Tidarfelagi.com

የአፍሪካ የቁም ቅዠት

የአፍሪካ የቁም ቅዠት – የኡጋንዳ አምባገነን መሪ ስለ የነበረው ኢዲ አሚን ዳዳ | Idi Amin Dada – እነሆ መቆያ! 

3 Comments

 • longlive-ma@hotmail.co.uk'
  amsal commented on October 18, 2017 Reply

  [Link deleted]

  • longlive-ma@hotmail.co.uk'
   amsal commented on October 18, 2017 Reply

   ኢዲ አሚን ዳዳ.. — የአፍሪካ አምባገነኖች ፈር-ቀዳጅ!!
   ድፍን አፍሪካን ከጫፍ ጫፍ ብታስስ እንደ ኢዲ አሚን ዳዳ አስቂኝ ሰው አታገኝም እኮ፡፡ አስቂኝ ስልህ እኮ ኮሜዲያን ሆኖ አይደለም፡፡ ይበልጥ ወደ አውሬነቱ የተጠጋ አረመኔ ፍጡር ነው፡፡ እጅግ የሚያስፈራ፡፡ ግን ድርጊቱ፣ ንግግሩ፣ ነገረ-ሥራው ሁሉ… በቃ ከሰው አገኘዋለሁ ብለህ ስለማትጠብቀው.. ሳትወድ ያስቅሃል!! ያሳፍርሃልም፡፡ ኢዲ አሚን በ1969 እ.ኤ.አ. መፈንቅለ-መንግሥት አካሂዶ ወደስልጣን ከመውጣቱ በፊት ለተከታታይ 5 ዓመታት የኡጋንዳን የከባድ ሚዛን ቦክስ ቀበቶ ያነሣ – ተወዳዳሪ ያልተገኘለት የጦሩ የቦክስ ሻምፒዮና ነበር፡፡
   እንዲህ መሪ ሊሆን ነው ያላለ – በቃ ለተጠየቀው ሁሉ – ለምሳሌ የአንዱን ሃገር ሽማግሌ ልዑል – እኔ ብሆን ኖሮ የቀሩትን ጥርሶቹን በቦክስ ነበር የማረግፈው – ወዘተ ሲል፣ ከታወቁ ሰዎች ጋር ቦክስ እየሰነዘረ ፎቶ ሲነሳ – ምን ሲል – ሰዉ በኮሚክነቱ ወዶት ነበር፡፡ ወይ ኮሚክ እቴ!!! ለካ ደንበኛ ያልተገራውን ኮርማ ኖሯል እዝጌሩ ባልጠረጠሩት ኡጋንዳውያን ላይ እንደ መቅሰፍት አርጎ የላከባቸው??!! — ሌላ ሌላውን ትተን — ኢዲ አሚን ዳዳ — የሱ አባል የነበረበትን የጦሩን ክፍል — ከሥልጣን ላስወገዳቸው – ለሚልተን ኦቦቴ — ታማኝ ናቸው ብሎ በመጠርጠር ብቻ — በዚያን ጊዜ ቁጥራቸው 9,000 ከነበሩት የሩዋንዳ መደበኛ ጦር — 6,000 የሚሆኑትን የገዛ ጓደኞቹን ሣይቀር — ሥልጣን በፈነቀለ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ እምሽክ አርጎ ነው የፈጃቸው!!!!
   ጦሩን ካሸማቀቀ በኋላ… በፌብሩዋሪ 2/ 1971 ራሱን በራሱ — የኡጋንዳ ባለሙሉ ሥልጣን ፕሬዚዳንት በማለት ሥልጣኑን በብቸኝነት ጨበጠ፡፡ በመጨረሻም.. አብረነው አንሰበሰብም፣ አንድ ጠረጴዛ ላይ አንቀመጥም፣ ይሄማ ሰው-በላ አውሬ ነው፣ ሕዝቡን አይወክልም ብለው ባወገዙት አፍሪካውያን የነፃነት መሪዎች.. በእነ ጃንሆይ፣ በእነ ጆሞ ኬንያታ፣ እና በተለይም በኔሬሬ ጥረት.. በነጨረሻ በአፕሪል 11/ 1979 —በታንዛኒያ ወታደሮች እገዛ ከሥልጣኑ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተመነገለ፡፡ በእነዚህ 8 ዓመት አረመኔ የሥልጣን ዓመታት ውስጥ በወቅቱ ከነበሩት 12 ሚሊዮን ዩጋንዳውያን መካከል — ኢዲ አሚን 500 ሺህውን ሕዝብ በርሸና እንደፈጀው የአምንስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርት አስፍሮለታል፡፡ የተባበሩት መንግስታት ዓለማቀፉ የፍትህ ችሎት (አይ ሲ ጄ) ሪፖርት በበኩሉ — በእርግጠኝነት በኢዲ አሚን በቀጥታ ነፍሳቸው እንዲጠፋ የተደረጉት ኡጋንዳውያን ሟቾች ቁጥር እስከ 300 ሺህ እንደሚጠጋ ያሳያል፡፡ ይሄ ማለት እኮ በቃ ኢዲ አሚን ሥራዬ ብሎ በየዓመቱ – ቢያንስ ከ40 ሺህ እስከ 50 ሺህ ኡጋንዳውያንን – በየዓመቱ እየፈጀ ነው የተቀመጠው ማለት እኮ ነው!!!! ጉድ ጉድ ጉድ ማለት ነው እንጂ – ይሄ ሰው እኮ ጤነኛ ነው ማለትም ይቸግራል፡፡ በእርግጥ እንዲያም የሚሉ ነበሩ፡፡ እርሱስ መች ሊክድ?
   እርሱ በተወለደባት የኡጋንዳ ግዛት በኮቦኮ አካባቢ – የሆነ የጥንቆላ አምልኮ የሚከተሉ ነዋሪዎች – በወቅቱ ለገድ እያሉ የሰውን – በተለይ የጠላታቸውን ልብ ከነህይወቱ ፈልቅቀው በማውጣት – ይመገቡታል – እየተባለ ይነገር ነበር፡፡ እና አንዴ ኢዲ አሚንን አንተ የሰው ሥጋ ትበላለህ ይባላል እና ምን ትላለህ?? ሲሉት ‹‹ — አዎ እውነት ነው፡፡ የሰው ሥጋ አልቀመስኩም ብል ዋሾ ያሰኘኛል፡፡ አዎ ቀምሼያለሁ፡፡ ግን ለኔ አልሆነኝም፡፡ ስላልተስማማኝ ትቼዋለሁ፡፡ ብትቀምሰው – በጣም ጨው የበዛበት ነው – አይመችም!!!›› ብሎ ነውኮ የመለሰው፡፡ ነገሩ እውነት ያልመሰለው – የምዕራቡ ሚዲያ ግን እያሽካካ – እያውካካ – ይዘግብለት ነበር፡፡ ኋላ ነው ጭንቅላታቸውን በኡኡታ የያዙት – የኢዲ አሚን ዳዳ ጉድ ሲፍረጠረጥ!!!!
   ኢዲ አሚን እኮ በአደባባይ ‹‹ሒትለር ለእኔ ጀግና ሮል ሞዴሌ ነው! አደንቀዋለሁ! ደመ-መራራ ነው! ወኔ አለው! ላመነበት ዓላማ ማንንም ያጠፋል! ያ ደግሞ ለሃገሩ የግድ አስፈላጊ ስለነበረ ነው!! እና ሂትለርን ከልቤ አደንቀዋለሁ!!›› ብሎ የተናገረ ሰው ነው፡፡ እና በዚህ የተነሳ ምዕራቡ ዓለም፡- ‹‹ዳግማዊው ሒትለር በአፍሪካ›› እያሉ በፊት ገጻቸው ያወጡት ነበረ፡፡ ‹‹የአፍሪካው የዱር አውሬ!›› ብለውም ያወጡት ነበረ፡፡ አንዳንዶቹ በመልኩና በተክለቁመናው ነው – አፍሪካውያንን እየተሳደቡ ነው – ብለው ቅር ቢሰኙም – ሌሎቹ ግን ያ ያንስበታል – የዱር አውሬ እኮ ለመደሰት ሲል ሰውን አይገድልም፣ አያሰቃይም – ሲርበው ለመብላት ነው – ኢዲ አሚን ግን ለእርካታ ሲል – ወይ ሲወልፈው – ሰው አርዶ ደሙን ሊመጥ ይችላል – ያውም ውሃ ቀጠነ – ወይ ጠረጠርኩት ብሎ!!! ‹‹አያድርስ የሆነ የአፍሪካ ማፈሪያ!!›› ነበር እንጂ ይሄማ – ይላሉ ሌሎች ደግሞ፡፡
   /በነገራችን ላይ የኡጋንዳ የአቪዬሽን ሚኒስትር የነበሩ አንድ ሰው – በኢዲ አሚን ተጠርጥረው ከኢንቴቤ ከቤተመንግስቱ አቅራቢያ ባለ ምድር ቤት ውስጥ ስላዩት ስቃይ እና እንዴት እንዳመለጡ – በኋላ ኢዲ አሚን እያለ ኬንያ ገብተው እጅ ከሰጡ በኋላ የጻፉት እውነተኛ ታሪክ መጽሐፍ አለ – እጅግ የሚያሰቅቅ አውሬነቱን የሚገልጽ – ሰውየውም በህይወት አሉ መሠለኝ – እስከቅርብ ጊዜ – በኢዲ አሚን ተጠርጥረው በህይወት የተረፉ ብቸኛ ባለሥልጣን ሁሉ እየተባሉ ይጠሩ ነበር እኚህ እድለኛ ሰው፡፡/
   እስቲ ለጊዜው ኢዲ አሚን ዳዳ ከሚታወቅባቸው አስገራሚ አባባሎችና ነገሮች ጠቅሰን እንለይ፡-
   1. ኢዲአሚን ፊት የቀረበ ሰው ሁሉ፤ ማንም ይሁን ማን የሚከተለውን ረዥም ማዕረግ መጥራት ነበረበት፡፡ ማዕረጉን ራሱ ለራሱ ነው የሰጠው፡፡ የምድሪቱ ብቻ ሳይሆን፣ የባህር አሶች፣ የሰማይ ወፎች፣ የፍጡራን ሁሉ ገዢ የሚል ሁሉ ነበረበት፡- “His Excellency President for Life, Field Marshal Al Hadji Doctor Idi Amin, VC, DSO, MC, Lord of All the Beasts of the Earth and Fishes of the Sea, and Conqueror of the British Empire in Africa in General and Uganda in Particular.” ይህቺን ያጓደለ የእጁን ያገኝ ነበረ!!!
   2. ኢዲ አሚን በሃገሩ ስላለው የመናገር ነፃነት ሲጠየቅ፡- ‹‹አዎ በዚህ ሃገር የመናገር ነፃነት አለህ፤ ሆኖም ግን ከተናገርክ በኋላ ስለሚከተልህ ነገር ግን በበኩሌ ማረጋገጫ ልሰጥህ አልችልም››
   3. ሁሌ ኢዲ አሚን የሚጠቀስበት ትልቅ አባባል አለ፡፡ እንዲህ የሚል፡- ‹‹ከተተኮሰ ጥይት ፈጥኖ ሊሮጥ የሚችል ማንም የለም!››
   4. አንዴ ግን ስለራሱ እና እርሱን ፈርተው ከስልጣን ስለወረዱ ሰዎች ሲጠየቅ፡- ‹‹ያለብኝ ችግር ምን መሰለህ? እኔ መፈጠር ከነበረብኝ ሃምሳ ዓመት ወይም መቶ ዓመት ቀድሜ የተወለድኩ ሰው ነኝ፡፡ ፍጥነቴንም እንደዚያው ሌሎች ሊደርሱበት ይከብዳቸዋል፡፡ ለዚህ ነው ጥቂት ሚኒስትሮቼ ከመንግስቴ ስልጣን ሊወርዱ የቻሉት፡፡ ምክንያቱም ከፍጥነቴ ጋር አብረው ሊሄዱ አይችሉማ!››
   5. አንዴ ደግሞ ለምን ሰዎችን እንደሚገድል ሲጠየቅ፡- ‹‹እንዴ! ምን ነክቶሃል? በማንኛውም ሃገር እኮ በቃ መሞት ያለባቸው ሕዝቦች አሉ፡፡ አይደለም እንዴ? እነዚያ ሰዎች ሁልጊዜም አንድ ሃገር ህግና ስርዓትን ለማስፈን እንዲቻላት ጭዳ ሆነው መስዋዕት መሆን ያለባቸው ሰዎች ናቸው!››
   6. አንዴ ደግሞ ፖለቲካ ለእርሱ ምን እንደሆነ ሲጠየቅ ኢዲ አሚን የተናገረው፡- ‹‹ፖለቲካ ማለት ለእኔ ልክ እንደ ቦክስ ውድድር ነው፡፡ በቃ ተቃዋሚዎችህን በተቻለህ ዙሮች ትዘርራቸዋለህ!!!››
   7. አንዴ ደግሞ ቶማስ ኤንድ ማርጋሬት ለተባለው መጽሔት በ77 ዓ.ም. ቃለምልልስ ሲሰጥ በምዕራባውያን የሚደረግበትን ተፅዕኖ የማይቀበልበትን ምክንያት እንዲህ ሲል ነበረ ያስረዳው፡- ‹‹አያችሁ እኔ በማንም ኃያል የሆነ ኃይል ቁጥጥር ሥር መዋል አልፈልግም፡፡ ለምንድነው? ካላችሁኝ – ምክንያቱ ግልጽ ነው፡፡ እኔ ራሴ በዚህ ዓለም ላይ ከሁሉም የበለጠ ኃይል ያለኝ ሰው ነኝ – ወይም ራሴን የምቆጥረው እንደዚያ አድርጌ ነው፡፡ እና ራሴ እንደዚያ ስለሆንኩ እንዴት ብዬ ሌሎች ሃያላን እኔን እንዲቆጣጠሩኝ እፈቅድላቸዋለሁ?››
   8. በሃገሩ ለምን ሕዝባዊ ምርጫ እንደማያካሂድ፣ ለምን በዲሞክራሲ የሚመራ መንግስት እንደማያቋቁም ሲጠየቅስ? ፡- ‹‹የእኔ ሥልጣን ላይ መውጣት አንዱና ብቸኛው ዓላማ.. ሃገሪቱን ከፊት ለፊት እየመራሁ ከተዘፈቀችበት ዘግናኝ የሆነ ሙሰኝነት፣ መከራ እና ባርነት ማውጣት ነው፡፡ እና ምንም የማልሸሽገው ነገር… ሃገሪቱን አንዴ ከእነዚህ እኩይ ነገሮች ነፃ ካወጣኋት በኋላ ያለጥርጥር በእውነተኛ ዲሞክራሲያዊ መርሆዎች የሚመራ የሲቪል መንግስት እንዲቋቋም ሕዝባዊ ምርጫ አደራጅቼ መተግበሩንም በበላይነት እንደምቆጣጠር – ይሄን ላረጋግጥልህ እወዳለሁ – አንድ ቀን አረገዋለሁ – ግን አሁን ጊዜው አይደለም፡፡››
   9. አንዴ የ1973ቱ የኒውስዊክ መጽሔት ባደረገለት ቃለምልልስ አንተ ለአፍሪካ ምንድነኝ ትላለህ? ምንድነው ለአፍሪካውያን አንተ የምታስተጋባው ተምሳሌት? ተብሎ ለቀረበለት ጥያቄ ሲመልስ፡- ‹‹እኔ የአፍሪካ ታላቁ ጀግና ነኝ! ያ ነው ተምሣሌትነቴ!››
   10. በስተመጨረሻው ግድም ኢዲ አሚን ደመመራርነቱ እያየለበት መጣ፡፡ አስፈሪነቱንም መደበቅ አልቻለም፡፡ እና ዲፕሎማቶችን ሳይቀር ማሰር፣ ማጎር፣ እና በየታሰሩበት እየሄደ እንዲፈሩት የሰው ስጋ ነክሶ ማኘክ.. ወዘተ ነገር ስራዎችን ማሳየት ሁሉ ጀመረ፡፡ አንዴ ባርቤት ሽሮደር የተሰኘ የፈረንሣይ የፊልም ሰሪ ኢዲ አሚንን እንዲቀርጽና ዶኪመንተሪ እንዲሰራ ፈቀደለት፡፡ ከዚያ ፊልሙን ሰራ፡፡ በስምምነታቸው መሰረት ኢዲ አሚን ያፀደቀው ፊልም በሃገር ውስጥ ሊታይ፤ ሳንሱር ያልተደረገበት ደግሞ በውጨው አለም ሊታይ ሆነ፡፡ በሃገር ውስጥ የታየውን ፊልም ለተከታታይ እያየ ኢዲ አሚን ትልቅ ድግስ ደግሶ ባለስልጣኖቹን እየጋበዘ ከፊልሙ ጋር ሰርግ ደግሶ ከረመ፡፡ ደግሞ በስምምነታቸው መሰረት፡- ዳይሬክተሩ ኢዲ አሚን ተብሎ ተጠቅሶለታል፡፡ ቀራጩ ባመዛኙ ኢዲ አሚን፡፡ ተዋናዩ ኢዲ አሚን፤ አርታዒው ኢዲ አሚን፡፡ እና የሽሮደር ተንኮል የፊልሙን ርዕስ፡- ‹‹ጄነራል ኢዲ አሚን ዳዳ – የራስ ምስል›› ነበር ያለው – ሰልፍ ፖርትሬት!!! ግን ጉድ የፈላው በፓሪስ ፈረንሳይ የሚታየው ፊልሙ ቀን ሲደርስ ነበር፡፡ ኢዲ አሚን ሙሉ ወጪያቸውን ችሎ 6 ከፍተኛ ኮሚሽነሮችን ላከ፤ ሙሉውን ፊልም አይተው ሙሉ ማስታወሻ ይዘው ተመልሰው በአካል ሪፖርት እንዲያደርጉለት!!! አይተው መጡ፡፡ ብዙ ቦታ ላይ በፊልሙ አስቂኙ የኢዲ አሚን ስብዕና በግልፅ ይታይ ነበረ፡፡ እና ኢዲ አሚን ባርቤት ሽሮደርን በተደጋጋሚ አስፈራራ፤ ቀይረህ አሳይ አለው፤ የተዘገቡለትን አባባሎች ሰርዝ አለው፡፡ ሽሮደር ደግሞ – አንዴ ከኡጋንዳ በሰላም ወጥቶ የለ? – ገደል ግባ አለው!! ከዚያ ኢዲ አሚን በቀጥታ ለጄነራሉ ትዕዛዝ ሰጠ – በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ ኡጋንዳ ውስጥ የሚገኙትን ፈረንሳውያን ሁሉ ሰብስበህ ባንድ ከርቸሌ አጉርልኝ!!! ታጎሩ፡፡ ከዚያ ለሁሉም እስረኞች የሽሮደር ስልክ ቁጥር ተሰጣቸው – ሁለት መቶዎቹም እየደወሉ ዳይሬክተሩን ሽሮደርን ለመኑት፡፡ እላያቸው ላይ ሽጉጥ ተደቅኖባቸው ነው እንግዲህ የሚለምኑት፡፡ በመጨረሻ ሽሮደር ተስማማ፡፡ እና ቀየረለት፡፡ ኢዲ አሚንም እስረኞቹን ፈታ!!!
   11. በነገራችን ላይ ማናቸውም ከውጭ የነጮች ሃገር የተሾመ ዲፕሎማት ከመጣ.. በሚዘጋጅላቸው ፕሮግራም ላይ ደረቅ የሳር ሜዳ ላይ ተንበርክከው – ኢዲ አሚንን በሙሉ ማዕረጋቸው እየጠሩ የሹመት ደብዳቤያቸውን ጮክ ብለው ማንበብ እና ለኢዲ አሚን ያላቸውን ታማኝነትና ክብር በተመለከተ ቃለመሃላ መግባት ነበረባቸው – ያለዚያ ኢዲ አሚን – በመጣህበት እግሩ ከሃገሩ ያበርርሃልና፡፡
   12. በመጨረሻ በነሃሴ 16 ቀን 2003 እ.አ.አ. – ነፍሱ ልትወጣ በተቃረበባት – በሳዑዲ አረቢያ ጂዳ በሆስፒታል እንደተኛ – ኢዲ አሚን አንድ ጥያቄ ተጠየቀ፡፡ ለመሆኑ አንተን ዓለም.. እና ኡጋንዳውያን ሁልጊዜ አንተን በምን መልኩ ቢያስቡኝ… እኔን ይገልጸኛል ብለህ የምታስበው? ወይ የምትመርጠው?? ተብሎ ተጠየቀ፡፡ ምን ብሎ ቢመልስ ጥሩ ነው?? ፡- ‹‹እኔ ሁልጊዜም መታወስ የምፈልገው በታላቅ አትሌትነቴ ነው — በሁልጊዜም የቦክስ ሻምፒዮናነቴ!!›› / ‹‹I want to be remembered as a great athlete. As a boxing champion.››/
   አበቃሁ፡፡
   written by: Assaf hailu

  ከአሳፍ ሀይሉ የፌቡ ገፅ የተሰረቀ ☺

አስተያየትዎን እዚህ ይስጡ

የኢሜል አድራሻዎ አይወጣም

Loading...