Tidarfelagi.com

ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦7)

አድፍጬ  ትጠባበቅ የትዬ ቤት አንፖል ታይጠፋ  እኩለ ሊሊት ሆነ።ተትዬ ባህሪ የማውቀው መብራት ታይጠፋ እንቅልፍ እንደማይወስዳቸው ነው።ግራ ገባኝ እስታሁን አልተኙም ወይስ ታያጠፉ እንቅልፍ ጥሏቸው ይሆን ?ጨነቀኝ። በጭንቀት ትወዛወዝ  ገርበብ ያለው የትዬ ምኝታ ቤት ቲከፈት ሰማሁ።ቆሌዬ ተላዬ ላይ ረገፈ። ተተቀመጥኩበት  ተበሩ ስር ዘልዬ አልጋዬ ላይ ወጣሁ። ጆሮዬን ቀስሬ የትዬን ኮቴ ትከታተል እትዬ ወደ ክፍሌ ተጠጉና በር ላይ እንደደረሱ የርምጃቸው ድምጥ ጠፋ  ቆየና የክፍሌ በር  በትንሹ ቲከፈት  ሰማሁ። ፊቴ ወደ በሩ አቅጣጫ ትልነበር አውቄ የከደንሁትንት አይኔን  የውስጤ ፍርሀት ሊበረግደው ይታገለው ዥመር።

አይኔን ጨፍኜ መጠበቅ ፈተነይ።  ታሁን ታሁን  እላዩ ላይ  የሆነ  ነገር  አረፈ አላረፈ እያልሁ በሰቀቀን መጠበቁ ታቅሜ በላይ ቲሆንብይ አንድ አይኔን በስሱ ከፍቼ ጭንቀቴን ልተነፍሰው ወሰንሁና ያይኔን ቆብ በሽፋሽፍቴ ልክ ገለጥ አድርጌ ወደ በሩ ትመለከት  እትዬ ተላይ እስተ ታች ጥቁር ካቦርታ ውስጥ ተሰንገው  አናታቸው ላይ  ደሞ ጥቁር የሹራብ ኮፍያ እንዳጠለቁ በሬ ላይ  ተገትረው ቁልቁል ቲመለከቱኝ  በማየቴ አንቀው ሊገላግሉኝ ነው ብዬ  በተኛሁበት በላብ ተዘፈቅሁ።

ትንሽ ቆም አሉና ተካፓርታው  ኪስ ውስጥ ቁልፍ አወጡ።

ተዛ ተክፍሌ ወጥተው ተውጪ ክፍሌን  ቆለፉት።ሰውነቴ በፍርሀት እየተንቀጠቀጠ ጆሮዬ የትዬን አቅጣጫ ተከትሎ አብሮአቸው  ቲወጣ  እትዬ ወድ ጠሎት ቤቱ አቅጣጫ መሄዳቸው ተረዳኝ ። ወድያው ታልጋዬ ወርጆ ወለሉ ላይ በሆዴ ተነጠፍሁና ጆሮዬን እወለሉ ላይ ለጥፌ ታደምጥ ጠሎት ቤት ገብተው አፍታም ታይቆዩ  ድም…ድም….ድም..እያለ ሰው ደረጃ ቲወርድ የሚያሰማው አይነት ድምጥ ትሰማ  እትዬ ተወለል  በታች ቁልቁል እየወረዱ መሆንን ለማወቅ  አልተሳነይም ነበር። እህን ግዜ ልቤ ተውስጤ አፈትልካ ለመውጣት የከጀለች እስቲመስለኝ ድረስ ደረቴን ለጉድ ትደልቀይ ዥመር። ክፉኛ  ተመደንገጤም ባለፈ  እስተዛሬ ጠሎት ቤት የተባለው ቤት ድብቅ መውረዥ ያለው የዋሻ በር   እንዴት እና  በየት በኩል ሊኖረው  ይችላል  ብዬ  ባስብም  አልመጣልሽ አለይ ። ወይ ጠሎት ቤት ፣ ወይ ጠሎተኛዋ እትዬ ይገርማል “ተወገብ በታች ጣኦት ፥ ተወገብ በላይ ታቦት ” ያለችው  እምዬ  እንደዚህ አይነት ግማሽ ሰይጣ ግማሽ ሰው የሆነው ገጥሟት ይሆን? አልጋዬ ጫፍ ላይ ቁጭ ብዬ በጭንቀት ትብገነገን  በዛ ውድቅት ለሊት የውጭው በር ቲከፈት ሰማሁና ተተቀመጥሁበት በርግጌ ተነሳሁ  ወድያው  በልሁ ”  በህግ አምላክ ምን  ፈልገህ  ነው አትጠጋይ !” ቲል ተሰማይ እትዬ በጠሎት ቤቱ  ነው  የገቡት አሁን  ደሞ በልሁ  ተወንድ ጋር  ነው  እሚጨቃጨቀው  ፈጣሪዬ  ምን  ጉድ  ውስጥ  ከተትከይ  እኝ ሴትዬ እዥ ብዙ  ናቸው  ያለው በልሁ እውነቱን ነው ውይ ወንድሜ እኔው ነይ ጦስ ያመጣሁብህ።

ውስጤን አንዳች ነገር ቲያናውጠው ታወቀይ። ትንሽ ቲጨቃጨቁ ቆዩና  አንድ ሰው በሀይል  እንደተመታ  “ወይኔ እናቴ”  የሚል ድምጥ አስማ ። በሩ ዳግም ተከፍቶ መልሶ በሀይል ተዘጋ  ተዛ ሁሉም ነገር መልሶ ፀጥ ረጭ አለ ። ትንሽ ቆይቶ ተትዬ ጎን ያለው ትልቅ ግቢ ውስጥ ምን እንደሆነ  የማይለይ ድምጥ ሰማሁ መልሶ  ፀጥ አለ። በልሁን አንድ ነገር እንዳደረጉት ልቤ ቲጠረጥር እራሴን መሆን ተሳነኝ።  አልቅሼ የማላውቀውን  መራር ለቅሶ አለቀስሁ። እልህ  እና ጭንቀቴ ተቀይሮ እንደ እብድ አደረገይ በጥፍሮቼ ግድግዳውን መቧጠጥ ልብሴን  መቅደድ ጀመርሁይ።

እትዬ ታልሞትኩ በቀር እሄን ጉዶን ለአለም አሳይሎታለሁ አልሁ ጮክ ብዬ  …

ይቀጥላል

2 Comments

  • value commented on November 16, 2019 Reply

    ምርጥ ነዉ

  • Anonymous commented on June 22, 2021 Reply

    ለኔም ጭንቀት ሆነብኝ ከባድ ነው

አስተያየትዎን እዚህ ይስጡ

የኢሜል አድራሻዎ አይወጣም

Loading...