Tidarfelagi.com

…ገነት

” እየተስለመለምኩ ፊትዋን በሁለት እጆቼ ያዝኩ . .
አሟልጮኝ እንደሚወድቅ ሁሉ. . .
እንደሚፈስ ሁሉ . . .
ፊቴ ገነት ፊት ላይ ወደቀ…
አፌ ዉስጥ ከንፈሮቿን እንደ ቢራቢሮ ክንፎች ይዤአቸዋለሁ
በገላዬ ዉስጥ አየር እንደሚያልፍ ሁሉ ነበር . . .
እንኰይ እንኰይ ከሚል…..
ዉሃ እናቶች ከሚከናበሉበት የአምቦ ምንጭ ዉስጥ እንደተኛሁ ነበር . . .
ዐይኖቿ … ወተት መሃል እንደወደቁ አጋሞች ነበሩ . . .
ልቤ እንዳይፈነዳ እፀልያለሁ ..
ልቤ እንዳይፈርስ እንቀጠቀጣለሁም …
ጣቶቼ በጀርባ ቆዳዋ ላይ ተማስለዉ እንደተኙ ነበር
ደማችን ተደባልቆ ሲፈስ…..
ፈረሰኛዉ ከተራሮች በላይ ነበር
መዝፈን አማረኝ . . .
እንደ ንጋቷ ከልካይ መዝፈን አማረኝ…
እንደጥላሁን መጮህ አማረኝ…
እንደ አስቴር መተከዝ አማረኝ….
እንደ ሙሉቀን መጨፈር አማረኝ….
ከእግሮቻችን ስር የዚህች ከተማ የልብ ምት ከተቀበረበት ይሰማኛል…
የዚህች ሀገር የልብ ምት ከተቀበረበት ይሰማኛል….
የዚህች ምድር የልብ ምት ከተቀበረበት ተሰማኝ መሰል….
በከንፈሮቼ ተሰማኝ መሰል….
በአጥንቴ ተሰማኝ መሰል….
በጉበቴ በጣፊያዬ ተሰማኝ መሰል….
በብልቶቼ ሁሉ ተሰማኝ መሰል….
ገነት ከሩቅ እንደሚሸት ትኩስ ህብስት ነበረች . . .
ይቺ ልጅ ተጣጥፋ አፌ ዉስጥ እንደ ናና ከረሜላ ነበረች ….
#ግራጫ_ቃጭሎች
አዳም ረታ አንጋፋ የሀገራችን ደራሲ ነው፡፡

አስተያየትዎን እዚህ ይስጡ

የኢሜል አድራሻዎ አይወጣም

Loading...