Tidarfelagi.com

ግን እስከመቼ!?

እንግዲህ መቼም ሀገር እንዲህ ተወጥራ የተለመደውን የፖለቲካ ጸጉር ስንጠቃችንን ለዛሬ ማካሄድ ነውር ነው

በቀጥታ ወደ ገደለው ስንገባ በአዋሳ እና በወላይታ ሶዶ ክቡሩ የሰው ልጅ እንደ አውሬ እየተገደለ ነው። በጣም…. በጣም …..ያማል…! በዚህች በችጋራም አገር በአተት እና መሰል በሽታዎች ከሚሞተው ወገናችን በተጨማሪ እንዴትስ አንዲትስ ነብስ በድድብናችን ምክንያት ትጠፋለች??! ከጓደኞቼ በደቡብ ክልል ስለደረሰው ሰቆቃ በስልክ መረጃውን ሰምቼ የነበረ ቢሆንም መንግስት በጉዳዩ ላይ ዝምታን በመምረጡ እኔም ወሬውን በማራገብ ይህን ነገር ከኋላ በመሆን ለሚዘውሩት “የቀን ጅቦች” መሳሪያ ላለመሆን ዝምታን መርጬ ነበር። (አብይ የቀን ጅቦች ያላቸው እነማን እንደሆነ ማንም ለአቅመ ፌስቡክ ማንበብ የደረሰ ሰው ያውቃል ብዬ ስለምገምት ስማቸውን በመግለጽ ጊዜ አላጠፋም…..)

እንደማየው ብዙዎቻችን የመረጥነው የጉዳዩን መንስኤ በማውገዝ ላይ ነው።በእርግጥ እውነት ነው….”ታላቁ መሪ” መለስ ዜናዊ እና ጓዶቹ ለ27 አመታት የለፉበት ስራ ዛሬ ፍሬ አፍርቶ ሰብሉ እየታጨደ ነው።ባለ ወርልድ ክላስ ማይንዱ.. አሰላሳዩ እና ምጡቁ መሪ ከበረሃ ጓዶቹ ጋር ለ17 አመት ከኢትዮጲያ ጋር ከተዋጋ በኋላ በለስ ቀንቶት የዚህች ከ60 ሺ በላይ ወገኖቹን የሰዋችበት አገር መሪ መሆን ችሏል…..የመጀመሪያ ቀን ስራውንም አገሪቷ በተፈጥሮዋ የተጎናጸፈችውን ወደብ በማሳጣት ጀመረ ….ለጥቆም ……በደቡብ አፍሪካ ነጮቹ ይከተሉት የነበረውን አፓርትአይድ ሲሰተም (…ኮሜዲያኑ ትሬቨር ኖዋህ (ኖህ) አፓርት- ሄት (ከፋፍለህ -ማጠላላት) ሲለው ሲስተሙን የበለጠ ይገልጸዋል ) የአገሬውን ተወላጅ ……ጦሳ …ዙሉ ..ጽዋና ..ዎንጋ…. ፔዲ …. ..ንዴቤሌ……አንዱን ካንዱ በነገር እያባሉ በባርነት እንዳኖሩት ሁሉ መለስና ጓደኞቹ በትረ ስልጣኑን ከተቆናጠጡ በኋላ በጥላቻ ትርክቶች ያጀሉት ህዝብ ምንም እንኳን በራሱ ቋንቋ መማሩ ፡መዳኘቱ…ወዘተ….አንድ ነገር ቢሆንም በከፋፍለህ አጠላላ ፖሊሲው አገሪችን ኣሁን ላይ ለደረንስበት አስከፊ ደረጃ ላይ ልትወድቅ ችላለች….…ግን ለምን ….?!

ግን ለምን?!

መቼም ቢሆን መልስ የማላገኝለት ጥያቄ ነው….
ዛሬ በአዋሳ ሲዳማው ወላይታውን ያጠቃል….በወላይታ ደግሞ ሲዳማ ይጠቃል…..ይህ የዘረኝነት እሳት እየተሸከረከረ ያልጎበኘው የለም….ኦሮሞው ተፈናቅሏል ተገድሏል..አማራውም ትግሬውም ….ሲዳማውም ወላይታውም..አኝዋኩም ኝዌሩም..ሶማሌውም…..ጉራጌውም ….ሁሉም በየተራ የዚህ እሳት ሰለባ ሆኗል….. ይሆናልም…..
የቀን ጅቦች …እዳሪያቸውን ከመብላት የማይመለሱ አሳሞች ……ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ ሲሉ ነገን የሚያጨልም ማናቸውንም ነገር ዛሬ ለመወጠንም ሆነ ለመፈጸም ወደኋላ የማይሉ ደም መጣጭ ቫንፓየሮች አገራችንን ለመበታተን ቆርጠው ተነስተዋል..….ከነሱም በታች በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ፍርፋሪ ለመልቀምም ከስራቸው የሚያቶሰቱሱ መሃይሞችም በየቦታው..ተደራጅተው የሚወርድላቸውን ትእዛዝ በተጠንቀቅ እየተጠባበቁ ይገኛሉ…

እናስ?!

እቺ በብዙ መሰዋትነት በደምና በአጥንት የተገነባች ታላቅ አገር ግን በእሪያዎች የደመነፍስ እንቅስቃሴ ትፈርስ ዘንድ ልንፈቅድ አይገባም …..ሁላችንም ያለን ጥንካሬ አንድ ና አንድ ብቻ ነው ……አሁን የጋራ ጥላት ያለን በመሆኑ ድሮውኑም ጥንካሬያችን አንድነታችን በመሆኑ ፈጣሪም አሳፍሮን የሚያውቅ ባለመሆኑ በምንችለው ሁሉ ይህችን አገር እጅለእጅ በፍቅር ተያይዘን ጥላቶቻችንን እናሳፍራቸው ( ወደ ልዩነታችን ለመመለስ ገና ሰፊ ግዜ ስላለን ያኔ እንደርሳለን)…..። ጠላቶቻችን ገና ብዙ ገና ብዙ የደገሱልን ነገር ይኖራልና እባካችሁ እንንቃ!

በአዋሳ የሚሞተው ወላይታ አንተ ነህ! …በወላይታ የምትሞቺው ሲዳማ አንቺ ነሽ!……ከቤንሻንጉል እና ከሶማሌ የተፈናቀለው የአማራና የኦሮሞ ህዝብ እኔ ነኝ!…..

ይህቺ አገር ወደ ቀድሞ ሰላሟ ሙሉ በሙሉ እስከምትመለስ ድረስ ሁላችንም ደ/ር አብይ አህመድ ነን።
ይመቻችሁ

One Comment

  • Kassahailu6@gmail.com'
    ጀማሉዲን ሚፍታ፡፡ commented on June 30, 2018 Reply

    Andualem you have used much insult.; any ways, thanks for your effort and Andmeta for your offer.

አስተያየትዎን እዚህ ይስጡ

የኢሜል አድራሻዎ አይወጣም

Loading...