የተሰወረ ጥበብ ይፈለጋል

መምህር ሰሎሞንን ድሮ ነው የማውቃቸው ፤ በሙያቸው ሂሳብ መምህር መሰሉኝ ፤ ምን እንደደረሱ ባላውቅም አንድ ሁለቴ ደራሲያን ማህበር ስብሰባ ላይ አይቻቸዋለሁ፤ በስብሰባው ላይ እጃቸውን ያወጡና አስተያየት ለመስጠት ይጠይቃሉ፤ መድረክ ላይ የሚቀመጡት ጋባዦች ብዙ ጊዜ አይተው ቸል ይሉዋቸዋል፤” በህግ አምላክ እሱንማንበብ ይቀጥሉ…

ፎቶና ውዴታ

ፌስቡክ የተቀላቀልኩ ወደ 2012 አካባቢ ነው፤ እና ያኔ ከቤተሰቤ እና ከጎረቤት በቀር የሚያውቀኝ አልነበረም፤ የፌስቡክ አጠቃቀም ራሱ በቅጡ አልገባኝም ነበር፤ የሆነ ጊዜ ላይ ሁለት ሄክታር ቶክሲዶ ሱፌን ግጥም አድርጌ ለብሼ፤ ጆፌ አሞራ እሚያህል ክራቫት ጣል አድርጌበት፤ ፎቶ ተነሳሁና ፌስቡክ ላይማንበብ ይቀጥሉ…

ታሪክን የሁዋሊት 2

ዘመነ መሳፍንት በሚባለው የየጁዎች መንግስት ወቅት እንዲህ ሆነ፤ ራስ አሊ የተባለ ጎፈሬ መስፍን አገሪቱን ይመራ ነበር፤ ከእሱ በታች፤ ደጃች ውቤ የተባለ ባለሹርባ መስፍን፤ ከስሜን እስከ ምፅዋ ያለውን ግዛት ያስገብራል። የሆነ ጊዜ ላይ ውቤ ደጃዝማችነቱ አላረካው አለ፤ ደጁን ብቻ ሳይሆን ሙሉውንማንበብ ይቀጥሉ…

ግን አንድ ሰው አለ

እርጅና ሲጫንሽ እድሜ ተጠራቅሞ ፥እንዳስም ሲያፍንሽ ሽበት እንዳመዳይ በጭንቅላትሽ ላይ በድንገት ሲፈላ ያይንሽ ከረጢቱ ፥ በንቅልፍሽ ሲሞላ ምድጃ ዳር ሆነሽ መጣፍሽን ከፍተሽ ያለፈውን ዘመን ፥ ከፍተሽ ስታነቢ የኔን ቃል አስቢ፦ ስንቶች አፈቀሩት ፥ በሐቅ በይስሙላ የገፅሽን አቦል፥ የውበትሽን አፍላ ግንማንበብ ይቀጥሉ…

ሴት እና ትዳር- ‹‹እርቃን››- (ክፍል ሁለት)

ፀሃፊ፡ ቢኮዙሉ ‹‹The Emperor’s Naked” ትርጉም፡ ሕይወት እምሻው ትዳራችን ይነፍስበት የጀመረው እዚህ ግባ በማይባሉ ጥቃቅን ነገሮች መነሻነት ነበር። አለ አይደል…ጠዋት ከእንቅልፋችን ስንነቃ እንዴት አደርሽ ማለት ሲተው…(ባሎች፣ እባካችሁ..ሁሌም ሚስቶቻችሁን እንዴት አደርሽ ብላችሁ ጠይቁ….በክር ከተሰራች አሻንጉሊት ጋር አይደለም እኮ ተኝታችሁ ያደራችሁት! አንድማንበብ ይቀጥሉ…

ሴት እና ትዳር – ‹‹እርቃን›› (ክፍል 1)

ፀሃፊ፡ ቢኮዙሉ ‹‹The Emperor’s Naked” ትርጉም፡ ሕይወት እምሻው የሶስት ወንዶች እና ሁለት ሴት ልጆች እናት ነኝ። ይህ ማለት፣ ከእንቅልፌ ከምነሳባት ሰከንድ አንስቶ መሽቶ የቤታችን የመጨረሻዋ መብራት እስክትጠፋ ድረስ ቀኑን ሙሉ ስተራመስ ነው የምውለው። ሌሊቶቼ አጭርና ቶሎ የሚያልቁ ናቸው። ንጋት ጠላቴማንበብ ይቀጥሉ…

እየተደማመጥን፤ (በዳምጠው)

የሆነ ጊዜ ከሬድዮ ጣቢያዎቻችን እንዱን ሳዳምጥ ጋዜጠኛው፤ “አድማጮቻችን እንዴት ዋላችሁ ፤ ሰላማችሁ ብዝት ይበል ፤ በዛሬው እለት የምንወያየው ካንገብጋቢ የማህበራዊ ችግሮቻችን ባንዱ ዙርያ ነው ፤ አንድ እንግዳ ስቱድዮ ድረስ ጋብዣለሁ … እስቲ ስምዎትን ለአድማጮቻችን አስተዋውቁ” እንግዳው : “ የመቶ አለቃማንበብ ይቀጥሉ…

አንዳንዴ

ባልተገራ ፈረስ በፈጣን ድንጉላ ኑሮን ባቦ ሰጠኝ ህይወትን በመላ በዚህ በኩል ሲሉህ ንጎድ ወደ ሌላ፤ እስከመቼ ድረስ ዳር ዳሩን መራመድ ፤ በጭምት ሰው ስሌት በክብር ካልመጣ፤ ሞክረው በቅሌት ሰው ቅፅር አይደለም፤ በእሾህ የታጠረ እንድትጥሰው ነው፤ ህግ የተፈጠረ። አይሰለቺህም ወይ መኖርማንበብ ይቀጥሉ…

ምን አጠፋ? (ክፍል ሁለት)

‹‹ ቆመሽ ቀረሽ እኮ…ቁጭ በይ እንጂ!›› አለኝ ወደ ትልቁ የቆዳ ሶፋ እያመለከተኝ። ለወትሮው ሶስት ወፍራም ሰው አዝናንቶ እንደሚያስቀምጥ የማውቀውን ሶፋ በሰጉ አይኖቼ ስገመግመው የአራስ ልጅ አልጋ ሆኖ ታየኝ። መቀመጤን በመጠኑም ቢሆን ለማዘግየት ጮህ አልኩና፣ ‹‹ስልኬ…ስልኬን ዴስኬ ላይ ትቼ ነው የመጣሁት….ከቤትማንበብ ይቀጥሉ…

‹‹ምን አጠፋ?››

መነሻ ሀሳብ This is Harassment አጭር ፊልም (ዴቪድ ሽዊመር) ሃምሌ ላይ በማእረግ ተመርቄ እስከ ግንቦት ስራ ስፈልግ ነበር። ቀኑ በገፋ፣ ወሩ በተባዛ ቁጥር- ትላንት በድግስ ዲግሪ ጭኜ ዘጠኝ ወር ሙሉ- ዛሬ ልክ እንደተማሪነት ዘመኔ በየቀኑ ከአባቴ የትራንሰፖርት ተቀብዬ ስራ ፍለጋማንበብ ይቀጥሉ…

‹‹ሲያመኝ ነው የከረመው››

ከሁለት አመታት በፊት ኤርትራ ስሄድ ብዙዎች የለየለት አምባገነን የሚሉትን ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን በታማኝ የሚደግፉ ሰዎች በተደጋጋሚ የሚያነሱት የድጋፍ ምክንያት አንድ ነበር። ‹‹ዙሪያውን እና ከበታቹ ያሉት ናቸው እንጂ እሱ እኮ ጥሩ ሰው ነው…አይዘርፍም…አያጠፋም…ለኤርትራ ታማኝ ነው›› የሚል ነበር። እንደ ዘፈን አዝማች ይደጋግሙትማንበብ ይቀጥሉ…

it is my WiFi

ጎረቤቴ ቺስታ ግብፃዊ ነው፤ ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድቡን ከገነባች እንግዲህ ተስፋ የለንም ብሎ አሜሪካ ውስጥ ጥገኝነት ጠይቆ በመኖር ላይ ይገኛል ! እኔ ከወራት በፊት “ግድቡ ተሽጡዋል” እሚለውን ዜና አምኜ ጥገኝነት መጠየቄን የሰማ አይመስለኝም ! ኑሮየ ለክፉ እሚሰጥ አይደለም! ኡበር እነዳለሁ! ዩቲውብማንበብ ይቀጥሉ…

የድሮ ዘፈን ላይ የቀረበ አጭር ትንታኔ!

  የድሮ ዘፈን ነፍሴ ነው ! የድሮ ዘፈን የሆነ ቬጂተርያን ቃና ነበረው:: በጊዜው ያልተዘመረለት የዱር ፍሬ የለም! “ የሾላ ፍሬ ” “ እንኮይ እንኮይ” “ ብርቱካኔ” “ ሸንኮራ” “ ፓፓየ” ነሽ ! “ ተቀጠፈ ሎሚ ተበላ ትርንጎ/ ከሸጋ ልጅ መንደርማንበብ ይቀጥሉ…

በእንተ ዲያስፖራ

ዲያስፖራ አይደለሁም፤ተመላላሽ ነኝ፤ “ ሲራራ “ የሚለው መጠርያ ይገልፀኛል:: እኔ እንደታዘብኩት ፤ዲያስፖራ ሁሉ አንድ አይነት አይደለም፤ መአት አይነት ዲያስፖራ አለ! ለዛሬ ዋና ዋናዎቹን ላስታዋውቃችሁ ! የመጀመርያው ክፍል አድፋጭ ዲያስፖራ ነው፤ አሳምሮ የተማረ፤ ዘናጭ ስራ ያለው፤ ፖለቲካን የሚያውቅ ግን በፖለቲካ ውስጥማንበብ ይቀጥሉ…

የጣልኩብሽ ተስፋ

ከአምስት አመታት በፊት የሐረር ከተማን በጎበኘሁበት ወቅት ያደረብኝን ተስፋ እና ስጋት “ካሜን ባሻገር “ በተባለው መፅሀፌ ውስጥ በሚከተለው መንገድ አስፍሬው ነበር፤ “ ከጁገል በር ላይ ቆሜ ሳያት ፤ሀረር ተስፋና ስጋት አግዛ ታየችኝ፤ የምን ተስፋ ? የምን ስጋት? ባንድ ወቅት ስለማንበብ ይቀጥሉ…

‹‹እኔም የናፈቅኩት ጨዋታሽን ነበር››

እንደ ወትሮው የማያቋርጥ የቢሮ ስራ ሲያዝለኝ ነው የዋለው፡፡ ጨዋታ ናፈቀኝ፡፡ ሙዚቃ አማረኝ፡፡ መደነስ ውል አለኝ፡፡ እንደለመድኩት ልክ እንዲህ ስሆን ነዳጅ የሚሆኑኝ የድሮ ሙዚቃዎችን ፍለጋ በተቀመጥኩበት ኮምፒውተሬ ላይ ዩቱዮብን ማሰስ ላይ ነበርኩ፡፡ ያው በኮሮና ምክንያት እስካሁን ስራዬን ከቤት አይደል የምሰራው? ልክማንበብ ይቀጥሉ…

ስለ ያ ቡዳ

“እንጫወት እንጂ የምን ማፈር ማፈር ያ ቡዳ ሳይመጣ ሳይጫነን አፈር ‘ -(የማንኩሳ ዘፈን )- ስለሞት ሁለት አይነት አመለካከት አውቃለሁ ፤ የመጀመርያው ከሃይማኖታዊ መገለጥ የመነጨና ብዙ ህዝብ የሚያምንበት ነው፤ ሰው የእግዚያብሔር አምሳያ ፍጡር ነው፤ ሲሞት ነፍሱ ወደ ሰማይ ትሄዳለች፤ ምግባረ ሰናዮችማንበብ ይቀጥሉ…

የሆነ ምሽት

ይሄ ንፍጣም ቫይረስ ወደ አገራችን ከመግባቱ ሁለት ወር አስቀድሞ የነበረውን ጊዜ እንደ ጉድ ጨፈርኩበት! ዛሬ እንዲህ ተጨማድጄ ልቀመጥ ያኔ እየዞርኩ የክለብ ምንጣፍ በዳንስ ሳጨማድድ አመሽ ነበር! የዚያን ቀን ምሽት ከጊድዮን ጋር ነበርሁ፤ ባለትዳር ነው፤ የሚስቱና (ዛዮን) የሶስት ልጆቹ ፎቶ በስልኩማንበብ ይቀጥሉ…

ከታጋቹ ማስታወሻ የተቀነጨበ

ብዙ ያሜሪካ ላጤዎች ውሻ አላቸው። እኔ ውሻ የማሳድርበት አቅም የለኝም፤ ቢሆንም በቅርቡ ቤት ውስጥ ከሚርመሰመሱት ጉንዳኖች መካከል የሰልፍ መሪውን መርጨ አለመድኩት፤ ምሳ ስበላ አንድ ሩዝ ፍሬ ጣል አደርግለታለሁ፤ ወደ ዘመዶቹ ይዞ ሊሄድ ሲል አንገቱን ይዤ አስቀረዋለሁ፤ እኔ የስዊድን ቮድካየን ስቀመቅም፤ማንበብ ይቀጥሉ…

የታጋቹ ማስታወሻ

ይሄ ቀሳ ግን ስንቱን አሳበደ? ቲክቶክ ምስክሬ ነው፤ የድሮ እብድ ሙዚቃ ቤት በር ላይ ይደንስ ነበር ፤ የዘንድሮ ዲጅታል እብድ ደሞ ሞባይሉ ካሜራ ፊት ይደንሳል ፤ እኔ ራሴን እየታዘብኩት ነው፤ አሁን“ ዘፈን ሃጢአት ነው አይደለም?” በሚል ክርክር ላይ በስካይፒ መሳተፌማንበብ ይቀጥሉ…

አመፅ!!

በለው! በለው! ዛሬ ታሪክ ተሰራ! ከተማውን ባንድ እግሩ አቆምነው!! “ሽጉጥ መትረይሱን አንግቶታል ያ ጥቁር ግስላ ደም ሽቶታል” የሚለውን የአለማየሁ እሼቴን ዘፈን በአለማየሁ ፋንታ ድምፅ እያንጎራጎርሁ ከቤቴ ወጣሁ ፤ ፓርኩ ላይ ስደርስ አንዲት ደርባባ ኤሽያዊት ሰልፈኛ ተዋወቅሁ፤ ከኢትዮጵያ እንደሆንኩ ስነግራት አይኗማንበብ ይቀጥሉ…

ትዝታየ በፎቶ ዙርያ

በልጅነቴ ትዝ ከሚሉኝ መፈክሮች አንዱ “ያልሰራ አይብላ” የሚል ነው። ስራ ብሄራዊ ሀይማኖት ሆኖ ነበር። ይሄ ደግሞ በጊዜው ፎቶ አነሳስ ላይ ሳይቀር ይንፀባረቃል ፤ አንድ ሰው ፎቶ ሲነሳ የሆነ ሰርቶ ማሳያ ነገር ፎቶው ውስጥ ማካተት ነበረበት፤ የቤት እመቤት ከሆነች ጥጥ እየፈተለችማንበብ ይቀጥሉ…

ስለ ፎቶ (ክፍል አንድ)

ልጅ እያለሁ ፎቶ ብርቅ ነበር ፤ ከእናቴ ጋራ የሆነ ግብዣ እሄዳለሁ፤ የቤት እመቤቲቱ ቡናው እስኪፈላ ከግድግዳው ላይ መስኮት የሚያህል ባለፍሬም ፎቶ መስቀያ አውርዳ በዳንቴል ወልወል አድርጋ ትጋብዘናለች። በፎቶው ውስጥ ሚስት ጥበብ ቀሚስ ለብሳ ፤ገብረክርስቶስ ጫማ አድርጋ ቁጢጥ ብላ ትታያለች ፤ማንበብ ይቀጥሉ…

ከባልሽ ሐብታሙን ሽማግሌ ከመረጥሽ በኋላ (ክፍል ሶስት)

አጭር ገመድ ማነኝ ብለሽ ትሄጃለሽ? ስለዚህ የሚስቱን ለቅሶ አትሄጅም ። ቀብሯ ላይ አትገኚም። አቶ ይሄይስ የጠበቀው ቢሆንም ከባድ ሃዘን ላይ ስለሆነ ከሳምንት በላይ አይደውልልሽም። የገባልሽን ቃል ሳያጓድል – ግን ደግሞ ምንም ሳይጨምር መንፈቅ ያልፋል። የመንጃ ፈቃድ አውጥተሸ ኒሳን ጁክ መያዝማንበብ ይቀጥሉ…

ከባልሽ ሐብታሙን ሽማግሌ ከመረጥሽ በኋላ (ክፍል ሁለት)

ያለ ተጨማሪ ጥቅማጥቅም ለተከታታይ ቀናት በግብዣ ያጣድፍሻል። በስጦታ ያንበሸብሽሻል። ምንም ነገር ውድ ነው ከማይል ወንድ ጋር መሆን ምንኛ ያስደስታል? ያየሽውን ሁሉ በሁለትና በሶስት አባዝቶ፣ ያማረሽን ሁሉ በጅምላ ገዝቶ የሚሰጥ ወዳጅ እንዴት ያረካል? ብለሽ ታስቢያለሽ። የቁርስ-ብረንች-ምሳ- እራት ግብዣዎቹ ያልለመድሻቸው አይነት ናቸው።ማንበብ ይቀጥሉ…

የፖለቲካ ቋንቋችን

እጄን በሳሙና ከመታጠብ በተረፈኝ ጊዜ ለንጀራ የሚሆን ስራ እሰራለሁ፤ ማታ ማታ ደግሞ አፌ ላይ ነጭ ሽንኩርት፤ ትከሻየ ላይ ነጭ ጋቢ ጣል አድርጌ ዩቲውብ ላይ እጣዳለሁ፤ ከፊልሙም ከዘፈኑም ቀማምሼ ያገሬን ቃለመጠይቅ ወይም ውይይት መመልከት እጀምራለሁ:: አልናደድም፤ አላዝንም፤ እንቅልፍ ደርሶ ከነዚህ ስሜቶችማንበብ ይቀጥሉ…

ከባልሽ ሐብታሙን ሽማግሌ የመረጥሽ እለት

ከአስራ ሶስት እህት ድርጅቶቹ በአንዱ ውስጥ ጀማሪ የማርኬቲንግ ሰራተኛ ነሽ። ድካሙ ብዙ፣ ደሞዙ ትንሽ ነው። አግብተሻል። የሁለት አመታት ባልሽ ከአመት በፊት ከስራ ከተቀነሰ ወዲህ ስራ ለማግኘት ሳያሳልስ ደጅ ቢጠናም አልሆነለትም። ብዙ ነገር አይሆንለትም። ግንባር ብቻ ሳይሆን ራእይም የለውም። የሚሰራውን ሰርቶ፣ማንበብ ይቀጥሉ…

የታጋቹ ማስታወሻ

ከፀሀይ በታች አሮጌ ነገር የለም ፤ ፀሃይ ራሷ በየሰኮንዱ ትታደሳለች፤ ከእንቅልፌ ተነሳሁ፤ ተንጠራራሁና አይኔን ባይበሉባየ ጠራርጌ ከእምብርቴ በታች ያለውን ቃኘሁት፤ አጅሬ ከኔ በፊት ቀድሞኝ ተነስቱዋል ፤ የዛሬው ደግሞ የተለየ ነው፤ እስክንድር ነጋ ንግግር ባደረገ ቁጥር ባንዲራ ይዞ ከጀርባ እሚቆመውን ሰውየማንበብ ይቀጥሉ…

ዝክረ- ኳራንታይን (ክፍል ሁለት)

ውበት የውበት ሳሎኖች እንደ መድሃኒት መደብሮች፣ የምግብ መሸጫ ሱቆች እና የህክምና ጣቢያዎች ሁሉ ‹‹አንገብጋቢ አገልግሎት አቅራቢ›› ተብለው መመደብ እንደነበረባቸው ያየንበት ጊዜ ነው- ኳራንታይን። የሴቶች ትክክለኛ የጠጉር ቀለም (በአብዛኛው ሽበት) ፣ ትክክለኛው ኪንኪ ጠጉርን (ሂውማንሄር ለረጅም ጊዜ በካውያ ሳይሰራ ሲቀር ተሳስሮማንበብ ይቀጥሉ…

ዝክረ- ኳራንታይን

ከወረርሽኙ መባቻ አንስቶ፤ ‹‹ብትችሉ ከቤት ንቅንቅ አትበሉ›› ከተባለ ጀምሮ፣ መደበኛ የቢሮ ስራቸውን በቢጃማ፣ ቢያሻቸው ሶፋቸው፣ ቢላቸው አልጋቸው፣ ሲያምራቸው መሬት ተቀምጠው በርቀት እንዲሰሩ ከተፈቀደላቸው፣ እድል ከቀናቸው ጥቂት አዲስ አበባዊያን መሃል ነኝ። እግሮቼን ከሰፈር ሳልርቅ ለማፍታታት ወጣ ከማለት፣ ወጥ ወጥ፣ ቤት ቤትማንበብ ይቀጥሉ…

የትዳር አጋርዎን እንዴት ያገኛሉ?

በአሁኑ ሰአት የአኗኗር ዘይቤያችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተቀየረ የመጣበት ወቅት ላይ ነን። የዕለት ተለት ማህበራዊ ግንኙነታችን በእጅ ስልካችን ውስጥ የሚያልፍ ሆኗል። ብዙውን ሰአታችንንም በስልካችን ላይ እንደምናሳልፍ ይታወቀቃል። ስለሆነም ሰዎችን ለመተዋወቅና ግንኙነትን ለማዳበር ከተለመደው የተለየ መንገድ መከተል የግድ ይሆናል። በቅርቡ በተደረገማንበብ ይቀጥሉ…

እህ እንዴት ነው ገዳዎ!

በጥንታዊ የጋርዮሽ ስርአት የመጀመርያው የሰው ልጆች ስራ አደንና ፍራፍሬ መልቀም ነበር፤ አንድ ወንድ እና ሴት ተጣምረው ዱር ለዱር ይንከራተታሉ። እንጆሪ ለቅመው ወይም የዱር ፍየል አድነው በጋራ ይበላሉ፤ከእለታት አንድ ቀን ሴቲቱ ታረግዛለች፤ ሆዷ ገፍቶ እንደ ድሮው ዛፍ መውጣት ወይም መስክ በሩጫማንበብ ይቀጥሉ…

ድንጋይ ዳቦ ሆነ

አንዲት አረጋዊት ጥቁር ኢትዮጵያዊት ትመካበት የላት ባለፀጋ ዘመድ ፊቷ የለበሰ፤- ፅናት ላብና አመድ እሷ አለቃ ሆና፤ ክንዶቿን ቀጣሪ እሱዋ ድሃ ሆና ፤ የሀብታሞች ጧሪ:: እየተጋች አድራ እየለፋች ስትውል እድሜና ተስፋዋን፤ ያስተሳሰረው ውል ቢቀጥን ቢሳሳ ከሸረሪት ፈትል መሀረብ ዘርግታ ተዘከሩኝ ሳትልማንበብ ይቀጥሉ…

ታጋቹ ማስታወሻ

ቀሳ ከወጣሁ ጊዜ ጀምሮ ቤቴ ውስጥ ያገኘሁት ምግብ ሩዝ ብቻ ነው ፤ ሰኞ ሩዝ በቲማቲም- ማክሰኞ ሩዝ በጅንጅብል- ረቡእ ሩዝ እንደወረደ፤ ወዘተ…ባጭሩ በሩዝና በሪዝ ተከብቤ ሰነበትሁ ማለት ይቻላል፤ አንዳንዴ ምግብ የቀየርኩ እንዲመስለኝ የምበላበትን ቦታ እቀያይራለሁ፤ ሳሎን ውስጥ ሁለት ማንኪያ እጎርስናማንበብ ይቀጥሉ…

የግል ስሜትና ብሄራዊ ምልክት

ባገራችን ህዝብ ከገዥ ጋር ተማክሮ የመረጠው ብሄራዊ ምልክት ኖሮ አያውቅም ፤ ያገር ገዥዎች የሆነ የስልጣን ምልክት ይመርጣሉ፤ ያ ምልክት በውድም ሆነ በግድ ብሄራዊ ምልክት ሆኖ ይቀራል ፤ገዥው አምራቹን ህዝብ( ገበሬውን፤አንጣሪውንና ነጋዴውን) አማክሮ የመረጠው ምልክት መኖሩን የሚያስረዳ ታሪክ ካለ አቅርብልኝ! የእድሜማንበብ ይቀጥሉ…

‹‹እግዚአብሔር ለሚረሱት ሁልጊዜ ማስታወሻ ይልካል››

ብዙዎቻችን፣ ከልጅነታችን አንስቶ ‹‹ የጭንቅ ጊዜ ሳይመጣ በጉብዝናችሁ ወራት ፈጣሪያችሁን አስቡ›› ብንባልም አንደበታችን ለፀሎት፣ ጉልበታችን ለስግደት የሚዘጋጀው መከራ ከፊታችን ሲደቀን ብቻ ነው። አመዛኙ ፀሎታችን ‹‹ከዚህ ፈተና አውጣኝ››፣ አብዛኛው ልመናችን ‹‹ይሄን የመከራ ጊዜ በድል አሻግረኝ›› ነው። ሲጎድለን ‹‹ይሄን ጨምርልኝ›› ክፍተት ሲታየንማንበብ ይቀጥሉ…

አይ የሰው ኑሮ መለያየት!

ካናዳ የሚገኘው የመስሪያ ቤታችን ቅርንጫፍ ባልደረባ ለስራ ጉዳይ የኢሜል መልእክት ልካልኝ ምን ብላ ጀመረች? ‹‹እንዴት ይዞሻል? አዲስ አበባ ያላችሁ ሰራተኞች ከቻላቸሁ ከቤት እንድትሰሩ እንደተመከራችሁ ሰማሁ። እኛ ያው በግድ፣ በመንግስት ትእዛዝ ቤት ታሽገን ተቀምጠን ልናብድ ነው። ወላ ሬስቶራንት ሄዶ መብላት የለ፣ማንበብ ይቀጥሉ…

መፋቀር አጋባን፣ መፋቀር አኖረን

ሰሞኑን ‹‹ከእገሌ ዘር አትግቡ…የተጋባችሁም ተፋቱ›› መባሉን ስሰማ ይህችን ላካፍላችሁ መጣሁ። የእኔ እና የባለቤቴ ሰርግ ብዙዎቹን አግልሎ ያስቀየመ፣ በሃያ ሁለት ሰዎች እንግድነት (ሁለቱ በወሬ ወሬ ሰምተው ራሳቸውን ጋብዘው ነው) ብቻ የተፈፀመ ነበር። ደህና ቤት በደህና ዋጋ ለመከራየት ከሰፈር ሰፈር እየተንከራተትን መቶዎችንማንበብ ይቀጥሉ…

የዛሬ አክቲቪስት የማይነግርህ ዘጠኝ አንኳር ነገሮች

1. ‹‹ ክፋቱ አዶልፍ ሒትለርን የዋህ የሚያስብል ነው ፣ ጭካኔው እና ግፉ ከግራዚያኒ የበለጠ ነው፣ ተንኮሉ ከሳጥናኤል የረቀቀ ነው፣ ሴራው ከቀኝ ገዢ የተወሳሰበ ነው…ይሄ ዘር ታሪካዊ ጠላትህ ነው….ያኛው ዘር መቼም የማይተኛልህ ነው፣ ካላጠፋኸው ሊያጠፋህ ነው…ካልቀደምከው ሊቀድምህ ነው›› እያለ የሚነግርህ…እዚያ…ከጋራው ማዶ…ማንበብ ይቀጥሉ…

“ማሕሌት” አጭር ልብ ወለድ ላይ የተሰጡ ሃሳቦች

፩ “… ማሕሌት ሕይወትን ከልጅነቷ ጀምራ እንደ ፈቀደችው ያልኖረች፣ ዕጣ ፈንታዋ በጉልበተኛ ወንዶች ጫማ ሥር ያዋላት ልብ ሰባሪ ገፀ – ባሕሪ ናት። በልጅነቷ ተገዳ የተዳረች፣ ከገጠር ሸሽታ ወደ አዲስ አበባ ስትመጣ በአጎቷ ጓደኛ የምትደፈር፣ ይህን ለማምለጥ ሥራ ብትቀጠር እንደ ቀደሙትማንበብ ይቀጥሉ…

ትዳርን ከነ ብጉሩ

አንድ፡ ‹‹ወሲብ በአርባዎቹ›› ጥር የሰርግ ወር አይደለ? የትዳር መጀመሪያ…? ያንን ይዤ ትዳርን ሀ ብለው ለሚጀምሩም፣ ትንሽ ለዘለቅንበትም፣ ገና ዳር ዳር ለሚሉም ቁምነገር አይጠፋውም ብዬ ‹‹ትዳርን ከነብጉሩ›› የሚገልፁ እውነተኛ ታሪኮችን ፍለጋ ባለትዳሮችን ማነጋገር ጀምሬ ነበር። አሁንም ከዜሮ እስከ አርባ አመታት የትዳርማንበብ ይቀጥሉ…

‹‹ሻይ በምሬት››

ዛሬ በጠዋቱ አስቸኳይ ጉዳይ ገጠመኝና ስራ ከመሄዴ በፊት አንድ ወዳጄን ለማግኘት አስፋልት ዳር ካለ የሰፈር ካፊቴሪያ ተቀምጬ ቅመም ሻዬን በብርድ እጠጣለሁ። ወሬ አያለሁ። ነፋሱ ይጋረፋል። ብርዱ ያንዘረዝራል። በትንሽ ብርጭቆ የቀረበልኝ ሻይ ስላልጠቀመኝ ሁለተኛ አዘዝኩና ፕላስቲክ ወንበሬ ላይ እየተመቻቸሁ ወደ ጎንማንበብ ይቀጥሉ…

Loading...