍት በልዩ ኹኔታ ከማስታውሳቸው ጥቂት ሥራዎች አንዱ የሕሩይ ሚናስ “እብዱ” የሚለው ሥራ ነው። የራሱን devastating experience በመጽሐፍ መልክ በመሰነድ ለአጥኚ ባለሙያዎች ራሱ እጅግ እንቆቅልሽ የኾነውን የአእምሮ መታውክማንበብ ይቀጥሉ…

የጉራጌ ሕዝብ ከ158 ዓመታት በፊት

ሰማዩም ምድሩም የኛ ነው የሚሉን ኦነጋውያን የሚይዙት ቅጣምባሩ ጠፍቷቸዋል። ከሰሞኑ ደግሞ ባሰራጩት በምስል የታገዘ ዜና በጉራጌ ምድር ከ158 ዓመታት በፊት ተቋርጦ ነበር ያሉን የገዳ ስርዓት ማስጀመራቸውን ነግረውናል። እንዲህ አይነት ዜና ሲሰማ ዝም ማለት ተገቢ ባለመሆኑ ከ158 ዓመታት በፊት የጉራጌ ሕዝብማንበብ ይቀጥሉ…

ኢትዮጵያ የባሩድ በርሜል

ዳሠሣ መጻሕፍት ዘወርሃ ግንቦት ዛሬ የምነግራችሁ አማራን በመጥላትና ኢትዮጵያን ለማፍረስ ስለተጋውና ለዚህም ህልሙ መሳካት ጥለቻን በመጽሐፍ ከትቦ ለትውልድ ስላቆየው አውሮፓዊ ሮማን ፕሮቻዝካ እና ስለ መጽሐፉ ነው።”ኢትዮጵያ የባሩድ በርሜል” የመጽሐፉ ርዕስ ነው።በባሩድ በርሜል ፍንዳታ ትፈራርስ ዘንድ ስለተፈረደባት ሃገር ኢትዮጵያ በመርዝ ጭስማንበብ ይቀጥሉ…

በዘመን ሂደት ያልተፈታ ችግር

“በዘመን ሂደት ያልተፈታ ችግር፤ በዘመን ሂደት የችግር ካንሠር ይሆናል።” ለአንዲት ሐገር ዘመንን የሚዋጅ፣ ትውልድን አንደአዲስ የሚቀርፅ ጥበብ ያስፈልጋታል። ሐገርን ወደኋላ የሚጎትት የማይጠቅም አስተሳሰብ በአዲስና በተሻለ አስተሳሰብ መለወጥ ከዜጎች የሚጠበቅ ተግባር ነው። ያረጀውን ማደስ፣ የሌለውን ጥበብ መፍጠር፣ ያልነበረውን መልካም ተሞክሮ መቅሰምማንበብ ይቀጥሉ…

ጃጋማ ኬሎ

በ15 አመቱ ሀገሩን ከወራሪ ፋሽስት ኢጣልያ ጦር ነፃ ያወጣው ባለ አፍሮ ፀጉሩ ወጣት አርበኛ: ጃጋማ ኬሎ በሚልድሬድ ዩሮፓ ቴይለር ጃጋማ ኬሎ ሀገሩ ኢትዮጵያን ከ1928ቱ የኢጣሊያ ወረራ ለመከላከል ወደ ጫካ በመግባት መዋጋት ሲጀምር ዕድሜው ገና 15 ብቻ ነበር። በመስከረም 1928 ኢጣልያዊውማንበብ ይቀጥሉ…

መርፌ

አብዬ መንግስቱ ለማ እጅግ ሲበዛ አስተዋይ ነበሩ። አማሪካን ሀገር ሄደው ተምረው ሲመለሱ ከሀሳብ ሁሉ ገዝፎ ሀሳብ የሆነባቸው ከአንድ ኢትዮጵያዊ ገበሬ ጋር ድንገት ቢገናኙ ሊጠይቃቸው የሚችለው ጥያቄ ነበር። ውጪ ተምረው እንደመጡ ሲያወሩ ድንገት የሰማ ገበሬ ጠጋ ብሎ “መርፌ ትሠራለህ? ” ብሎማንበብ ይቀጥሉ…

Loading...