Tidarfelagi.com

የጥልቁ ትንታኔ

በቀደም ስለሉሲፈር ፊልም በፃፍኩት ፅሁፍ ስር አንዱ “ትውልዱን በማር የተለወሰ መርዝ እያስነበብሽው ነው” ብሎኝ ሳቅቼ ሞተውት። እናውራ እንዴ? የትኛውን ትውልድ? ይሄ ትውልድ ቲክ ያላደረገው የሉሲፈር ስራ አለ ነው የምትሉኝ? ይሄ የኔ ዘር አይደለህም ብሎ ወንድሙን ዘቅዝቆ የሚሰቅለው ትውልድ ሉሲፈር እሩቁ ሆኖ ማለት ነው? ይሄ የኔ ሀይማኖት ተከታይ አይደለህም ብሎ ቤት በእሳት የሚለኩሰው ትውልድ? ይሄ በቀደም ሰው ከነነፍሱ እያነደደ በእርካታ ሲያብድ ያየነው የትውልዳችን አካል ከሉሲፈር በጣም ርቆ ማለት ነው? ተውኣ!

ሉሲፈር ራሱ ሳድግ እንደሱ ነው መሆን የምፈልገው የሚያስብለውን ክፋት በውስጣችን አጭቀን ጣታችንን ምንጠቁምበት አጋንንት አንፈልግኣ! Focus on yourself! የጥልቁ ትንታኔ ላይ ትደርስበታለህ! እስኪ የጥልቁን ሴራ ትንታኔ ወደጎን አድርገን የጥልቁ ስራችንን እንተው። ምቀኝነት ፣ክፋት። በወንድማማች መሃል ፀብን መርጨት፣ መግደል፣ የሰውን ልብ መስበር፣ የሰውን ውድቀት ማበጃጀት፣ በሰው ስኬት መቅናት። ቲክ ያላደረግነው የክፋት ዓይነት አለ? አዝለነው እየዞርን የሆሊውድ ፊልም ውስጥ ሉሲፈርን መፈለግ አይከብድም? ልክ እኛ በድርጊታችን ያልተዛመድነው ያህል ሆሊውድ ሰይጣንን ሊያስለምደን የሰራው ፊልም ነው! አላላችሁም? ብታዩት ፊልሙ ላይ ሰይጣን ራሱ ደግ ሲሰራ ነው ፊልሙ ጀምሮ የሚያልቀው። ወላ ፍቅር ይይዘዋልኮ! ተውኣ! 🤣🤣🤣🤣🤣🤣 አንዳንዱንኮ የጥልቁ አለቃ ራሱ “bro ክፋት አበድረኝ እስኪ?” ምናምን የሚለው ነው በናታችሁ🙆🏻‍♀️🙆🏻‍♀️

የሆነ ቦታ ላይ ግን በድሮ የአባቶቻችን ማንነት መኮፈስ አቁመን እውነታውን መቀበል ያለብን አይመስላችሁም? አሁንም ሀገራችን ቅድስት ናት የሚለው ላይ ነን? ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ እና ቅዱስ አባትና እናቶች ላንተ ነፍስ ተጠያቂ አይደሉም! እስከማውቀው ድረስ ኢትዮጵያዊ ስለሆንክ መንግስተ ሰማያትን አትወርስም! ወላ እኔ እስከማውቀው ሀይማኖት አያድንም እምነት እንጂ! በጋራ አንፀድቅም! በጋራ አንኮነንም! ስራህ ያወጣሃል ስራዬ ያወጣኛል። ዝም ብለን እንደትውልድ ስራችንን ካየነው ደግሞ እመነኝ ለመንግስተ ሰማያት ወይም ለፈጣሪ የቀረበ አይደለም። የሉሲፈር ታላቅ ወንድም ቢያደርገን እንጂ!! (አሁን እኔ ግን የዚህ ትውልድ ነው ያ ትውልድ ነው የምባለው? 🙆🏻‍♀️🙆🏻‍♀️🙆🏻‍♀️🙆🏻‍♀️🤪🤪🤪)

እንደው እስኪ ጥያቄ ልጠይቃችሁ? 666 በሉት ጥልቁ ሴራ በሉት ሉሲፈር በሉት በፈለጋችሁ ስምና መደብ ጥሩት ምንድነው የሚመስላችሁ? የመጨረሻ ግቡስ ምንድነው? ምንድነው ድብቅ ሴራው? ምንድነው የሆነ ታላቅ መገለጥ ያገኛችሁ ይመስል የጥልቁ ሚስጥር ፣ ታላቁ ሴራ ምናምን እያላችሁ የምትቀነጣጠሱት? የሰጡዋችሁንማ ዝምብላችሁ አትጨልጡ። ይሄን የሚያህል አናት የሰጠን እንድንጠይቅ፣ እንድናስብበት አይደል እንዴ? ከጥንት ያልተነገረ እና በእምነት መፅሃፍት ያልተፃፈ የጥልቁ ሴራ ዛሬ የተገለጠ አለ?
1/ ባጠቃላይ በምድር ስትኖር ነፍስህን ለእግዜር ማደሪያ ከማድረግ ለክፋትና ለተንኮል ማደሪያ ማድረግ
2/ በመፅሃፍ ቅዱስ ለምታምኑ ነፍስን ከእግዚአብሄር ማስኮብለልና የራሱ ማድረግ። ከገነት ይልቅ ሲኦል ተመዝጋቢ ቁጥር መጨመር።
ከዚህ ሌላ እኔ የማላውቀው የጥልቁ አላማ ካለ enlighten me pls

እስኪ መጀመሪያ በውስጣችን ያለውን ክፋት እናሸንፍ። ያለዘር ያለቀለም ያለሀይማኖት ምርጫ ፈጣሪ ስለሰራው ሰውነት እንደሰው እናስብ! ሉሲፈርን ሉሲፈር ያደረገው ስራው እንጂ እሱም መልአክ ነበር በነገራችሁ ላይ! እኛንም ሰው የሚያደርገን ስራችን እንጂ ምግባራችን ሰው ሰው ካላለ ከሉሲፈር አንሻልም! «ልጄ ሆይ ሰው ሁን» ያለው ሰው መሆን ከስጋና ደም ከፍ ስለሚል ነው!!
አስራ ምናምን ዓመት ፌስቡክ ላይ ስፅፍ «ሜዬ ዛሬ የፃፍሽው ደስ ይላል። ጎበዝ!» ልትለኝ ያልተከሰትክ ፣ እንኳን ተወለድሽ ወይም እንኳን ደስ ያለሽ ልትለኝ ያልተከሰትክ ስለሉሲፈር ፃፍሽ ብለህ የጥልቁን ሴራ ለመተንተን ከፍ ዝቅ ልታደርገኝ ትከሰታለህ? እና ካንተ በላይ ጥልቅ ሴረኛ አለብኝ እኔ አሁን? 🤣🤣🤣🤣
አንዳንዶቻችሁ ደግሞ ነውር ነው ፊልሙ ስለምን እንደሆነ እንኳን ሳታውቁ እሪሪሪሪ አትበሉ። ሉሲፈር የሚል ስም ስላለው ብቻ ከሆነ መፅሃፍ ቅዱስ ላይም ብዙ ቦታ አጋንንት ስሙ ተፅፏል። እርግጥ ነው ራስህንና የእምነትህን ልክ ካላመንከው ባታየው ይመረጣል አልኩኝኮ!
ሰው ታስወራላችሁ ግን ኸረ በሰላም አውለኝ!!………🏃🏽‍♀️🏃🏽‍♀️🏃🏽‍♀️🏃🏽‍♀️🏃🏽‍♀️

አስተያየትዎን እዚህ ይስጡ

የኢሜል አድራሻዎ አይወጣም

Loading...