Tidarfelagi.com

ጐጆ ቤት

ሀገርስ ጐጆ ናት !!!
መሪዋም ምሰሶ
ሹማምንቷም ማገር 
አንዳንዶቹም ቋሚ
ሌሎቹም ወጋግራ
ሰራዊቷም አጥር!

ሀገርስ ጐጆ ናት !!!
ሕዝቡም ክዳን ሆኖ
ጐጆውን አልብሶ
እንደሳር ቢቀጥን፤ ቢኖር ተራ መስሎ
ከዝናብ ያድናል፤ ውርጩን አሰናብቶ
ፀሃይን ይከላል፤ በጥላው ከልሎ…

ሀገርስ ጐጆ ናት !!!
እውነትም ጐጆ ናት
ሊቃውንቷም እሣት
ላንዱ ጭስ ሲደርሰው
ለሌላው ትኩሣት፡፡
ምሰሶው ቢተልቅ – መሪው ገዝፎ ቢታይ
ጐጆው ከቶ አይሞቅም – ካልጫሩበት እሣት
ጐጆው ቤት አይሆንም – ሳር ከሌለው በአናት…
… ሀገርስ ጐጆ ናት !!!…
..
(እንዳለጌታ ከበደ፣ልብ ሲበርደው፣2000)

አስተያየትዎን እዚህ ይስጡ

የኢሜል አድራሻዎ አይወጣም

Loading...