Tidarfelagi.com

የ deቫልዌሽኑ ጉዳይ

(ንፋስ አመጣሽ ንፋስ ወሰደሽ )

መጀመርያ ይቺን የድሮ ዜና ያዝልኝ

[Jan 2011 – የ ብር ዲቫልዌሽንን ተከትሎ የኢትዮጵያ ባንኮች በነፋስ አመጣሽ ታክስ 1.5 ቢልየን ብር ለመንግስት ከፈሉ።]

ሀገሪቷ ያደረገችውን የትላንቱን የውጭ ምንዛሬ ማስተካከያ ተከትሎ ብዙ ብሶቶች ጭንቀቶች ና እስተያየቶች እያየሁ ነው።

(ጀለሶቼ ! )

ጉዳቱ ጥቅሙ ምናምን ብዬ አዛ አላደርጋችሁም ። ግን ለመግቢያ ይህል; ዲቫልዌሽን፡ መንግስታት የወጪ ና የገቢ ንግድ imbalance ን ልክ ለማስገባት የሚጠቀሙበት ዋነኛ ና አለምአቀፍ የፋይናንስ ፖሊሲ tool ነው። የራሱ ሳይድ ጉዳቶች አሉት ።ምንም ጥያቄ የለውም !

ይመራል፣ ራስምታት ይኖረዋል ፣ ሆድቁርጠትም ጭምር ግን ዋናውን በሽታህን ለማስታገስም ይሁን ለማዳን የግድ ትውጠዋለህ።

ደግሞም በየቀኑም ቢሆን ብር የመግዛት አቅሙ በትንሹ እየቀነሰ ነበር ። ዋናው አከራካሪ ጉዳይ መሆን ያለበት በአንዴ መሆኑ ይሻላል ወይስ ቀስበቀስ ? ( ሌላ ግዜ እንከትፈዋለን)

አሁን ግን በዚህ የዲቫሉዌሽን ቀን ሊፈጠር የሚችለውን የ ሁለት ነጋዴዎች ና ባንኮቹን ወግ በአጭሩ 😜ጀባ ልበላችህ !

(1-ጀማሪ አስመጪ ነህ)

የ ቀላል የኢንጅነሪንግ ዕቃዎችን ለማቅረብ የወጣ የ መንግስት ጨረታ ትሳተፋለህ፣ ያው ጀማሪ ስለሆንክ ዋጋ ሰበር አድርገህ በትንሽ ትርፍ ትገባለህ (የ 20ሚልየን ብር ዋጋ ስታስገባ ውድድሩ ከፍተኛ ነውና 15% የትርፍ ህዳግ ከበቂ በላይ ነው ትላለህ)

እናም

ረጅም ጊዜ ከሚፈጀው የ ቴክኒካል ኢቫልዌሽን ና የዋጋ ውድድር በኋላ አሸናፊ መሆንህ ይገለፅልሀል በ 3 ወር ውስጥም ዕቃውን ለማቅረብ ተስማምተህ ውል ትዋዋላለህ…..ወዳጄ የዚህን ያህል ጨረታ አሸንፈህ መቼም ዝም አይባልም….ጔደኛ ፣ቤተሰብና ዘመድ እንኴን ደስ አለህ ይሉሀል ያው አንድ ሳምንት ፌሽታ ይሆናል።👏👏

እንግዴህ 15% ትርፍ 25% ደግሞ ቀረጥን ጨምሮ የተለያዩ cost ተቀናሽ አድርገህ ዕቃዎቹን ለማዘዝ የ500 ሺህ ዶላር የውጭ ምንዛሬ እንዲፈቀድልህ ትጠይቃለህ (ያው ባለፈው ምን እንደተባለ ትዝ ይላችኌል )

ዶላሩ እስኪፈቀድ ብትጠብቅ ብትጠብቅ ….ወፍ የለም !
አንድ ፣ ሁለት….እያለ 3ኛ ወር መምጣት ጀምሯል ።
በውሉ መሰረት በ 3 ወር ለማስረከብ የተዋዋልከው ነጋዴ ገና ዕቃውን አላዘዝክም……🤔🤔🤔

ጭንቅ ጥብብ ይልሀል

(ያዝ !)
** ውሉን ስትዋዋል ፣
-ውሉን በአግባቡና በግዜው ለመፈፀምህ ዋስትና (Performance bond) 10% (የ 20 ሚልየን 2 ሚልየን ብር መሆኑ ነው) አሲዘሃል።
– ጀማሪ ከሆንክ ደግሞ መናጢ ነህ ማለት ነውና 30% ቅድሚያ ክፍያ ትፈልጋለህ ፣ያው ለሱም ተመጣጣኝ ዋስትና (advance guarentee)ታሲዛለህ።**

ያው ዕቃውን ካላስረከብክ ይህ ገንዘብ ና ያስያዝከው ንብረት ለመንግስት ገቢ ይሆናል ፣ ከአቅራቢ ዝርዝር ውስጥ ትሰረዝና በገንዘብ ና ኢኮኖሚ ሚንስተር ጥቁር መዝገብ ውስጥም ስምህ ይሰፍራል።

ያው ስኳር ፣ ደም ብዛት ምናምን ይጀማምሩሀል !
የባንኩን ሰዎች ምንተሻለኝ ብለህ ታማክራለህ

የባንኩ መሳፍንቶችም ከ ላኪዎች ጋር የሚቀረጭፉትን በአንድ ዶላር 3 ብር ትደራደራለህ 500ሺህ ዶላሩን ስትመታው 1.5 ሚልየን ብር ገና ከጅምሩ ባልጠበከው ና ሂሳብ ውስጥ ባላስገባህበት ሁኔታ ትቀረደዳለህ።

ነገር ግን የዛሬን ብትሸወድ ነገን መስራት አለብኝ ብለህ፣ ባታተርፍም የተሻለውን ኪሳራ ትመርጣለህ ።
በ 11 ኛው ሰዓት (በ3ኛው ወር) ም ቢሆን ዶላሩ ተፈቅዶልህ ለሰፕላየርህ(ፋብሪካው) ትዕዛዙን ትሰጣለህ።

ግን ሌላ ችግር አለ !
አሁን ውሉን ከሰጠህ ድርጅት መደወል ይጀምራሉ……..
……..”ዕቃው ከወየት ነው? በጊዚው አላስረከብክም፣
ውሉን ልንሰርዘው ነው ” ይሉሀል …..
በመሀል ለመሳፍንቶቹ ምቹ ግዜ ይፈጠራል።
🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔

ሌላ ራስምታት፣ ጭንቅና ድብርት

አየህ ውሉ ቢሰረዝብህ በ 3 ድንጋይ ትመታለህ (ይጥበቅ)።
ለዋስትና ያስያዝከው ገንዘብ ይወረሳል፣ ዕቃውን ከፍለህበታል (አምጥተኸው ማንም ላይገዛህ ይችላል)፣ ጨረታም ካሁን በኋላ መሳተፍ አትችልም……ምኑቅጡ …

ስለሆነም የመሳፍንቶቹ የመደራደር አቅም ከፍተኛ ነውና 2%(2%* 20,000,000= 400 ሺህ መሆኑ ነው) ትለቅላቸዋለህ።

(ያዝ!)
*** ከማስረከብያው የመጨረሻ ቀን በኋላም ቢሆን ለሚዘገየበት እያንዳንዱ ቀን 0.01% of the total amount በቅጣት መልክ ለውል ሰጭው መክፈልህ አይቀርም።***

አሁን ዕቃው በመርከብ ተጔጉዞ በሳምንታት ውስጥ ጅቡቲ ይደርሳል ከ ዛም በኋላ ሞጆ ደረቅ ወደብ ደርሶ ለመቀረጥ ዝግዡ ይሆናል ።
ያው ቀጣዩ ስራህ የ ባንኩን ሂሳብ ከፍለህ የጉዞ ና ሌሎች ዶክመንቶችን ከባንኩ ተረክበህ ለ ጉምሩክ ክሊራንስ ማዘጋጀት ነው። የገቢ ሰነዶቹም ከ ቀናት በኋላ ከ ሰፕላየር ባንክ ወዳንተ ባንክ ይደርሳሉ።

“የማያልፍ የለም ያ ሁላ አለፈ”
እያልክ ልታዜም ደርሰሀል 🙃🙃

ግንግን
( 30-01-2010 ዓም )
አንድ እንደመብረቅ የሚያደርቅ ዜና ትሰማለህ…..
😱😱😱😱😱😱😱😱😱😱
የዶላር -ብር ምንዛሬ በ 15% እንዲጨምር መታወጁን ! ( በአንድ ዶላር 3.51ብር ጭማሪ)

(ያዝ)
**መንግስት በአንድ ግዜ ከፍተኛ የሆነ የምንዛሬ ለውጥ ያደረገው ከ 7 አመት በፊት ነው የየቀኑን ለውጥ ልታስብ ትችላለህ እንጂ እንዲህ አይነት ደራሽ ይመጣብኛል ብለህ speculate ለማድረግ የሚያስችል ብቃትም የኢኮኖሚ ምህዳርም የለም።**

ቤቃ ትደነግጣለህ፣ ትበረግጋለህ፣ ኢንዴ ምንአጠፋው? ትላለህ፣ በቃ ምስቅልቅል ይልብሃል ፣ ስልክህን አውጥተህ ካልኩሌት ታደርጋለህ (500ሺህ $* 3.51= 1.7 ሚልየን ብር )

ይህ ብቻ አይደለም ጉምሩክም ቀረጡን የሚያስከፍለው በአዲሱ የዶላር ምንዛሬ ተምኖ ይሆናል።

ወደ ባንክህ እየበረርክ ትሄዳለህ የጉዞ ሰነዱ አልመጣም ወይ ትላለህ ? እንዳልመጣ ታውቃለህ ነገር ግን በ ሁለት ቀን ውስጥም እንደሚደርስ መረጃው አለህ ግን …..
ምንምምምምም ማድረግ አትችለም በ ሁለት ቀን ልዩነት ለ አንዱ ንፋስ ሲያመጣለት ለአንተ ንፋስ ይወስድብሃል።

(ያዝ!)
** በገቢ ወጪ የንግድ ስርዐት ( ከ TT የክፍያ ስርአት ውጭ) ውስጥ ለክፍያ ተግባራዊ የሚደረገው የምንዛሬ ቀን የመጨረሻው ዶክመንት ደርሶ ሂሳብ የተሰራበት ቀን ነው።**

አተርፋለው ብለህ የገባህበት ውል በምንዛሬ ውጥንቅጥ ምክንያት ያለህንም ይዞ ይሄድና እዬዬ ትላለህ ፣ ሀገሪቷን፣ ህዝቡን ትራገማለህ !
ያንተ እርግማን ደግሞ አይደርስም ማለት ዘበት ነው ….ንፁህ ነሃ !!

(2-ላኪ /ኤክስፖርተር)

እዚህ አገር ላኪ ማለት አያት ያሳደገው ልጅ አይነት ሞልቃቃ ነው። ሲጀመር ከየትኛውም የአለም ክፍል የሽያጭ ውል አምጣ እንጅ የትኛውም ባንክ እጅህን ስሞ የ ውሉን መጠን (contract value ) 100% ብድር ይፈቀድልሀል። ሲቀጥል ተጨማሪ የካፒታል እና የስራ ማስኪያጃ ብድር ከየትኛውም ነጋዴ በፊት ቅድምያ ይሰጥሀል።

ግንግን የዚህ ሁሉ ማሞላቀቅ መነሻ ምን እንደሆነ ይገባሀል እንደሀገር የውጭ ምንዛሬ ዕጥረት desperate አድርጎናል
የባሰው ነገር የ ግል ባንክ CEO ዎች ሳይቀር የላኪዎችን በር እያንኴኩ ምን እናድርግላችሁ? ይላሉ ።

እነሱም የሚፈልጉትን ያቃሉ….ዶላሩን !
ዶላሩን
ዶላሩን

እኛ ስቃያችንን በልተን ያመጣነውን ዶላር ለምንድነው የማንም ኩታራ አስመጪ የሚጠቀምበት ነው ? ጉዳዩ ።

(ያዝ!)
*** የ ውጭ ንግድ ( export) ትርፍ ህዳግ ከ -10% እስከ 10% ብቻ ነው( የባሰ ኪሳራም የሚመጣበት ግዜ አለ)**

ለባንክ ኢንደስትሪው የዶላር ነገር ሆድ ይቆርጣል ነውና
ብሄራዊ ባንክን የሚያስቆጣ ሙስናውን የሚያቀጣጥል ቢሆንም…….ሁለት አይነት የማሞላቀቅያ ሜዳ ለላኪዎቹ ተሰጣቸው ።

ዶላሩን አስገባ እንጅ አንድም እንሸጥልሃለን ካልሆነም አንተው ታስመጣበታለህ ። deal !

ይሄኔ ነው በዶላር አንድ ብር …ሁለት ብር….ሶስት ብር…..የምትባል ፀዴ የቢዝነስ ጨዋታ የመጣችው።
ያው ከ ቅርንጭፍ ስራ አስኪያጅ እስከ የባንኩ ስራ አስፈፃሚዎች፤ ከ ኤክስፖርተሩ እስከ ደላላው ድረስ የሚያስተሳስር ደንበኛ ቢዝነስ ።
ቅድም ያያቹትም አስመጪ የከፈለው 1.5 ሚልየን የገባው እነዚህ ሰዎች ኪስ ነው።

ይሄ ካላዋጣ ደግሞ የአስመጭነት ፈቃድህን ታወጣና የፈለከውን ሸቀጥ አምጥተህ ትሸቅላለህ (የ ቢዝነስ መስመርህ ሆነ አልሆነ ምንተዳህ) አንተብቻ የሆነ ነገር በኪሳራም ወደውጭ ላክ እንጅ ከዋናው አስመጭ የተሻለ ዶላር የማግኘት ዕድል አለህ ምን ከአስመጭው ብቻ ከመንግስትም የተሻለ ዕድል አለህ 😃😃😃
(እንደውም ኤክስፖርተር ሁላ አስመጭም ነው !!!)

የትምህርት መሳርያዎች፣ medical supplies ና መድሀኒቶችን ለማስመጣት እንኳ ራሳቸው የመንግስት መስርያቤቶች እየተሳናቸው አንተ ግን ወይ ገበያ ላይ ዕጥረት የታየበትን ሸቀጥ አምጥተህ ትቸበችባለህ አልያ ህጋዊውን የባንክ system ተጠቅመህ የጥቁሯን ገበያ አጠባ ትለበልባለህ።

(ያዝ!)
*** በ ኤክስፖርተር ስም የውጭ ምንዛሬ ብቻ ሳይሆን የፈለገውን ያህል ብድርም መውሰድ ይችላል ***

እናምን ይጠበስ ?
እትቸኩላ
እየመጣሁ ነው

ይሄ ሁላ ሲሆን ብሄራዊ ባንክ ያውቃልና ችግሩን /ሙስናውን/ ኢፍትሀዊ የዶላር አሰጣጡን ለመቅረፍ ብዙ ሞክሮ ሞክሮ ….ባለፈው አመት ግን የአንድ ባንክ አመራሮችና ቦርዱን ሳይቀር አጥረግርጎ ካነሳ በኋላ የውጭ ምንዛሬ አሰጣጡ ላይ ስትሪክት መመርያ በተነ።

ሲጀመር ያለትርፍ የኤክስፖርት ንግድ እየሰራ ከጀርባ በሚገኝ ጥቅም ተሞላቆ የቆየው ላኪ ሁላ ቀጥ አለ…ለወራትም ምንም ኤክስፖርት ሳያደርግ ቆየ ።ሲያሻውም ከመንግስት ጋር ለመደራደር ሞከረ !
መንግስት ግን ያለትርፍም ቢሆን ኤክስፖርት እንዲያረግ ቢያስገድደውም የውጭ ንግዳችን ግን ያድጋል ተብሎ ሲጠበቅ ጭራሹኑ ማሽቆልቆሉን ያዘው።

(ያዝ !)

*** የዚህ ሁላ መሞላቀቅ/ሙስና እና የተዘባረቀ የምንዛሬ ሂደት መነሾው የማያዋጣ የውጭ/ኤክስፖርት ንግድ ነው። ለዚህም መስሎኝ የውጭ ምንዛሬ ማስተካከያ ማድረግ የሚያስፈልገው።***

እና ይኸውልህ ዛሬ ግን ለብዙ ላኪዎች የፌሽታ ቀን ነው!!

አስበዋ !

ከ ወራት ወይም ቀናቶች በፊት 1 ሚልየን ዶላር የሚገመት የሰሊጥ ወይም ቡና የአቅርቦት ውል ለመፈፀም ከውጭ ኩባንያ ጋር ተፈራርመሀል።

ያው በትርፉ ደስተኛ ባትሆንም ኤክስፖርት የማድረግ ህጋዊ እና አገራዊ ግዴታ አለብህና የሚላከውን የግብርና ምርት ከ ገበያ (ecx)ገዝተህ እና ሁሉንም ዶክመንቶች አዘጋጅተህ ጨርሰሃል ምርቱንም በጅቡቲ በኩል መርከብ ላይ ተጭኖ ከተፈለገበት ደርሷል ። ክፍያህ ከ ገዢው ባንክ እስኪለቀቅልህ እየጠበቅክ ነው።

ግን ግን
30-01-2010
እንደ ሎተሪ ዜና ያልጠበከውን ትሰማለህ
😀😀😀😍😍😍😍😍😍😍😍😍
የዶላር – ብር ምንዛሬ በ 15% እንዲጨምር መታወጁን ( አንድ ዶላር 3.51ብር ጭማሪ)

እናም ከቀናት በኋላ ክፍያው ሲደርስህ 1,000,000 * 3.51= 3.5 ሚልየን ብር ኔት፣ ያልተጠበቀ ንፋስ ያመጣው ትርፍ እጅህ ይገባል። ሀሌሉያ !!
እግዚአብሔርን ታመሰግንናለህ ። ለሰከንድ እንኴ ያልጠበከው ገንዘብ ኪስህ ይገባና መንግስትን ሳይቀር ትመርቃለህ።

(3-ባንኮች)

ከላይ የጠቀስኩት ዜና በ 2010 የተደረገውን ከፍተኛ ዲvaluation ተከትሎ ከልማት ባንክ በስተቀር ሁሉም ባንኮች በአጋጣሚ ወይም ንፋስ አመጣሽ ሁለት ቢልየን ብር ማትረፋቸውን ተከትሎ 75% (1.5 ቢልየን ብር) ለመንግስት በታክስ መልክ እንደከፈሉ የሚያሳይ ነው።

እናማ ነፋስ የወሰደባቸውና ኪሳራ ውስጥ የገቡት አስመጭዎች እንግዲ ብራቸው ማንጋር እንዳለ መገመት አይከብድም።

አሁን ጥያቄው መንግስትና ባንኮች ንፋስ አመጣሹን ገንዘብ በኑሮ ውድነት ምክንያት ለሚሰቃየው ህ/ሰብ እንዴት አድርገው ይደጉሙበት መሆን አለበት።
😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢😰😢😢

በቃኝ በቃኝ አንዛዛሁት
ተሳስቼ ነው
ይቅርታ !!!

One Comment

  • bazezo74@yahoo.com'
    Ane commented on October 16, 2017 Reply

    What an article! So much as it is funny and articulated, it contains tons of info which otherwise many so called economic experts would struggle to explain. Kudos to Michael!
    Please keep it up.

አስተያየትዎን እዚህ ይስጡ

የኢሜል አድራሻዎ አይወጣም

Loading...