Tidarfelagi.com

የገደለ አባትሽ የሞተው ባልሽ (ክፍል አምስት)

በነገራችን ጎን እኔ ከነአካቴው ሲጋራ አጭሼ አላውቅም። አንድ አይናለም የምትባል የእማዬ ጓደኛ ናት ጭስና አክሱሜን አቋልፋው የሞተችው። ይኸው ከዚያ ወዲህ የምታጨስ ሴት፣ የሲጋራዋ ጭስ ሽታ፣ ጥቁር ዳንቴላም ስቶኪንግ፣ ወንድነት (ቀበቶ) ፣…….. ማላብ…… በነፍስም በስጋ ተዛምደውብኛል።

ምድረ አዳም ያለጭስ አክሱሙ አይሰራም ብለህ አትቦፍፍ። የምልህ እርቦህ ስፍስፍ ብለህ የድፎ ዳቦ ቁራሽ በክክ አልጫ ቢሰጡህ ትበላለህኮ…… ከዚያ ቀን በኋላ ክክ አልጫ አታሳዩኝ ብትል ነው።… አስበው እርቦህ ሆድህ ውስጥ የምትወረውረው… ሳታላምጥ የምትውጠው እህል ስትሻ… በቅልጥም ያበደ ፍትፍት ቢሰጡህ… (ነገሩ እንደምርጫህ ሊለይ ይችላል)… ትቀረጥፈዋለህ። እንደዛ ነው ነገሩ… ለልግጫ አትመቻች።

አይናለም? አይናለም እንኳን ሲጋራ የምታጨሰው? ይሏታል ማንነቷን ሲያስረዱ። የፀደይ እናት አይሏትም። ያቺ የካፒቴን ሞገስ ሚስት አይሏትም። ያቺ የሆነ የመንግስት ቢሮ ታይፒስቷ አይሏትም። ያቺ ሁሌ አመት—በዓል የምትመስለው አይሏትም። ያቺ በዓይኖቿ የምትስቀው አይሏትም። ያቺ ሰው እቤቷ በልቶ የሚጠግብ የማይመስላት ብለው ደግነቷን አይነግሩላትም። ያቺ በሰበብ አስባቡ እየደገሰች ጎረቤት የምትጠራው ብለው እቤቷ ለድግሶቿ መመላለሳቸው ውል አይላቸውም።…… አንድ እነሱ እንከን ነው ብለው ያመኑበት ጉድፈት አጊንተውላታል… ታጨሳለች… የስሟ ማዕረግ አድርገው ለጥፈውላታል። የሷን ምግባረ ብልሹነት ካላቆለጳጰሱ የእነርሱ ምግባረ ሰናይነት ሊኮሰምን ነዋ…… ነገሩ ሰውኛ ነውኮ። በጣሙን ደግሞ ሀበሽኛ……
ብዙ የሳምንቱን ቀናት ከስራ ሰዓት መልስ እኛ ቤት እየመጣች ከእማዬጋ ቡና እየጠጡ ይጫወታሉ። ከቢሮ በቀጥታ ስለምትመጣ ብዙውን ጊዜ በአጫጭር ጉርዶቿ እንደዘነጠች ነበር። የሆነ እለት እማዬ ለቅሶ ሄዳ መጣችና አለመኖርዋን እያወቀች አሮጌ ሶፋችን ላይ ዘና ብላ ተቀመጠች።

“ጎረምሳው? እስኪ የእናትህን ነጠላ ጫማ አቀብለኝ” አለችኝ።ለወትሮው “ጎረምሳው” የምባለው ከሰው ተደባድቤ ወደቤት የመጣሁ እለት ነበር። እድሜ ለአብርሽ እንኳን የእኔን የወንድሙን የሰፈሩን ጎረምሳ የድብድብ ወልፍ መድብሎ በየቀኑ እየተደባደበ የሚደባደቡትስ ሰው ከየት ይመጣል? ነጠላ ጫማውን ሰጥቻት ልወጣ ስል
“ወዴት ነው ጥድፊያው? ና እስኪ የጉርዴ ዚፕ ፓንቴን ነክሶብኛል አስለቅቅልኝ! “አለችኝ። ትዕዛዝ ነገር ይመስላል። የሆነ “እህህህ… “ብለው እያጉረመረሙ ግን እንቢ የማይሉት ትዕዛዝ… የእውነቷን ነው። ደማቅ ቢጫ አጭር ጉርድዋ የኋላ ዚፕ ጥቁር ፓንቷን ነክሶታል። አሁን ላይ ሳስበው ከላይ የለበሰችውን ልብስ አለማስታወሴ ይገርመኛል። አውቃ ነው ያስነከሰችው? አውቆ ዚፕ ማስነከስ ይቻላል እንዴ?
“ምን ያንቀጠቅጥሃል?…… ቀስ… ዚፑ እንዳይበላሽ የምወደው ቀሚሴ ነው።” አለችኝ። ተንቀጠቀጥኩ እንዴ እኔእንጃ ቶሎ መገላገል ፈለግኩ። ዚፑ ግን አልለቅ አለኝ።

“በሩን ዝጋው እስኪ ላውልቀውና ልሞክር “ያለችኝ በደንብ የገባኝ አልመሰለኝም። ደግሞም በሩን ከውጪ ሆኜ ይሁን ከውስጥ የምዘጋው አልገባኝም በሩ ጋር ደርሼ ልጠይቃት ዘወር ስል ጉርዷን ከነፓንቷ አውልቃዋለች። እስከወገቧ ድረስ የመሰለኝ ስቶኪንጓ ብቻ ጭኗ አጋማሽ ላይ ቀርቷል።
“ምን ይገትርሃል ዝጋውና ና አግዘኝ እንጂ? “ምኑን ነው የማግዛት? በጭንቅላቴ “አሮን ዓይንህን አታዝረክርክ! ” እላለሁ ያደረግኩት ግን ነገሮችዋ ላይ ዓይኔን ማዝረክረክ ነው። በሩን የድንብር ዘጋሁት። ሳቀችብኝ።

“ሃሃሃሃ ወየው ዓይናለም ሴት አታውቅም? ና እስኪ ወዲህ ሃሃሃሃ ” እህህህ 16 ዓመቴ ነውኮ ሴት አውቃለሁ። ራቁቷን ግን አላውቅም። ያውም ደግሞ ትልቅ ሴትዮ…… ያውም ትልቅ ብዙ ነገር ያላት…… ያውም የእማዬ ጓደኛ…… እሷ ግን ፋራ የሆንኩ ነገር አስመሰለችው። አለገጠች።
“እስኪ አውልቀው! ” አለችኝ እግሯን እየዘረጋችልኝ እግሯ ላይ የቀረው ስቶኪንጓ ብቻ ቢሆንም
“ምኑን? ” አልኳት። ይሄ ነገር ዚፕዋን ልናስለቅቅ አልነበር እንዴ?
“ሃሃሃሃ የምን መርበትበት ነው ወንድ ልጅ አይደለህ እንዴ? ነውስ ያንተ ወንድነት ለመደባደብ ግዜ ነው?” ወንድነቴንማ ይህችን የማትረባ ስቶኪንግ ባለማውለቄ አላስገምትም ብዬ ዘው
“ቀስ…… ቀስ …… የምትሄድበት አለህ? ቀስ…… እንደወንዶቹ ሁና ሃሃሃሃሃ” ይሄ ወንድነት እንዴት ነው ፈተናው በዛሳ? ቀስ ብላ ነገሮችዋን በሃላል እንዳይ አድርጋ ተቀመጠች። ሲጋራዋን ከቦርሳዋ አውጥታ ስትለኩስ አውልቅ በተባልኩበት የዝግታ ልክ የሁለቱንም እግሮቿን ስቶኪንግ አውልቅያለሁ። አንድ ስባ ጭሱን አየር ላይ እየለቀቀችው ፍቅረኛዋ ጥሏት በሚሄድ አይነት ስስት ጭሱን በአይኗ ትሸኘዋለች። የእኔ ጭሱን እያየሁ መባባት ምን ይሉት ነው? እሷ ናታ! የሆነ ፍቅር የምትሰራ ነገር ታስመስለዋለችኮ
“ሃሃሃሃ አንተ ልጅ ወንድ አይደለህ እንዴ? ቀበቶ አይደል የታጠቅከው? ምን አፍጣለህ? ታጨሳለህ? “እሰይ ይሄ ወንድነት ጉድ አፈላ
“አይይይ ኧረ እኔ አላጨስም።” አልኩ ማፍጠጤን ሳላቆም ።
እንዴ አዳምና ሄዋን የሚቀጥለውን እንድነግርህ እየጠበቅክ አይደለምኣ? ከዚህ በላይ ከነገርኩህኮ አብረን ተኛናት ማለትኮ ነው። ያው የወንድነት ጥያቄ ነው…… የቀበቶ ልክ ነው ጉዳዩ…… ወንድነቴን አሳየኋታ! አላመናችሁኝም መቼም! የዛን ቀንማ አይሆኑ ሆንኩ። ምን ማለቴ እንደሆነ የአዳም ዘር ገብቶሃል። የሄዋን ዘር ደግሞ ከአዳም ዘር ጠይቂ።
***** ******** ******* *****

እነዚህ ደግሞ ጭራሽ መጠባጠብ ይዘዋል። ሰርኬና አሚ ናቸዋ! እነርሱ ይሄን ጉንጭ አልፋ ፅብፀባቸውን እስኪያቂሙ ነበርኮ ዘመንን ተሳፍሬ መሸምጠጤ
“እናንተ ደግሞ ከውጭ የምትመጡ ሰዎች ችግራችሁ እዛ ከአንድ እጅ ጣት ያልበለጡ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና አቋም ባለበት ሃገር ሲባል የሰማችሁትን የፖለቲካ አቋም፣ ፅንፍ አንጃ ግራንጃ እዚህ ትዘረግፉታላችሁ። በውሃ ቧንቧ ቱቦ ኮብል እስቶን ካላፈሰስኩ ብሎ ድብድብ ነገር እኮ ነው። ስትኮርጁ ከሃገሪቷ ነባራዊ ሁናቴ አንፃር ለጆሮ እንኳን ብታመቻቹት ምናለ? መቶ ምናምን የፖለቲካ ፓርቲና በህዝቡ ቁጥር ልክ መቶ ምናምን ሚሊየን አቋም ባለበት ሀገር የምን ፅንፍ የምን አቋም ነው የምትቃዡት?” የኔዋ ናት ሰርኬ ላይ የምታፈጠው
“እንዴ ሰርኬ ከውጭ ነው እንዴ የመጣሽው? እንዴት አላውቅም? ” አልኩ ከምሬን ነው ለእኔ በሶስት ወር ያልተነገረኝን መቼ ነው ያወሩት?
“ሂድ ከዚህ ይሄ ደግሞ…… ” ቀጠለች ፅብፀባዋን ስላደናቀፍኳት ተበሳጭታ።
“ምግብ እየበላን ይሁን ይሄ ነገር ?” እላለሁ ሰሚ የለም እንጂ
****** ******** ******* ********

“ጎሽ ልጄ ሂድ እስኪ አይናለም እቃ ገዝቶልኝ ይምጣ ብላሃለች።” እየተባልኩ እቤትዋ እግርም እጅም እንትም አበዛሁ። ሲከራርም ባልዋ ከመርከቡ ወርዶ እቤቱ የሰነበተ ሰሞን ደሜን ያገነፍለው ጀመር። በአሳሳች ቀን ለአብርሽ ብነግረው “ሚስትህ” እያለ ከማብሸቁም ልቆ “ሼባውን እናጭሰውና ሆስፒታል ይተኛልህ እንዴ? ” ይለኛል ባልዋ መክረሙን ስነግረው።
“አሮን እስኪ ተቀመጥ! ” አለችኝ ከሁለት ዓመት በኋላ እቤትዋ ልክ እንደገባሁ። ላቤ ጠፍ ሳይል ተቀምጬ ስለማላውቅ ግር እያለኝ ተቀመጥኩ።
“አሁንኮ ትልቅ ሰው ሆንክ። ጩንቻህም ፈረጠመ። ደግሞ አማላይም ሆነሃል።” ነገሩ ግልብጥ ሆነብኝ። እንዲህ አውርታኝ አታውቅም። እንደልጅ ነው የምታወራኝ። ለወትሮው ሲያደርጉ አይቼ እንደማላውቀው “እንደወንዶቹ ” ነበር የምባለው።

“ከዚህ በኋላ ትክክለኛ ህይወት መኖር መጀመር አለብህ። መቼም የሆነ ቀን ይሄን ነገር እንደምናቆመው ታውቅ ነበር አይደል? ከኔ መልስ ትጠብቃለች። ” ዛሬ ለምንድነው እያባበለች የምታወራኝ? እንደአለቃ የሚሰራራት ነገሯ የት ሄደ? ሁለት ዓመት እሷ ታዛለች……… የተባልኩትን አደርጋለሁ…… “ወንድ ወቶሃል” ትላለች ቁና ቁና እየተፈሰች……… የቀበቶ ልክ ተከብሯል ማለት ነው ወደእቤቴ ዳንስ እየቃጣኝ እመለሳለሁ።
“እኔ እንጃ አስቤበት አላውቅም።” እያልኳት ሲከፋኝ ታወቀኝ። አታደርገውም አሮን!
“ይሄን ነገር ማቆም አለብን። በቃ። ከዛሬ በኋላ በሌላ ምክንያት ካልሆነ በቀር በዚህ ሰበብ አትመጣም። ወጣት ነህ። እንደወጣት እኩያህን ጠብሰህ……… ” ለምንድነው ዛሬ ላይ “ይሄ ነገር” የምትለው? በግልቡ አልነበር የምትነግረኝ ሌላ ጊዜ? ጥያቄ አልጠየቅኩም። ከሷ ጋር ተጠያይቀን አናውቅማ! መልስም አልመለስኩም። ተነስቼ ወጣሁ። ልቤን ቋጥኝ የተጫነበት ያህል ከበደኝ።

“አንተ ነቅለህላታል እንዴ? ይለኛል አብርሽ አኳኋኔ አልመስጥ ብሎት። ” እህህ እኔኮ ጉድጉዱ ብቻ አስምጦህ መስሎኛል። አሮጊቷንም ነው እንዴ ?”
“በቃ ሂድና ትንሽ ጊዜ ስጭኝ…… ምናምን… እስኪወጣልኝ አንጎዳጉጂኝ ምናምን… በላታ። ” ያለግጣል። አልሳቅኩለትም። ብቻውን ይገለፍጣል። ተነስቼ ወደቤቷ በሩጫ ረገጥኩ።

“አንተ የምር አደረግከው እንዴ? ” የአብርሽ ድምፅ ከጀርባዬ አጀበኝ። በሩን ከፍቼ ስገባ ደርቄ ቀረሁ።

የገደለ አባትሽ የሞተው ባልሽ (ክፍል ስድስት)

 

አስተያየትዎን እዚህ ይስጡ

የኢሜል አድራሻዎ አይወጣም

Loading...