የትርፍ ጊዜ ሥራ ( ክፍል ሁለት) 

– ቀሚስሽ በጣም ያምራል አለች ገነት ምግብ ቤቱ ውስጥ ገብተን እንደተቀመጥን። – ይሄ? አልኩ በመገረም ቀሚሴን እያየሁ። ተራና ረዘም ያለ ነጭ ቀሚስ ነው የለበስኩት። – አዎ…ቅልል ያለ ነው…ለነገሩ ከመስቀያው ነው…አለች አተኩራ እያየችኝ። (በተሰቀልኩ። እዚሁ እንዳለሁ ተሰቅዬ በሞትኩ!) ፈገግ ብዬ አቀረቀርኩናማንበብ ይቀጥሉ…

‹‹የትርፍ ጊዜ ስራ››

( የታሪክ መዋቅር እና ሃሳብ- የቼታን ባጋት ‹‹ዋን ኢንዲያን ገርል›› አንዲት ዘለላ ታሪክ) ቅዳሜ ስምንት ሰአት ተኩል። አዲሱን ቤቴን ለማደራጀት የቤት እቃዎች መገዛዛት ከጀመርኩ አንድ አመት ሞላኝ። የቀረኝን የመፅሃፍ መደርደሪያ ለመግዛት በባልደረቦቼ ጥቆማ መሰረት ‹‹ፍሎውለስ ፈርኒቸርስ›› የሚባል ቤት መጥቻለሁ። የሱቁማንበብ ይቀጥሉ…

ይበለኝ

በቀደምለት፤አልጄዚራ ያማርኛ ክፍል ጋዜጠኛ ከኔ ጋር አጭር ቃለመጠይቅ አድርጋ ነበር፤ በሁዋላ ግን ቃለ መጠይቁ ከባህላችን ጋር ስለማይጣጣም ልናቀርበው አንችልም የሚል ኢሜል ላከችልኝ፤ ለማንኛውም ሙሉ ቃለመጠይቁ ይህንን ይመስላል፤ “የት ነው የተወለድከው?” -ሆስፒታል “የትውልድ አገርህ ማለቴ ነው” -ማንኩሳ ሚካኤል “በልጅነትህ የሚያስደስትህ ነገርማንበብ ይቀጥሉ…

‹‹ቆንጅዬ›› (ክፍል ሶስት)

አንዳንድ ሴቶች በቁርጥ ስጋ እና ቱርቦ ተደልለው ወደ አልጋ ይሄዳሉ። አንዳንዶች ውድ ሽቶ ሲሰጣቸው ገና ሳይቀቡት ልብሳቸውን ለሰጪያቸው ያወልቃሉ። አንዳንዶች ለቪትዝ የውስጥ ሱሪያቸውን ያስወልቃሉ። አንዳንዶች ጂ ፕላስ ምናምን ቤት ሲያዩ ጭኖቻቸው ይከፈታሉ። አንዳንዶች ላሳቃቸው ወንድ ገላቸውን ይቸራሉ። የእኔ ምስ ግንማንበብ ይቀጥሉ…

‹‹ቆንጅዬ›› (ክፍል ሁለት)

– ወይኔ….ወይኔ! አረ በማርያም ቀስ በይ…ሰጋዬን እንዳትቦጭቂው! አልኩ በጩኸት። ከዚያ ቁንጅናውን ይዞ ከአዲሱ መስሪያ ቤቴ ሊለቅ ለተዘጋጀው- ቀሚሽ ያምራል- ሽሮ ልጋብዝሽ ምናምን ብሎ ላሽኮመመኝ የመጀመሪያው ወንድ ልጅ እራት እየተዘጋጀሁ ነው። የእግሮቼን ጠጉሮች በሞቀ ሰም እያስላጨሁ ነው። ከብስጭት የተሰራ የሚመስል ፊትማንበብ ይቀጥሉ…

‹‹ቆንጅዬ›› 

(የታሪክ መዋቅር እና ሃሳብ- የቼታን ባጋት ‹‹ዋን ኢንዲያን ገርል››)  እንደ እህቴ ቆንጆ አይደለሁም። ሕይወቴን ሙሉ በተደጋጋሚ የሰማሁት አንድ ነገር ቢሆን እንደ እህቴ ቆንጆ ያለመሆኔን ነው። የሁለት አመት ታላቄ ናት። ትምህርት ቤት እያለን ጀምሮ የአባትና የአያታችንን ስም ሰምቶ እስኪያረጋግጥ፣ አንድ ቤትማንበብ ይቀጥሉ…

ለእኔ ያላት እንጀራ (ክፍል ሁለት)

አንዱን ቅዳሜ መስፍኔ ቤት አድሬ ካልጋ ላለመውጣት እገላበጣለሁ። ጥሎኝ ሲወጣ ተገርሜ፣ – በናትህ ዛሬ እንደ ሮማን እና ፀጋዬ አልጋ ውስጥ እንበስብስ አልኩት። የበአሉ ግርማ በተለይ የኦሮማይ ፍቅሩ ሌላ ነው። ከአስራ አምስት ጊዜ በላይ እንዳነበበው ከአስራ አምስት ጊዜ በላይ ነግሮኛል። አልጋማንበብ ይቀጥሉ…

በውቄ እንዴት እንደተፈነከተ!

አባቴ በጣም ትግስተኛና ደመበራድ ስለሆነ ባመት አንድ ቀን ቢናደድ ነው፤ የተናደደ ቀን ግን ምድር አትበቃውም፤ ከደመኞቹ ጋር ሲደባደብ ጣልቃ የገቡ ገላጋዮች “እጁ ላይ ሰው አይበረክትም” እያሉ ያደንቁት ሰምቻለሁ፤ ዘጠነኛ ክፍል እያለሁ፤ በገና በዐል ዋዜማ፤አባየ ከባለንጀራው፤ ከጋሽ ፋኑኤል ጋር አንድ ሁለትማንበብ ይቀጥሉ…

‹‹ለእኔ ያላት እንጀራ››

ሰው አይወጣልኝም። በሰላሳ ሰባት አመቴ ሕይወቴ ከጥቂት ሰዎች የተሰራ ነው። ሁለት በሰላሳዎቹ እድሜዬ ያገኘኋቸው የልብ የማይባሉ ጓደኞች፣ እናቴ፣ አባቴ፣ አንድ ግማሽ እህት (አባቴ ከእናቴ በፊት የወለዳት) እና ጊዜያዊ ወዳጆች። እግዜር ከሰጠኝ ሰዎች ውጪ የእኔ ብዬ ያቆምኩትና የፀና የረጅም ጊዜ ግንኙነትማንበብ ይቀጥሉ…

የዛኔውና የዛሬው ጷግሜ 5 አንድ ናቸዉን?

ጷግሜ 5 በኢትዬጽያ ታሪክ ዉስጥ የራስዋ ድርሻ ኢንዲኖራት ካደረጉ ክስተቶች መሃል የ1966ቱ የኢትዮጵያ አብዮት አንዱ ነበር። ምንም እንኳን ንጉሱም የካቲት 19/1966 ለተነሳባቸው ህዝባዊ አመፅ መፍትሄ ይሆናል በሚል ስልት የጠቅላይ ሚንስትር አክሊሉ ሀብተወልድን ካብኔ አፍርሰው በእንዳልካቸው መኮንን የሚመራ አዲስ ካቢኔ በተማሪዎችናማንበብ ይቀጥሉ…

‹‹ዛሬ ቀኑ ምንድነው?››

(የታሪክ መነሻ ሃሳብ- የካሊድ ሆሴኒ ‹‹ዘ ካይት ረነር›› አንዲት ዘለላ ታሪክ (The Kite Runner- Khaled Hosseini) ተንበርክኬ ነበር። በዚያ የጥቅምት ውርጭ፣ ከምሽቱ አራት ሰአት ተኩል ላይ ከሰማይ በላይ እሪታዬን እያቀለጥኩ፣ ቀዝቃዛው አስፋልት ላይ ተንበርክኬ ነበር። በብርድ በሚንጫገጩ ጥርሶቼ መሃከል እጮሃለሁ።ማንበብ ይቀጥሉ…

ሥግር ልብ ወለድ፤ ሕፅናዊነት (ክፍል 4)

ሕፅናዊነትን በዚህ ዘመን አስፈላጊ ያደረጉት የአገሪቷ ሁኔታዎች መብዛት፣ መስፋት፣ የተለያዩ ብቻ ሳይሆን መያያዛቸውም ነው። ጥቂቶቹን ወይም ክሱቶቹን ልጥቀስ 1. ከስድሳ ስድስት ዓመተምህረት በፊት የዜጎች ስደት ትልቅ ጉዳይ አልነበረም። 2. ሽብር ትልቅ ጉዳይ አልነበረም። 3. በፖለቲካ ምክኒያት መሞት ትልቅ ጉዳይ አልነበረም።ማንበብ ይቀጥሉ…

‹‹ፀዲ››

(መነሻ ሃሳብ- የጁኖ ዲያዝ ‹ዘ ቺተርስ ጋይድ ቱ ላቭ›› አጭር ልቦለድ) ሰው ሁሉ ‹‹ፀዲና ሙሌማ ይጋባሉ። ተጋብተው አራት ልጅ ይወልዳሉ። አብረው ያረጃሉ። ተለያይተው መኖር ስለማይችሉ አንዳቸው ከሞቱ በነጋታው ሌላኛቸው ይከተላሉ›› የምንባል አይነት ነበርን። እኔና ፀዲ። ከተለያየን ሁለት ወራት ሞላን። መጀመሪያማንበብ ይቀጥሉ…

ወንጀል እና ቅጣት (ክፍል ሶስት)

አሳዘነችኝ። በጣም አሳዘነችኝ። ግን ደግሞ አስርባ ሄርሜላን እንድበላ ያደረገችኝ እሷ ናት በሚል ወልጋዳ ይሁን ትክክለኛ ሰበብ ፀፀት ሳይሰማኝ ቀረ። ገፍትራ ሄርሜላ ጉድጓድ የከተተችኝ እሷ ናት….ምናምን እያልኩ በመናገሬ ሳልፀፀት ዝም ብዬ የምትሆነውን አየሁ። ምናልባት የማላውቀው የልቤ ክፍል ለትዳር ዝግጁ ባለመሆኔ አላገባህምማንበብ ይቀጥሉ…

ለመላው የፊንፊኔ እንዲሁም ያዲስ አበባ ነዋሪዎች!

በውቄ ስዩም የተባለ ድህረ- ወጣት ተጋዳላይ ፤ ከተወለደባት እና ከተገረዘባት እናት አገሩ ተሰድዶ፤በዱር በገደሉ፤ በፓርኩ በሆቴሉ፤ በተራራው በስዊሚንግ ፑሉ ፤ሶስት ወር ሙሉ ለናት አገሩ ሲንከራተት ቆይቶ ፤በመጭው መስከረም ሰላሳ በድል ይመለሳል፤ በዚህ ታሪካዊ ቀን የጀግና አቀባበል ይደረግለታል፤ ያቀባበሉ ትንቢታዊ መርሀማንበብ ይቀጥሉ…

Loading...