Tidarfelagi.com

ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦ 6)

እራሴን መሆን ተስኖኝ ተዝለፍልፌ መሬት እንደደረስኩ እትዬ “አንቺ ምን ሆነሻል”  አሉና  አምባረቁብኝ ።  ተንቅልፉ እንደሚነቃ ሰው ሰመመን ውስጥ  ሆኜ ምድር ምድሪቱን ትመለከት በልሁ ተወደ ጀርባዬ እየሮጠ መጣና …”እይይ እቺ ሚስኪን ልጅ  እንዲሁ እትዬ ክፉ እንዳይገጥማቸው ብላ ትትጨነቅ ነው የዋለችው አይዞሽ እትዬ መለኛ ናቸው መላ አያጡም ክፉ አይነካቸውም ብላት አልሰማኝ አለች  ወይ ለርሶ ያላት ፍቅር እትዬ እንዲሁ ትታለቅስ ነው የዋለችው “በደንባራ በቅሎ ቃጭል ተደምሮ “አለ ያ ገር ሰው ልጅቱ ትትታይም ድንጉጥ ነገር ነች የፖሊሶቹ መምጣት የርሶ መጥፋት ጭራሽ ድንብርብሯን አወጣው አሁን ድንገት ስታዬት  ደንግጣ ነው ሰላም ትሆናለች እትዬ አይጨነቁ”

“ቆይ እሷ ምን ለጉማትና ነው አንተ አስረጂ የሆንከው?ምን ሆነሻል እያልኩሽ እኮ ነው!? አሉ አሁንም እየጮሁ ግንባሬን በጣታቸው በመግፋት ታቀረቀርኩበት ቀና እያረጉኝ።

በልሁ እኔን ለማዳን የባጥ የቆጡን ቲቀባጥር ግዜ ስላገኘሁ ተድንጋጤዬ ተመልሼ ነብስ ዘርቼ ትለነበር …እትዬ ሁሉንም ነገር እሱ ተናግሮታል በቃ አንድ ነገር የሆኑ መስሎኝ ደንግጬ ነው አልኩ አፌን እሬት እሬት እያለኝ ፍታቸውን ላለማየት  ያይኔን ቆብ እንደከደንኩ ።

“በይ ተነሽና ወደ ክፍልሽ ገብተሽ አረፍ በይ ”

ክፍሌ እንደገባሁ ሙሉ በሙሉ እራሴን አረጋግቼ ስለተፈጠረው ነገር አሰላስል ጀመር ።እዛ ጠሎት ቤት ውስጥ አንድ ሚስጥር እንዳለ ልቤ ጠረጠረ ።እዚህ ቤት ተተቀጠርኩ ጀምሮ ያላጠዳሁት የቤቱ ክፍል የለም ጠሎት ቤቱን ግን  ላጥዳሎት ብዬ ብዙ ግዜ ብጠይቅም አንድም ቀን እንዳጠዳው ፈቅደውል አያውቁም ።

ብዙ ግዜ  ደግሞ ልጠልይ ብለው ገብተው ቶሎ አይወጡም። አንዳንዴ ደግሞ ድንገት ስልካቸው ቲጠራ መጣሁ ይሉና ስልኩን ተዘጉ ቡሀላ ቆየት ብለው የሚገቡት እዛው ጠሎት ቤት እንጂ ሌላ ቦታ አይሄድም። ተዚህ በፊት ልብ ታልላቸው  በዋዛ ያለፍኳቸው አጠራጣሪ ሁኔታዋች ሁሉ በየተራ በጭንቅላቴ መሰግሰግ ቲጀምሩ የዛን ጠሎት ቤት ሚስጥር ለማወቅ ወገቤን አጥብቄ ተነሳሁ ። ተክፍሌ ውስጥ አድፍጬ እትዬ እስቲተኙ መጠባበቅ እንደጀመርሁ …ተመተኛታቸው በፊት ወደ ክፍሌ ቲመጡ ኮቴ ሰማሁ የተኛሁ መስዬ ተጠቀለልሁ ።ክፍሌን በርግደው ገቡና “ሰናይት አንቺ ሰናይት “ብለው ቲጣሩ ድምጤን አጥፍቼ ዝም አልኳቸው ተመልሰው ቲወጡ ግን

“በይ ተኚ ነገ እናወራለን ተዛ ዘበኝኛ ጋር ምን ስትይ እንደገጠምሽ  ቆይ  “በሬ ከደነበረ ደሀ ካመረረ  ሀገር ተሸበረ” አለ  ገብረ ማርያም “የናንተ አንድ መሆን ምቾቴን ነስቶኛል ቆይ እማረገውን እኔ ነኝ የማውቀው” እያሉ ቱያጉረመርሙ ሰማሁና  በድንጋጤ በተኛሁበት ደርቄ ቀረሁ።

ምን ሊያደርጉ አስበው ይሆን  ፈጣሪዬ እኔ  ወይስ በልሁን ነው ሁለታችንንም ሊያጠፉን  ነው ተመሞቴ በፊት ዛሬ የዚህን ጠሎት ቤት ጉድ ተመልክቼ ያኔ ሁሉም ነገር ይለይለታል እትዬ  እንኳን ምን  እንዳሰቡ በጆሮዬ ሰማሁ እኔና እርሶ ተንግዲህ እዚህ ቤት ውስጥ አይጥና ድመት ነን አልሁና  እራሴን ለመከላከል የሚጠቅሙኝን ነገሮች አበጅቼ ጠሎት ቤት ለመግባት የትዬ ክፍል መብራት እስቲጠፋ መጠባበቅ ጀመርሁ….

ይቀጥላል

ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦ 7)

 

አስተያየትዎን እዚህ ይስጡ

የኢሜል አድራሻዎ አይወጣም

Loading...