የብሄር ፖለቲካ

አማራ የለም የሚለው ክርክር የሚያሳቅ ነገር አለው። ሌላውን ማንነት ተፈጥሯዊ የማድረግ የዋህ ተግባር ነው። የትኛውም ሕብረት ሰው ሰራሽ ነው። እንኳን አንድ ብሔር ሀገር እራሱ ከተለያዩ ምናልባቶች ውስጥ በአንዱ ምናልባት የተገነባ አንድ አጋጣሚያዊ ማንነት ነው። አዎ አማራ የሚባል ማንነት የለም። በዛውማንበብ ይቀጥሉ…

ትንሣኤ

አምላክ፦ የአዳም ዘር ይድን ዘንድ፣ ግድ ቢለው ፍቅሩ፤ ሰው ሆኖ ወረደ፣ ከሰማያት ክብሩ። -> አይሁድ፦ የእርሱ ፍቅር ሳይሆን፣ ክብራቸው ገዷቸው፤ እውነቱ… ተግሣጹ… ስላሳበዳቸው፤ ለክፉ ሥራቸው፣ ነፃነት ፈልገው፤ እጅና እግሮቹን፣ በችንካር ሰንገው፤ “በክፉ ዓለማቸው፣ ደጉን እንዳያዩት፤ ዝቅ ብሎ ቢመጣ፣ ከፍ አ’ርገውማንበብ ይቀጥሉ…

አያና ነጋ (የእስክንድር ነጋ ወንድም አይደለም ☺) 

ሰው ራሱን የተፈጥሮ ማእከል አድርጎ ይመለከታል፤ለተንኮል። ያልተመቸውን እየቀጠፈ፣ የተመቸውን እያገዘፈ ለመኖር። ለሰው ሲባል፣በሌሎች ፍጡራን የሚደረገው ብዙ ነው። ይሄን የመሰለው በዓል አንዱ መስኮት ነው። ዓመት በዓል ብዙ እንስሳት የሚገደሉበት ሰዋዊ ስነስርዓት ነው። ሰው ግን እንስሳትን ዝም ብሎ አይገልም። መጀመሪያ ህይወት እንጂማንበብ ይቀጥሉ…

የገደለ አባትሽ የሞተው ባልሽ (ክፍል ስድስት)

“በቃ ሂድና ትንሽ ጊዜ ስጭኝ ምናምን እስኪወጣልኝ አንጎዳጉጂኝ ምናምን በላታ?” ያለግጣል። አልሳቅኩለትም። ብቻውን ይገለፍጣል። ተነስቼ ወደቤቷ በሩጫ ረገጥኩ። 199″አንተ የምር አደረግከው እንዴ?” የአብርሽ ድምፅ ከጀርባዬ አጀበኝ። በሩን ከፍቼ ስገባ ደርቄ ቀረሁ።.. የሄድኩት ምን ልላት ነበር? ለምንድነው የምናቆመው ልላት? አይደለም። እኔማንበብ ይቀጥሉ…

የገደለ አባትሽ የሞተው ባልሽ (ክፍል አምስት)

በነገራችን ጎን እኔ ከነአካቴው ሲጋራ አጭሼ አላውቅም። አንድ አይናለም የምትባል የእማዬ ጓደኛ ናት ጭስና አክሱሜን አቋልፋው የሞተችው። ይኸው ከዚያ ወዲህ የምታጨስ ሴት፣ የሲጋራዋ ጭስ ሽታ፣ ጥቁር ዳንቴላም ስቶኪንግ፣ ወንድነት (ቀበቶ) ፣…….. ማላብ…… በነፍስም በስጋ ተዛምደውብኛል። ምድረ አዳም ያለጭስ አክሱሙ አይሰራምማንበብ ይቀጥሉ…

ማን ይቀስቅሰን?

“አጥር መስራት የውሻ ተግባር ነው” ~ የገዳ ስርዓት — እንደ ማሕበረሰብ አንቀላፍተናል… ጥልቅ እንቅልፍ ውስጥ ነን… ለሞት የቀረበ እንቅልፍ… ችግሩ ማንቀላፋታችንን አናውቅም… ማንቀላፋታችንን ስላላወቅን የተኛንበትንም አናውቅም… ማንቀላፋታችን ደግሞ በሌባ አስደፍሮናል… ችግሩ መሰረቃችንን አናውቅም… ወይም ግድ የለንም… የተዘረፍነው ግን አማናዊነት ነው…ማንበብ ይቀጥሉ…

የገደለ አባትሽ የሞተው ባልሽ (ክፍል አራት)

“ጎዳኧው? ጥርስ ነው ያወለቅከው?….. እንደው ምን ተሻለኝ ይሁን?” በሩን የከፈተችልኝ እማዬ ናት። “እማዬ ደግሞ ትንሽ ጫፍ ካገኘሽ መምዘዝ ነውኣ?…. እኔ ከማንም አልተጣላሁም።” “አዪዪ…. ተዋ! ከሰው ካልተጣላህ በቀር በምንም ምክንያት አሚ እንዲህ እሳት አትለብስም?” ወድያው ድምፅዋን ሾካካ አድርጋ “ምንድነው ነገሩ? ፍቅርማንበብ ይቀጥሉ…

የዘውግ ፖለቲካ እንደ ሀገር?

ወደ 25 ሀገሮች ፌደራሊዝምን ይከተላሉ ይላል አሰፋ ፍስሃ ስለ ፌደራሊዝም በፃፈው መፅሐፍ። ያዋጣቸውን አዋጥቷቸው ይሆናል። የኛ ግን የቆመበት መሰረት በራሱ «ፀብ ለሚሹ የሜዳ ጠረጋ» ስለሆነ አልተሳካም ብንል አያኳርፍም። የዘውግ ፖለቲካ አያዋጣም ሲባል እንዲሁ ሳስበው ደስ አይለኝም ከሚል የሚሻገር ሰበብ አለው።ማንበብ ይቀጥሉ…

የኩባያ ወተት ወይስ የኩባያ ውሃ?

ስመጥሩ የእስልምና ታሪክ ተመራማሪና ፀሃፊ አህመዲን ጀበል ለ‹‹ከመጋቢት እስከ መጋቢት›› በተቀረፁት አጭር ቪዲዮ ላይ የተጠቀሟት ታሪክ ደስ አለችኝና አመጣሁላችሁ። ታሪኳ እንዲህ ትላለች። አንድ መሪ ህዝቡ ምን ያህል እንደሚወደው ለማውቅ ፈለገና አደባባይ ላይ ትልቅ በርሜል አስቀምጦ ህዝቡን እንዲህ ብሎ አዘዘ። ‹‹የሚወደኝማንበብ ይቀጥሉ…

የገደለ አባትሽ የሞተው ባልሽ (ክፍል ሶስት)

አማላይ ከሬሳ ሳጥኑ አጠገብ አልነሳም ብላ ለያዥ ለገናዥ አስቸገረች… ጋሼ የልጄ ገዳይ እሷ ናት ካልገደልኳት ብሎ ሁከት አስነሳ። እማዬም ለዓይኔ አልያት አለች። እኔስ? … እኔ ዞረብኝ። «አስወጡልኝ ይህቺን ልጅ… ለልጄ በቅጡ ላልቅስለት አስወጡልኝ! » እማዬ እሪሪሪ አለች። «ይግደሉኝ!… ይግደሉኝ እንጂማንበብ ይቀጥሉ…

‹አንበሳው› ማን ነው፤ ‹አህያውስ› የምን ምሳሌ?

አንበሳን የማምለክ አባዜ በየጉዳዮቻችን ውስጥ ገንኖ ይታያል፤ የምንወዳቸውና የምንፈራቸው ነገሮች በ‹አንበሳ› ስም እንዲጠሩ እንፈልጋለን፤ የሚያገሱ በሚመስሉ የአንበሳ ሀውልቶች ታጥረን መኖር እንፈልጋለን! በተቃራኒው ደግሞ፤ አህያን እዩት፤ የውርደት ምልክት ነው፤ አንድም ቦታ ጠላቶቹን ድል ስለማድረጉ የሚተርክ ተረት አጋጥሞኝ አላነበብኩም ፤ በተረቱ ውስጥማንበብ ይቀጥሉ…

‹‹አብሮ አይሄድም››

  ለስብሰባ ከመጣች ኖርዌያዊት የስራ ባልደረባዬ ጋር የባጥ የቆጡን እየቀባጠርን ነበር። ኢትዮጵያንም አፍሪካንም ስታይ የመጀመሪያዋ ነው። ምሳ ደረሰና ቡፌው ጋር ስንሄድ፣ ገበታው የጸም እና የፍስክ በሚል መከፈሉን ስታይ ተከታታይ ጥያቄዎች አዘነበችብኝ። ‹‹ብዙ ሰው ይጾማል?›› ‹‹ምን ያህሉ ሰው ኦርቶዶክስ ነው?›› ‹‹ምንማንበብ ይቀጥሉ…

የገደለ አባትሽ… የሞተው ባልሽ (ክፍል፦ ሁለት)

አሚዬ ከእህቴም በላይ ናት።…… አባቷ ወንድሜን ከገደለው እለት ጀምሮ እሷ የኛ ቤተሰብ አካል ሆናለች… የወንድሜ ምትክ.…… የሚያውቀን ሁላ ለዓመታት ከእንጀራው ጋር አብሮ ስማችንን አላመጠው፣ ጎረቤት ከተጣጡት ቡናቸው ጋር ስማችንን አብረው አድቅቀው… አፍልተው ጠጡት… እንዴት ከገዳያቸው ጋር ይወዳጃሉ? ሰው ጠላቱን እንዴትማንበብ ይቀጥሉ…

Loading...