ጠላታችን ሥም ነው!

ሥም ከወላጅ የሚሰጠን ቅርስ ነው። በውስጡ ፍላጎት፣ እምነት፣ ፍቅር፣ ተስፋ…ያጨቁ እንድምታዎች ሊኖሩት ይችላሉ። በግብር የምንወርሳቸው ሥሞችም አሉ። የሆነ ተግባር ፈፅመን የምንደርባቸው አይነት። የሥም ዋና ጥቅሙ አንዱን ከአንዱን ለመለየት ይመስለኛል። ይህ ሆኖ ሳለ ግን ሥምን እንደ ማነፃፀሪያ መቁጠሩ እየተለመደ መጥቷል። የምናከብረው፣ማንበብ ይቀጥሉ…

Déjà Vu / ዲጃቩ !

ከቀናት በፊት አዋሬ አካባቢ … ልክ ከታክሲ እንደወረድኩ ዝናብ ይዘንብ ስለነበር ተራሩጬ እግሬ እንዳመራኝ ተደርድረው ከተሰሩት ሱቆች ወደ አንዱ በረንዳ አመራሁ። የኮስሞቲክስ መሸጫ ሱቅ ነበር የተጠለልኩበት በረንዳ። ወደ ካሳንቺስ አዘውትሬ ብመላለስም አዋሬ ሚባለውን ሰፈር ግን አላውቀውም ነበር። መንገዱ ላይ ህዝቤማንበብ ይቀጥሉ…

ማሸነፍ ፤ መሸነፍ እና መበሻሸቅ

ከልጅነታችን ባንዱ ቀን፤ እኔ ከማ አቡኔ ቤት ጠላ ገዝቼ ወደ ቤቴ ስመጣ ፤ ሌላው እኩያየ ደሞ ላምባ ገዝቶ ወደ ቤቱ ሲሄድ መስቀልኛ መንገድ ላይ እንገናኛለን ፤ ከዩንበርሱ በጥቂት አመት የሚበልጥ ጥንታዊ ድንጋይ ላይ የተቀመጠ ቦዘኔ ጎረምሳ ይጠራንና “ ትቸለዋለህ?” ይለናል፤ማንበብ ይቀጥሉ…

ቀጮ! (ክፍል ሁለት)

 ምስጢሯን ለማወቅ የነበረኝ ጉጉትን ክብደትና ጥልቀት የተረዳችው ቅድስት አንድ ሰአት በማይሞላ ጊዜ ውስጥ ሁሉን ነገር ዘርዝራ ነገረችኝ። ግን ወሬውን የጀመረችው በአንድ ጥያቄ ነበር። ‹‹ለምንድነው ክብደት መቀነስ የምትፈልጊው?›› ሁሌም የማስበው ነገር ስለሆነ በቅደም ተከተል ነገርኳት። ‹‹በፊት በፊት የሚያምረኝን ልብስ ለመልበስ…ፋሽን ለመከተል…ቅልልማንበብ ይቀጥሉ…

‹‹ቀጮ!››

(ማሳሰቢያ፤ የዚህ ፅሁፍ አቅራቢ የህክምናም ሆነ የስነ ምግብ ባለሙያ አይደለችም፡፡ በዚህ ፅሁፍ ላይ የተካተተው መረጃ በግል ልምድ ላይ የተመሰረተ እና ለሌሎች ይጠቅም ይሆናል ከሚል ቀና አስተሳሰብ የመነጨ ምክር እንጂ በጥልቅ መረጃና ሳይንሳዊ መሰረት ላይ የቆመ ነው ለማለት አይቻልም) ከተወለድኩ አንስቶማንበብ ይቀጥሉ…

የሚጠይቁና ለጥያቄያቸው መልስ የሚሹ ሰዎች በደንብ የሚያስቡ ናቸው!

አባቶቻችን የመጠየቅን አስፈላጊነት ሲያሰምሩበት ‹‹ካለመጠየቅ ደጅ አዝማችነት ይቀራል›› ይሉናል። ፈረንጆቹም ‹‹ካልጠየቅክ አታገኝም! (If you do not ask, you will never get)›› ይላሉ። ሊቃውንቱም ‹‹መጠየቅ ያደርጋል ሊቅ›› በማለት መጠየቅ የሕይወት በርን፣ የአዕምሮ ደጃፍን፣ የልቦና መስኮትን ወለል አድርጎ ከፍቶ ከጥበብ ማማ ላይማንበብ ይቀጥሉ…

ለሌሎች መጮህ ለራስም መጮህ ነው!

ዝምታ ጥሩ የሚሆንበት ጊዜ አለ፤ ክፉም የሚሆንበት ጊዜ አለ። ዝምታን እንደየሁኔታው ማከናወን ከብልህ ሰው ይጠበቃል። ዝምታህ ለከት ይኖረው ዘንድ ማስተዋል ይፈልጋል። በሆነ ባልሆነው ከመዘባረቅ፣ በማይመለከትህ በሌሎች ሰዎች ግላዊ ጉዳይ ከመቀባጠር ዝም ማለት የተሻለ ነው። ዝምታን ወርቅ ማድረግ የሚችሉት የዝምታ ቅኔነትንማንበብ ይቀጥሉ…

የተሻለ ሃሳብም ጀግና አሳቢም አጣን!

ማሰብ መቻል ልዩ ፀጋ ነው። ሃሳብን መርጦ መተግበር ደግሞ ሰው በራሱ ላይ የሚያመጣው በረከት ነው። ማንም ለሆዱ የሚስማማውን ምግብ እንደሚመርጠው ሁሉ ለአዕምሮውም የሚመጥን ሃሳብን መመገብ ራስን መጥቀም ነው። ንፁህ ምግብ ሰውን ከበሽታ እንደሚከላከለው ሁሉ ንጹህና መልካም ሃሳብም ሰውን አፍራሽ ተልዕኮማንበብ ይቀጥሉ…

‹‹ግን…. ባይሆንስ?››

  ቴድ ቶክ ማየት በጣም ደስ ይለኝ የለ? ከምሳ ሰአቴ ቀንሼ ነው የማየው…አፌን በምግብ፣ አእምሮዬን ደግሞ በጥሩ የቴድ ቶክ ተናጋሪዎች ታሪክ ስሞላ ፍስሃ ይሰመኛል። በሁለት በኩል መመገብ ነዋ! ዛሬ ያየሁት የዳያንን ነው። ዳያን ቮን ፈርነስተንበርግ (ስሟ መርዘሙ፣ ደግሞ ማስቸገሩ).. ዳያንማንበብ ይቀጥሉ…

ጥሪት – ጥረት – ጥምረት

ቤተሰብ ውስጥ ምስቅልቅል የሚፈጠረው ወላጆች በተፈጥሮ ሞት ኑረትን ሲሰናበቱ ነው። ምክንያቱ ደግሞ ልጆች በእናት አባት ሕላዌ ወቅት ያልታያቸው የሃብት ክፍፍል ትዝ የሚላቸው ያን ጊዜ በመሆኑ ነው። ብዙ ጊዜ የሃብት ቅርምት ቤተሰብን ባላንጣ ያደርጋል። ከአንድ አብራክ ተከፍለው ከአንድ ማሕጸን በቅለው ክፉማንበብ ይቀጥሉ…

በኅዳር ውስጥ እኔን

(የነፍሴ ክስ) ተወው! ቆሻሻህን ተወው  ከሳቱ ዳር እራቅ ጭለማን ልበሰው ጥቁር ካባ ደርብ ዓይንህ ይጨልመው። … ግዴለህም ተወው እቤትህ ግባና ዓይንህን ጨፍነህ ስላሳመምካቸው ስላቆሰልካቸው ነፍሳት አስብና ራስህን ክሰስ ራስህን ውቀስ ራስህን አጥን ተረማመድበት በንፁሀን ፋና። … የነፍስህን እድፍ የውስጥህን ጉድፍማንበብ ይቀጥሉ…

አንድ ላይ ብንሆንም ተለያይተናል…

ትላንት ከአንዷ ጓደኛዬ ጋር ምሳ ለመብላት አንዱ ምግብ ቤት ቁጭ ብለናል። ምግቡን እየጠበቅን የተገናኘንበትን ብርቱ ጉዳይ ስንወያይ፣ አራት አለባበሳቸውና ነገረ ስራቸው ሁሉ ሃያዎቹን ከጀመሩ እንዳልቆዩ የሚያሳብቅባቸው ወጣቶች መጡና አጠገባችን ያለውን ጠረጰዛ ከበው ተቀመጡ። በእነሱና በእኛ መሃከል ያለው ርቀት በጣም ቅርብማንበብ ይቀጥሉ…

ከእንቅልፍ መልስ…

[ዳንሱን ከዳንሰኛው መነጠል ይቻላልን?] ___ ስለ ማንነት ሲነሳ በመስታወት ውስጥ ‘ፊቱን’ እያየ የሚመሰጥ ሰው ነው በዓይነ ሕሊናዬ የሚታየኝ… የናርሲስ ቢጤ … ናርሲስ በግሪክ ሚቲዮሎጂ ገጾች በውሃ ውስጥ የሚያየውን ምስል ለማምለክ ጥቂት የቀረው ሰው ሆኖ ተስሏል… በማንነት ጉዳይ ሁላችንም ናርሲስት ነን…ማንበብ ይቀጥሉ…

Connecting the dots

ልጅ እያለሁ ነጥቦችን በማዋደድ ጨዋታ እዝናና ነበር… በአንዳንድ ጋዜጣና መጽሔቶች የጀርባ ገጽ ላይ በተንተን ያሉ ጥቂት ነጠብጣቦች ይቀመጡና አንባቢያን በነጠላ መስመር ሲያገናኟቸው አንዳች ትርጉም ያለው ቅርጽ እንዲሰጡ ሆነው ይታተማሉ… ነገሩ መዝናኛ ቢሆንም አስተውሎ ላየው አንዳች እውነት ሹክ ማለቱ አይቀርም… ትላልቅማንበብ ይቀጥሉ…

Butterfly Effect

ተተንባይ ኑረት የሌላቸውን ሁነቶች የሚተነትነው ሒሳባዊ ንድፈ-ሃሳብ Chaos Theory ይባላል… ትወራው በዚህ ስም ከመጠራቱ በፊት መገለጫ ባሕሪያቱን ለመተንተን የመጀመሪያ ነው የሚባልለት የሒሳብ ሊቅ Henri Poincaré ይባላል… ፈረንሳዊ ነው… “It may happen that small differences in the initial conditions produce veryማንበብ ይቀጥሉ…

ድልድዮቹን ተውልን

እመሃል ላይ ተገምሰው ማዶ ለማዶ የሚያተያዩን ሰባራ ድልድዮች እየበዙ ነው… አንዳንዶቹን ሆን ብለን ሰብረናቸዋል… አንዳንዶቹ በሌሎች ሰንኮፎቻችን ዳፋ ተሰብረዋል… ሌሎቹን ግን መሰበራቸውን እንኳ አልተረዳንም… ~ አንዳንዶች የሚሰብሩትን ድልድይ ፋይዳ በወቅት ስሜታቸው ትኩሳት ውስጥ ብቻ ስለሚመዝኑ የሰባሪነት ወኔ እንጂ የአስተዋይነት ስክነትማንበብ ይቀጥሉ…

Nothingness!!

መስመር መስራት ስትጀምር ወዲህና ወዲያን ትፈጥራለህ… አጥር መገንባት ስትጀምር ውስጥና ውጭ ትፈጥራለህ… ፍርድ መስጠት ስትጀምር ክፉና ደግ ትፈጥራለህ… በመስመር – አጥርና ፍርድህ ምክንያት የልዩነት ዜማ ሰርክ ይቀነቀናል… እንዲህ ‘የሆኑ’ እና እንዲያ ‘ያልሆኑ’ ክልል ይበጃል… ‘የኛ’ እና ‘የእነርሱ’ ምድብ ይሰራል። ሕይወትማንበብ ይቀጥሉ…

ማንንም ለመማረክ የማትፈልግበት ደረጃ ስትደርስ

“ዌን ዩ ካም ቱ ኤ ፖይንት ዌር ዩ ሃቭ ኖ ኒድ ቱ ኢምፕረስ ኤኒበዲ” ከወደ ውስጥህ ያለው ኣንዱ የነፍስያህ የነፃነት በር ሰዎችን ለመማረክ ጥረት ማድረግህን ባቆምክበት አፍታ ወለል ብሎ ይከፈታል…ጎበዝ ተማሪ…ጠንካራ ሰራተኛ…መልከ መልካም…ደግ አዛኝ ሩህሩህ….ከበርቴ ባለሃብት በመባል ከይሲ ፍላጎትህ ላይማንበብ ይቀጥሉ…

የሱፍ አበባ ነኝ

የብርሃን ጥገኛ ነኝ… እኔዬ ከብርሃን ውጭ ውበት የላትም… ብርሃን ሳጣ ይጨንቀኛል… ቅጠሎቼ ይጠነዝላሉ… ቅርንጫፎቼ ይኮሰምናሉ… የሱፍ አበባ ነኝ… በሕላዌ ገመድ ለተንጠለጠለችው ኑረት ጨለማና ብርሃን የማይዘለሉ ሃቆች ቢሆኑም እኔ ግን በብርሃን ፍቅር እንደተለከፍኩ አለሁ… ልክፍቱ “..መሸ ደግሞ አምባ ልውጣ ስላልኩ የሚለቅማንበብ ይቀጥሉ…

ቆሻሻ መጣል ክልክል ነው

የሰዎችን አስተሳሰብ ሊለውጡ የሚችሉ ንግግሮችን በማድረግ የሚታወቀው ዓምደኛው ዴቪድ ጄ. ፖላይ ‹የቆሻሻ መኪና ሕግ (The Law of the Garbage Truck) የተሰኘ ተወዳጅና ተደናቂ መጽሐፍ አለው። ይህንን መጽሐፉን ለመጻፍ መነሻ የሆነው ኒውዮርክ ውስጥ አንድ ቀን በታክሲ ሲጓዝ ያጋጠመው አደጋ ነበር። እርሱማንበብ ይቀጥሉ…

ሕይወት- ሌስተርና ቼልሲ

ይገርምሃል ወንድሜ በሕይወትህ ድል አድርገህ ዋንጫ ወሰድክ ማለት እዚያው የልዕልና ማማ ላይ እንደተሰቀልክ ትቀራለህ ማለት አይደለም። አታየውም ቸልሲን መከራውን ሲቀበል። አምና እርሱ ዋንጫ ሲበላ ያየ ሰው ዘንድሮ መከራውን ይበላል ብሎ ማን ገመተ? ብዙዎችኮ ሲወጡ መውረድን ይረሱታል። ለሚወጣ ሰው ግን መውረድማንበብ ይቀጥሉ…

አራቱ የጠባይ እርከኖች

የሰው ልጅ አራት የጠባይ እርከኖች አሉት ይላሉ ትውፊታውያን ሊቃውንት። በነባሩ የኢትዮጵያ ትምህርት መሠረት ጠባይና ባሕርይ ይለያያሉ። ‹ባሕርይ› ማንነት ነው። በፍጥረትህ ታገኘዋለህ። ይዘህው ትኖራለህ። አትለውጠውም፤ አታሻሽለውም። ለምሳሌ ሰውነት ባሕርይ ነው። ሰው መሆንን፣ እንስሳ ወይም ዛፍ ወይም ውኃ በመሆን አትለውጠውም። ‹ጠባይ› ደግሞማንበብ ይቀጥሉ…

ራእይ (ክፍል ሦስት)

አክራሞታችን ሸጋና ፍሬያማ እንደሆነ ተስፋ አለኝ። ራእይ-2ን ከጻፍኩ ሳይታወቅ አንዱ አልቆ ሁለተኛው ሳምንትም ተገባድዶ አረፈው። እኔ በእኔ ነገሮች ተወጥሬ ጊዜውም ሳያስበው በራሱ ፍጥነት ሄደ ማለት ነው። ከቀረ የዘገየ ይሽላል በማለት … የደመቀ የሞቀ ሳላምታዬን ለሀሳብ ቤተሰብ፣ ጎረቤት ወዳጆቼ በእጅ በእጃችሁማንበብ ይቀጥሉ…

ራእይ (ክፍል ሁለት)

ሰላምታ ለሀሳብ ወዳጆቼ፣ ቤተሰብና ጎረቤቶቼ … እንደገና በመጽሀፈ-ፊት (fb) ገጻችን ምስል ለምስል ለመተያየት ያበቃን አምላክ ምስጋና ይድረሰው። ትዝ ካላችሁ የትንሿ ልጅ አሳዛኝ ታሪክ በምናቧ የቀረጸውን ስንኩል ህልም አንስተን ነበር ባለፈው። የመንደርደሪያ ሀሳቦችን ወርወር አድርጌ ነበር … ነገሩ እንደ ተጀመረ በእን…ጥል…ጥልማንበብ ይቀጥሉ…

ራእይ

ከካፌ በረንዳ ለይ ተቀምጬ ያላፊ አግዳሚውን ፊት በማየት መደነቅ ማደነቅ እወዳለሁ። ፊት የውስጥ ስሜት መገለጫ ሰሌዳና የሰፊው ሕይወታችን መታያ ሜዳ ነው።ለእንቦቀቅላ ሕጻናትም የሰው ፊት ከሁሉ የሚያዝናናቸውና የሚያስደምማቸው አሻንጉሊት ነው ይባላል። ፊት ባለ ብዙ ቀለም (ነጭ፣ ቀይ፣ ቡኒ፣ ጥቁር …)፣ ተንቀሳቃሽማንበብ ይቀጥሉ…

Loading...