ወዲህ በዳዊት ወዲህ በጋሻ!!!

ትላንትና ከባልንጀራየ ምኡዝ ጋር ተገናኝተን ቢራ ወይንና የመሳሰሉትን አልኮሎች ስንጠጣ:-አገርን በፍቅር ስለማስተዳደር አሰፈላጊነት ” በሰፊው ሰበክሁለት። እሱ እያዛጋና እየተቅበጠበጠ ሲሰማኝ ቆይቶ ሳያስጨርሰኝ የሚከተለውን ቀደዳ ቀደደ። “ማኪያቬሊ ስለተባለ ዝነኛ ደራሲ ሰምተህ ይሆን? ስለስልጣን ባህርይ እንደ ሌሎች ሳያለባብስ እቅጯን ፅፏል!! ይህ ሀቀኛማንበብ ይቀጥሉ…

ፈገግታ ነው የሚቀድመኝ 

የድሜ ነፋስ በገላየ : ተረማምዶ ኮበለለ ልቤን ክንዴን እያዛለ ያቀፍኩትን እየቀማ : የያዝኩትን እያስጣለ። እድል በኔ ጨከነ ስል-በምረት እጅ ደባበሰኝ አንቺ ነጥቆ ከቅፌ ላይ-በትውስታ ደሞ ካሰኝ። አሰታወሰኝ አስታወሰኝ። ወድያው ታይቶ :ጠፊ ኩርፍያሽ ገራም ሳቅሽ : ልዝብ ልፍያሽ ያለም ዘፋኝ የማያውቀውማንበብ ይቀጥሉ…

ግርምሽ ሲታወሱ

ግርማ ወልደጊዮርጊስ ፕሬዚዳንት ሁኑው የተመረጡ እለት ብዙ ሰዎች ተገርመዋል ። ከእስክንድር ነጋ ጋዜጦች አንዱ ዜናውን የዘገበችው ” ወያኔ አበደች ” በሚል ርእስ እንደነበር ትዝ ይለኛል። አንድ አሙስ የቀረው ሽማግሌ እንዴት ለዚህ ሚና ይታጫል በሚል እብሪት የተቹ አልጠፉም ። ብዙዎቻችን “ሽማግሌማንበብ ይቀጥሉ…

ጉደኛ ስንኞች

እንዳለመታደል ሁኖ የጎጃሙ ጌታ የራስ አዳል ልጆች አሪፍ ያገር አስተዳዳሪ አልነበሩም። እንደመታደል ሆኖ ደሞ የተዋጣላቸው ባለቅኔዎች ነበሩ። ግጥሞቻቸው ከኑሯችን ጋር በጣም የተቆራኙ ናቸው። ለምሳሌ የግፍ ዘገባ በሰማን ቁጥር የምንቀባበለው። “የለህም እንዳልል ይመሻል ይነጋል አለህም እንዳልል እንዲህ ይደረጋል” የሚለውን ገራሚ ግጥምማንበብ ይቀጥሉ…

ሁሉም ለምን ያልፋል?

የጣፈንታ መዳፍ ደስታና መከራን: እያፈሰ ሲናኝ “ሁሉም ያልፋል ” ብሎ : ማነው የሚያፅናናኝ? ግራ በተጋባ :በዞረበት አገር ካንቺ የምጋራው :ሰናይ ሰናይ ነገር ፊቴን የሚያበራው :ያይንሽ ላይ ወጋገን ዛሬ ተለኩሶ : የሚያሳየኝ ነገን ለምን ሲባል ይለፍ : ያንን መሳይ ፍቅር ደሰታሽማንበብ ይቀጥሉ…

ትናንት ዛሬ አደለም

ይገርማል!! ያገራችን ገበሬ የሚያርስበት በሬና ማረሻ ጥንታዊ ሰው ከአራት ሺህ አመት በፊት ይገለገልበት የነበረውን ነው። ይሁን እንጂ ቢቀናው ክላሺንኮቭ ይታጠቃል። ደሞ ገበሬውን ዘመናዊ ጠመንጃ እንጂ ዘመናዊ ማረሻ ለማስታጠቅ የሚያልም አክቲቪስት አይተን አናውቅም። ዘመናይ የብሄር አክትቪስት ጦርነት በናፈቀ ቁጥር ያባቶቹን ጀብድማንበብ ይቀጥሉ…

Loading...