Tidarfelagi.com

የመጀመሪያው ፎቶግራፍ እና ክሊኒክ ኣጀማመር በኢትዮጵያ

ዳግማዊ ምኒልክ ከዘመናዊነት ጋር ተያይዘው ከሚነሱባቸው ነገሮች መካከል አንዱ ፎቶግራፍ ይገኝበታል፡፡ ፎቶግራፍና ኢትዮጵያ የተዋወቁት በርሳቸው ዘመን እንደሆነ ይወሳል፡፡ በታሪክ እንደተመዘገበው ፎቶግራፍ አንሺ ከካሜራው ጋር ኢትዮጵያ የገባው በ1875 ዓ.ም. ነው፡፡

በወቅቱ የነበሩት ኣማካሪዎች አንደዘገቡት አና ቡሃላም በ በጳውሎስ ኞኞ ተተርጉሞ አንደቀረበው ዓጼ ምኒልክ አንድ ቀን የውጭ አማካሪያቸውን ጠሩትና “አንድ ነገር ሰማሁ። ይሄ የሰማሁት ነገር እኔን ትንሽ ያደርግና ከነቤተመንግስቴ፣ ሌላው ቤት ሁሉ፣ ህዝቡ፣ በቅሎና እና ፈረሱ ሁሉ ሳይቀር እትንሽ ጥቁር ሳጥን ውስጥ ይጨምረናል አሉ። ይሄ ነገር ፈፅሞ የማይቻል ነገር ነው እንዴት ሊሆን ይችላል?” አሉት።

ከዚህ በሇላ ካሜራ እንዲመጣ ታዞ ካሜራው ከነ ፎቶግራፍ አንሺው በ1875 ዓ.ም. መጣ። የፎቶግራፍ ማንሻው አዲስ አበባ ከመጣ በሇላ ዓጺ ምኒልክ ፎቶ እንዳይነሱ ቀሳውሥቱ አስፍራርተዋቸው ነበር። ሆኖም ግን ዓጼ ምኒልክ ምክራቸውን ወደ ጎን በመተው የመጀመርያውን ፎቶ በግንቦት 13 ቀን 1875 ዓ/ ም ተነሱ። ምኒልክ የመጀመሪያ ፎቶግራፍ የተነሡት ግንቦት 13 ቀን 1875 ዓ.ም. መሆኑንና የቤተ መንግሥት ፎቶግራፍ አንሺ ሆኖ የገባው ቦያጂያን ከሁለት ዓመት በኋላ የሕዝብ ፎቶግራፍ ማንሳት ሱቅን መክፈቱ በጳውሎስ ኞኞ በተዘጋጀው ‹‹አጤ ምኒልክ›› መጽሐፍ ውስጥ ሰፍሯል፡ ዓጼ ምኒልክ ፎቶ ከመነሳት አለፈው ፎቶ ማንሳት እና ማጠብም ጭምር ተምረው እንደነበር ይታወቃል።

Atse_Menelik4

መጀመሪያው ክሊኒክና ፋርማሲ በ1889 ዓ.ም. በቤተ መንግሥታቸው ውስጥ ያቋቋሙት ዳግማዊ ምኒልክ ናቸው፡፡ በዓድዋው ጦርነት ምክንያት ከሩሲያ ቀይ መስቀል ማኅበር የተላኩት ሐኪሞች አዲስ አበባ በተገኙበት ጊዜ ሥራቸውን የጀመሩት ካገራቸው ይዘው በመጡት ድንኳን ውስጥ መሆኑ በታሪክ ተመዝግቧል፡፡ ጎጆ ቤትም ተሠርቷል፤ በየጊዜው ንጉሠ ነገሥቱ ከክሊኒኩ እየተገኙ ሕሙማኑን ይጎበኙ ሐኪሞቹንም ያነጋግሩ ነበር፡፡ የሩሲያ ቀይ መስቀል ማኅበር ሕክምና በሚሰጥበት ጊዜ ምኒልክ በሥፍራው በመገኘት ያበረታቱ እንደነበር በተጠቀሰበት ‹‹አጤ ምኒልክ›› መጽሐፍ ውስጥ የእሸቸሴፍን ቃል እንዲህ አስፍሮታል፡፡

‹‹… ኦፕራሲዮን በምናደርግበት ጊዜ ምኒልክ በኦፕራሲዮን ክፍል መገኘት ይወዳሉ፡፡ … በዚያም ቆመው የኦፕራሲዮኑን ሥራ በሚመለከቱበት ጊዜ የበሽተኛውን እጅ ይይዛሉ፡፡ በኋላም ኦፕራሲዮኑ አልቆ በሽተኛው እስቲነቃ ጠብቀው ሲነቃ እግዚአብሔር ይርዳህ፣ እሱ ያድንህ ብለውት ይሄዳሉ፡፡…›› ብሏል፡፡
ምንጭ:
አጤ ምኒልክ
በጳውሎስ ኞኞ

አስተያየትዎን እዚህ ይስጡ

የኢሜል አድራሻዎ አይወጣም

Loading...