Tidarfelagi.com

ውይ መፅሐፍ ቅዱስ…

1. “ወደ እኔ የሚመጣ ሊከተለኝም የሚወድአባቱንና እናቱን፣ ሚስቱን እና ልጆቹን፣ወንድሞቹንና እህቶቹን፣ የራሱንም ሰውነት እንኳ ቢሆን የማይጠላ ደቀመዝሙሬ ሊሆን አይችልም” ሉቃ. 13፣33

እንደው ይቅርታ አድግልኝና እየሱስ፣ እንኳን እናትና አባቴን አሁን ታይፕ የማደርገውን ፅሁፍ እንኳ ትቼ ልከተለህ አልችልም፡፡ ካንተ በፊት እናትና አባቴን… ቤተሰቤን ነው የማውቀው፡፡ እና እናቴን ትቼ? አባቴን ትቼ? … ስንቱን ትተን ስንቱን እንከተል አንተስ ስታስበው? እና ይለፈኝ! አልከተልህም፤ አትከተለኝ፡፡

 1. ማቴዎስ 16፣18 ላይ “እውነት እላችኋለሁ፣ የሰው ልጅ በመንግስቱ ሲመጣ እስኪያዩት ድረስ እዚህ ቆመው ካሉት ሞትን የማይቀበሉ አሉ” ይላል እየሱስ፡፡ ይሄው ስንት ዘመኑ እስካሁን አልተመለሰም፡፡ሞትን የማይቀበሉ አሉ የተባሉትም ሞተው አለቁ፡፡ ውይይ… ምን ገጥሞት ይሀን? በርግጥ እንዲህ አይነት ነገር መፃፍ ብዙዎችን እንደሚያናድድ ይገባኛል፡፡ ግን እኮ እመጣለሁ ብሎ ቀልጦ መቅረትም ይበልጥ ያናዳል፡፡
 2. ዘፍጥረት አዳም ሄዋንን አወቃት… እንትና እንትናን አወቃት እያለ ይነግረናል፡፡ ጥያቄ፤ ሄዋን አዳም ሲያውቃት እሷ አዳምን አታውቀውም ወይ? ነው በፀሐፊዎቹ እይታ ወሲብ የወንድ ብቻ ነው፡፡ ወንድ አዋቂ፣ ሴት ታዋቂ?
 3. ወዲያ ማቴዎስ ላይ ደግሞ፣ ሳባቱን እንጀራ እና ጥቂት አሳ በልተው ከጨረሱ በኋላ እንዲህ የሚል ቃል አለ፤
  …የበሉት “ሰዎችም” ከሴቶችና እና ከወንዶች በቀር አራት ሺህ ነበሩ” ብሎን እርፍ ይላል፡፡ ሴቶች እና ልጆች ሰዎች አይደሉም ወይ? እንዴት ነው ነገሩ፣ “ምናምኑን ቆጥረውት እንጂ እኛ አምስት መቶም አንሞላ እንደተባለው ሆነብን እኮ

ወይይ መጥሐፍ ቅዱስ… እንዘልቀዋለን እስቲ

 

**************************************** ክፍል ሁለት ***************************************

ውይይ መፅሐፍ ቅዱስ/ እይይ ቁርዓን…
( እንደ ክፍል – 2 ነገር)

በቁራን ልጀምር፡፡ በመሰረቱ ስለ ቁራን የማወራው የለኝም፡፡ ምክንያቱም ለኔ ቁርዓን ከመፅሀፍ ቅዱስ ላየ ተፈለፈሎ የተበተነ ጥሬ ነው፡፡ መፅሐፍ ቅዱስ በሶስተኛው ክ/ዘ ሲፃፍ፣ ቁራን በሰባተኛው ክ/ዘ ተፃፈ፡፡ ምንም እንኳን መሰረቱን መፅሐፍ ቅዱስ ላይ ቢያደርግም፣ በራሱ የጨመራቸው ክፍሎች እንዳሉ ግን አይካድም( የኛው ቢላልም በመፅሐፉ ላይ ድርሻ እንዳለው ይነገራል) የመፅሐፍ ቅዱስን ክፍል እነ መሐመድ( ኢብን አል አራቢ?) በሚመቻቸው መልኩ ጨመርመር አድርገው ፃፉት፣ መፅሐፍ ቅዱስ ላይ ያሉ አንዳንድ ታሪኮችን ሰፋ እና ለወጥ አደረጓቸው፡፡

‘‘ቁርዓን በሶሪያዎች እና አይሁዶች ተጠናቅሮ የተፃፈው (1870-1919 ዓ.ም) ከብሉይ ኪዳን፣ ከአዲስ ኪዳን፣ ከጁዲስም ሥነ መለኮቶችና ርዕዮቶች ሲሆን በኋላም ልዩ ልዩ ማሻሻያዎች በሙሐመዳኒስም ብሎ፣ በእስላም ነቢያት ታክሎበት ተፅፏል፡፡’’ (የክርስትና እና የእስልምና ሥነ-መለኮቶች አመሰራረት፣ 113 – ተርጓሚው እንዳለ ገብረሕይወት)
ባለኝ ግንዛቤ ይህንን ሃሳብ የሚንድ ነገር እስካሁን አላገኘሁም፡፡ ስለዚህ ቁርዓንን እንለፈው፡፡

እጓለ ገ/ዩሐንስ የከፍተኛ ትምህርት ዘይቤ በተባለ መፅሐፋቸው ስለ መፅሐፍ ቅዱስ ትዝብታቸውን እንዲህ ብለው ያስቀምጣሉ፤
‘‘ ትምህርት ወይም እውቀት የሚባል ነገር ሕሊና በገዛ ራሱ ሕግጋት እየተመራ በመመርመር የሚገኝ መሆኑ ቀርቶ አንዲት መጥሐፍ በመተርጎም የሚገኝ ሆነ’’ (ገፅ-57)
እጓለ በመካከለኛው ዘመን ስለነበረው ሁኔታ ነው የሚያወሩት፡፡ ዛሬም ግን እንዲያው ነው፡፡ ዓለምን በመፅሐፍ ቅዱስ ዓይን ማየት ባልከፋ፣ ግን መፅሐፉ ከዘመኑ ጋር መራመድ ይችላል ወይ? መልሱ ምንም ሊሆን ይችላል፣ ግን እስቲ አብረን እንጠይቅ…

ሴቶችን እንደሁለተኛ ፍጡር የሚቆጥረው መፅሐፍ!..
****
የመፅሐፍ ቅዱስ ፀሐፊዎች ሴቶች ምን እንዳደረጓቸው እንጃ አያስተርፏቸውም፡፡ ከሰው ቁጥር አያስገቧቸውም፡፡ ከክርስቶስ አስራ ሁለቱ ተከታዮች ውስጥ አንድም ሴት የለችም፡፡ ክርስቶስ ወንድ ነው፡፡ በተደጋጋሚም የሰማዩ አባቴ እያለ ሲናገር እንሰማዋለን፡፡ አባትነት ከፍ ያለ ዋጋ ተሰጥቶታል ማለት ነው፡፡ ሴት አባት የለችም መቼስ…
የአባቶቻችሁን እምነት ጠብቁ ይላል… የእናቶችስ? እናቶች እምነት የላቸውም ወይስ የማመን ንቃተ ሕሊና ላይ አልደረሱም?
እንደ መፅሐፉ ሴት ለረዳትነት ፍጥረት ውስጥ የተሻጠች እንጂ እራሷን ችላ የተፈጠረች አይደለችም፡፡ ‘‘ ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም፤የሚረዳውን ጓደኛ እንፍጠርለት እንጂ’’ ብሎ ነው የፈጠራት፡፡ ስለዚህም የሴት መፈጠር ለረዳትነት ብቻ ነው፡፡ ሴቶች እስቲ በዚህ መፅሐፍ ካመናችሁ በሉ ወንዶችን በመርዳት ብቻ ኑሩ? ከአዳም አጥንት ተወስዳ መፈጠሯም ሌላው አስቂኝ ነገር ነው፡፡ ዓላማው ምንድን ነው? አዳምን በተለየ ቅርፅ ማብዛት? ወንድ ከራሱ አልፎ ለሴትም መሰረት እንደሆነ ማሳየት?

በመፅሐፉ ሰፊውን የጀብዱ ስራ የሚሰሩት ወንዶች ናቸው፡፡ ስለ ኖሕ እንጂ ስለ ኖህ ሚስት ምን ያህልተነግሮናል? ሔዋን አሳች ተሳሳች ናት ተብለናል፡፡ የሎጥ ሚስት የጨው አምድ ሆና ስትቀር አይተናል- ሎጥ ግን ጠንካራ ተደርጎ ተስሏል፡፡ (ዞራ የጨው አምድ ሆነች የሚለው እራሱ አዝናኝ ቢሆንም)

በእስራኤላውያን ፍቅር ያበደው መፅሐፍ!

ምኒሊክን ዘረኛ ነው ለማለት የደፈሩ የታሪክ አርታኢኣን ፣ እንዴት የከፋው ዘረኝነት አልታየቸውም እዚህ?
አዎ መፅሐፍ ቅዱስ እስራኤላውያንን እንደተለየ ዘር ነው የሚያቸው ወይም መፅሀፉን እራሳቸውን የተለዪ ዘሮች አድርገው ለማሳየት ተጠቅመውበታል(ነውም)
ሉቃስ 13፣33 ላይ ‘‘… ነቢይ በእየሩሳሌም ሊሞት አይገባውምና..’’ ይለናል፡፡ ለምን? እስራኤል ምንድን ናት? ሌላው ምንድን ነው?
የክርስቶስ ዘር ከእስራኤላውያን ይመዘዛል፡፡ በዘሩ እስራኤልን እንጂ ቀሪውን ዓለም አይወክልም ማለት ነው( ለነገሩ በዘሩ ብቻ ሳይሆን በግብሩም አይወክልም)

ዘዳግም 14፣12 እንዲህ ብሎ ሆሆይ ያስብለናል፤
‘‘የበከተውን ሁሉ አትብሉ፤ ይበላው ዘንድ በሀገርህ ዘንድ ለተቀመጠ መፃተኛ ወይም ለባዕድ* ስጠው፤ አንተ ለአምላክ ለእግዚኣብሔር የተቀደስክ ሕዝብ ነህና’’
ምን ማለት ነው? ሌሎች የበከተውን ይብሉ የሚል ምን ዓይነት ዘረኛ አምላክ ነው? ለእግዚሐብሔር የተቀደስክ ሕዝብ ነህ ማለትስ ምን ማለት ነው? -ሌላው የተረገመ ነው ማለት ነው??? አስቂኝ ኦኮ ነው፡፡ በሰው አምላክ ገብተን አበሳችንን ማየት!

ማቴ 10፣5 ላይም ይህ ተፅፏል፤
‘‘ በአህዛብ መንገድ አትሂዱ፣ ወደ ሳምራዊያን ከተማም አትግቡ፡፡ ነገር ግን <ከእስራኤል ወገን> ወደ ጠፉ በጎች ሂዱ፡፡ ሄዳችሁም መንግስተ ሰማያት ቀርባለች እያላችሁ አስተምሩ፡፡’’ ይሄ እንግዲህ እየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ለስብከት ዘመቻ ሲያሰማራ የተናገረው ነው፡፡ እዚህ ቃል ውስጥ አጭር መልስ አለ፤ እየሱስሰ የመጣው ለእስራኤላውያን እንጂ ለሌላው ዓለም አይደለም ( የፈለገ ያመጡትም እስራኤላውያን ናቸው ብሎ ማከልም ይችላል)

አንድ እንድገምለት፡፡ በዚሁ በማቲዎስ ክፍል ላይ አንዲት ‘‘ከነዓናዊት ሴት’’ ክርሰድቶስን እየተከተለችው ልጇን እንዲያድንላት ትማጠነዋለች፡፡ እሱ ግን ሊያዳምጣት አልወደደም(አልፈለገም!!) ደቀመዛሙርቱ ሲጠይቁት፤ ‘‘<ከእስራኤል ቤት> ወደ ጠፉ በጎች ብቻ እንጂ ወደ ሌላ አልተላኩም’’ ይላቸዋል፡፡ በእየሱስ ስም፣ አሁን ምን ማለት ነው ይሄ?? እሺ ይሄም ይሁን፣ ቀርባ ስትሰግድለት ምን አላት? …. ‘‘ የልጆችን እንጀራ ወስዶ ለውሾች መስጠት መልካም አይደለም አላት’’ “እግዜር” ያሳያችሁ እንግዲህ፣ እስራኤላውያንን ልጆች ሌሎቹን ውሶች እያለ ነው ዓለምን ሊያድን መጣ የተባለው ክርስቶስ? ክድሚያ ለእስራኤላዊ እያለን ነው!! ለወገኖቼ ነኝ እያለን ነው፡፡ ዘይገርም እኮ ነው!! ከዚህ በላይም ቡዙ የእስራኤልነቱን የሚያሳ ነገሮች መምዘዝ ይቻላል፡፡

… እኔ ግን እላለሁ፣ እኛም ለራሳችን የሚበች አማልክ፣ በራሳችን ስነ ልቦና እንደ እስራኤሎቹ እንዲመቸን አድርገን ኢትዮጵያዊ አምላክ ብንፈጥር መልካም ነው፡፡ ጠይም መልክ ያለው፣ አማርኛ የሚናገር፣ስናዝን የሚዝን፣ ጥብቅና የሚቆምልን፣እኛው አውርደን እኛወ የምንሰቅለው፤ ለኢትዮጵያውያን ነው የመጣሁት የሚል ኢትዮጵያዊ አምላክ ያስፈልገናል- በሰው አምላክ ምን ጥልቅ አደረገን?
Xenophanes;
“ … human beings have a tendency to picture everybody and everything as like themselves. Ethiopians make their gods dark and snub nosed, while Thracians make them red-haired & blue eyed” ቢልም እስካሁን የራሳችንን አምላክ አልፈጠርንም፡፡ እንፍጠን ጎበዝ! ተቀድመናል፡፡

/ካልተቋረጥን ይቀጥላል/

የራስ ናቸው፡፡ የማንንም ሃሳብ ለመፃፍ አልተከፈተም! የሚያስማሙንን ሃሳቦች እዚህ ካገኛችሁ እሰየው፡፡ ለመስማማት አንፅፍም፣ ለመፃፍ አንስማማም፡፡ ወዘተ

8 Comments

 • Anonymous commented on June 4, 2015 Reply

  ዎዮልህ ላንተ ።

 • lisan commented on April 3, 2017 Reply

  ENDALEGEBAKI GEBETOGNIAL

 • value commented on July 30, 2017 Reply

 • Alex Abreham commented on August 2, 2017 Reply

  AY AGEGNEHU ANTE ENEN TMESLALEH

 • value commented on September 21, 2017 Reply

  ከሳጥንኤል ልጅ ከዚህ በላይ ምን ይጠበቃል። !!(Anti Chirst )

 • value commented on January 2, 2020 Reply

  “ወአንተቀጠቀጥክአርስቲለከኢሲወሀቦሙመናለህዝበኢትዮጵያ”መዝ

 • Anonymous commented on January 13, 2021 Reply

  this is just stupid. yematamen kehone eko no problem gen besew religion endezi mafez tiru aydelem. not cool!!!

 • Melaku@gmail.com'
  መላኩ commented on July 29, 2021 Reply

  መፅህፍ ቅዱስን በጥሬዉ አታላምጠዉ! ይቀርሀል።

አስተያየትዎን እዚህ ይስጡ

የኢሜል አድራሻዎ አይወጣም

Loading...