ተማሪዎችን እንረዳቸው!

  የዩንቨርስቴ ተማሪዎች ወገን ለይተው በተደባደቡ ቁጥር ምን አደባደባቸው ብሎ የሚጠይቅ የለም። ከዚያ ይልቅ መስደብ መሸርደድ ማዋረድና ሙድ መያዝ ለምደናል። ባገራችን ከቤተመቅደስ እስከ ስቴድየም ድረስ ጎሰኝነት ያልነካካው ተቁዋም እንደለሌ እናውቃለን። ተማሪዎች ከሌላው የከተማ ነዋሪ የከፋ ጎሰኝነት እንደተሸከሙ የምናረጋግጥበት ሚዛን የለም።ማንበብ ይቀጥሉ…

ጐጆ ቤት

ሀገርስ ጐጆ ናት !!! መሪዋም ምሰሶ ሹማምንቷም ማገር  አንዳንዶቹም ቋሚ ሌሎቹም ወጋግራ ሰራዊቷም አጥር! ሀገርስ ጐጆ ናት !!! ሕዝቡም ክዳን ሆኖ ጐጆውን አልብሶ እንደሳር ቢቀጥን፤ ቢኖር ተራ መስሎ ከዝናብ ያድናል፤ ውርጩን አሰናብቶ ፀሃይን ይከላል፤ በጥላው ከልሎ… ሀገርስ ጐጆ ናት !!!ማንበብ ይቀጥሉ…

በኅዳር ውስጥ እኔን

(የነፍሴ ክስ) ተወው! ቆሻሻህን ተወው  ከሳቱ ዳር እራቅ ጭለማን ልበሰው ጥቁር ካባ ደርብ ዓይንህ ይጨልመው። … ግዴለህም ተወው እቤትህ ግባና ዓይንህን ጨፍነህ ስላሳመምካቸው ስላቆሰልካቸው ነፍሳት አስብና ራስህን ክሰስ ራስህን ውቀስ ራስህን አጥን ተረማመድበት በንፁሀን ፋና። … የነፍስህን እድፍ የውስጥህን ጉድፍማንበብ ይቀጥሉ…

ኖረሽ እይው በቃ

(ለoptimistቶች) ጨለማ ነህ ብለሽ እኔን ስትተቺ ዘልለሽ አትጠግቢ ስቀሽ አትሰለቺ ወርሃ- ፅጌ ነው አመት ሙሉ ላንቺ። ደሞ በየቀኑ ፋሲካ ነው ኑሮሽ ያለም ሰቀቀኑ ሩቅ ነው ለጆሮሽ (የፍጥረት ሰቆቃ) ለጋ ነው አእምሮሽ ገላሽም ነው ጮርቃ ሌላም አልልሽም ኖረሽ እይው በቃ። በየጎዳናሽማንበብ ይቀጥሉ…

ወንዞች

በሕይወት መንገድ ላይ አሉ ብዙ ወንዞች ምንሻገራቸው  ወንዙ ፈተና ነው ፈተናው ፈተና አሉት እልፍ ጭንቆች። ስንቶች ተሻገሩ፤ ስንቶች ተወሰዱ ስንቶቹ ሰመጡ ይኼ ነው ጥያቄው ይኸው ነው ሚዛኑ ይኸው ነው ልኬቱ ሰው ከተፈጠረ ሙት እስኪባል ድረስ አፈር እስኪገባ አሉት ብዙ ወንዞችማንበብ ይቀጥሉ…

Loading...