Tidarfelagi.com

ጎልማሳው አጤ ምንሊክ

ይደንቃል ይህ የአጤ ምንሊክ ምስል የተቀረጸው ቢተወደድ አልፍረድ ኢልግ በተባለ የስዊስ ተወላጅ አማካሪያቸው በምዕራባውያን አቆጣጠር በ1880 ዓም አጋማሽ ላይ ገና የሸዋ ንጉስ በነበሩበት የጎልማሳነት ዘመናቸው ነበር ታዲያ የአለባበሳቸው ስርዓት ፣ አናታቸው ላይ ያሰሩት ሻሽ ፤ አንገታቸው ላይ የተደረደረው ጌጣቸው እና የጢማቸው በስርዓት መከርከም ዘዬ የዛሬወቹ ታዋቂ የአሜሪካን የኪነጥበብ አቀንቃኞች እና የመድረክ ከያኔወች እንዳልፈጠሩት መረጃ መሆን ይችላል።

የአጤ ቴውድሮስ እና የአጤ ዮሐንስም የሚያምረው ሹሩባ እንዲሁም የጥንት ጀግኖች የተበሳው ጆሮአቸው ላይ የሚደረድሩት ሎቴ ፣ ከቁርበት ሸበጥ ጋር የሚያጠልቁት ባለእግር ጠባብ ቦላሌ ፤ ጋሜ ጎፈሪ እና የሌሎችም ዘዬወች ምንጩ የኢትዮጲያ ምድር መሆኑን የተለያዩ መረጃወች ቢጠቁሙም ባለመታደል ራሳችንን ከኋላ ፈረንጆችን ከፊት ማደርግ ለምዶብን ነው እንጂ የምዕራባውያን የሚባል ፋሽን ከቶ በዚህ አለም የለም።

ጥንት ምዕራባውያን ባዶ እጃቸውን ወደ አገራችን ምድር ዘልቀው የአባቶቻችን ስልት እና ጥበብ ቀስመው ወደ ቀዬአቸው ተመልሰው የራሳቸውን ኑሮ አሻሽለው እና ሰልጥነው ዛሬ ከእኛ በሺህ ኪሎ ሜትር ወደ ፊት መጥቀዋል እኛ ደግሞ ይሄው ትለብሰው የላት ትከናነበው አማራት እንዲሉ ሆዳችን ሳይጠግብ የማንነት ጥያቄ እያለን ዕርስ በዕርስ እየተናቆርን ከገድል ዳር ደርሰናል።

ለማንኛውም አንድነታችን ይጽና በዝች አጭር ህይወት ውስጥ የአገር ልጅ ይቅደም።

አስተያየትዎን እዚህ ይስጡ

የኢሜል አድራሻዎ አይወጣም

Loading...