Tidarfelagi.com

ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦ 5)

እሄን ግዜ በልሁ “እዚህ ቤት ሰራተኛች ሲገቡ እንጂ ሲወጡ  አይቼ አላውቅም” ያለኝ ነገር  ተትዬ መሰወር ጋር ተገናኝቶ በመላ ሰውነቴ ትኩሳት ከፍርሀት ጋር ለቀቀብኝ። ፓሊሶቹ ስራቸውን አገባደው ለምሄድ ሲሰናዱ አየሁና እየተጣደፍኩ ወደ በልሁ ጋር ሄጄ እኔ ይችን ቀን እዚህ ቤት ከማድር ወጥቼ መንገድ ላይ ብሞት ይሻለኛል ትለው  “እናትሽንስ ታናሽ ወንድምሽንስ  አታዝኝላቸውም ባክሽ  ተይ አታድርጊው ” አለኝ  ክንዴን ጨበጥ አርጎ።

እሄውልሽ ሰንዬ እኔን ምን እንዳሉኝ ልንገርሽ  አንድ ስተት ብትፈፅም በነዚህ ላይ እንደፈረድክ ቁጠረው ብለው  ያሉበትን ቦታ እንደሚያውቁ ቀያቸው ድረስ ሄደው ያነሱትን የቤተሰቦቼን ፎቶ ነው አምጥተው ያሳዩኝ። ታናሽ እህቴ  አድጋ ውሃ ለመቅዳት መብቃቷን እንኳን ያየሁት ተነ እንስራዋ አንስተው ባሳዩኝ ፎቶ ነው። ሰንዬ ያንችንም ማወቃቸው አይቀርም ተይ ይቅርብሽ ቀን እስኪያወጣን እንጠብቅ።  መሞት ካለብንም ቤተሰቦቻችን ታይነኩ  ብቻችንን እንሙት” ሲለኝ ምን እንደሆን እንጃ ተላይ እስከታች  ሲወረኝ ተስማኝ  አይኖቼ  በእንባ እንደተሞሉ  ፓሊሶቹ  ግቢውን ለቀው ወጡ… የፍርሀት ፣ የመገፋት እና  የመበደል  ስሜት መላ አካላቴን  አላወሰው። ተከትለሻቸው  እሩጪ እሩጪ አምልጪ  እራስሽን  አድኚ የሚል ስሜት ወተወተኝ።

በር በሩን ስመልከት  ሆዱ ነገረው  መሰል በልሁ  ተንደርድሮ በሩን ጠረቀመው እንኳን  እዛ ቤት   ተመልሼ ልገባ   ዞሬ  ማየት  አስፈራኝ   በሀገሬ  ውስጥ  ከሰው ጋር የምኖር  አልመስልሽ አለኝ።  ተዛ ግቢ ውጪ  ሰላም  ሰው  ሳቅ  ደስታ  በጥቅሉ የተለመደ የሰው ኑሮ   መኖሩን  ውስጤ አልቀበል አለኝ አርቀው  የወረወሩት የማይፈለግ  ጥቅም አልባ እቃ የሆንኩ  መስሎ ተሰማኝ  የሚያስብልኝ ወገን ዘመድ ቤተሰብ የለለኝ  ከሰው እንዳልተፈጠርኩ መኖሬም መሞቴም በሰው ፍቃድ የሆነ ሳልሞት ደራሽ ብሞት ወቃሽም  አልቃሽም  የሌለኝ ተስፋ ቢስ ሰው አልባ መሆኔ ሲታወቀኝ  ለዚህ የዳረገኝን ድህነቴን  ጠላሁት። መፈጠሬን ረገምኩት።  ተንሰቀሰቅሁ። በልሁ ሊያባብለኝ ሞከረና ለቅሶዬ ብሶቱን ፈንቅሎ አወጣው መሰል ይንሰቀሰቅ ጀመር።

ወደ ቤት ተመልሼ ለመግባት እግሬ አልላወሲ ቲለኝ እዛው ቁጭ እንዳልሁ በሉሁ ወሃ “እንኪ ፊትሽን ታጠቢና ግቢ ደሞ እትዬ እዚህ ጋር ተቀምጠሽ ታዩሽ ጥሩ አይመጣም ሰንዬ ” እሺ እስከመቼ በልሁ እስከመቼ ነው ታለ ወንጀላችን እንደ ወንጀለኛ ታስረን የምንኖረው? “እንጃ ሰንዬ ” እንጃ….እንጃ አልከኝ በልሁ  “ታድያ ምን ልበል ሰንዬ ” የህል ክፉ አጃ የሳር ክፉ ሙጃ  የነገር ክፉ እንጃ “አለ  ያ ገር ሰው   እባክሽ ተነሽ ሰንዬ እዚሁ ቁጭ ብለሽ እትዬ እንዳይመጡ”የሉም አልኩህ እኮ። “ፓሊሶቹ ያልደረሱበት መሸ መሸሸገያ ቢኖራቸው እንጂ ወየት ይሄዳሉ ሰንዬ?”ፈራሁ በልሁ  እኔ እዛ ቤት ተመልሼ አልገባም። ለምኖ ወደ ቤት አስገባኝና ጠጋ ብሎ ” በርታ በይ “ብሎኝ ወጣ  ቀኑ ደንገዝገዝ ብሏል እቤት ውስጥ መቀመጥ ስለፈራሁ ሳሎኑ ደጃፍ ላይ ተቀምጬ በልሁን በቅርብ ርቀት እያየሁት ትንሽ እንደቆየሁ ትከሻዬን ከበደኝ ደሞ ተጠሎት ቤቱ ውስጥ  የሆነ ድምጥ የሰማሁ መሰለኝና ልቤ በላይ በላይ መምታቷን  አባሰችው ብድግ አልኩና  ወደ በልሁ ተጠግቼ ተቤት ውስጥ ድምጥ ሰማሁ አልኩት “ስለፈራሽ ነው ሂጂ ሰንዬ እዛው ሁኚ” አለኝ ተመለስኩ ተመቀመጤ በፊት ወደ ቤቱ ውስጥ አየት ታረግ እትዬ ፀጉራቸው ተንጨብርሮ ጭራቅ እንደመሰሉ ሳሎኑ መሀል ላይ ተገትረው አፈጠጡብኝ ።ተይህ ቡሀላማ ምኑን ላውጋችሁ ..እንዳልጮህ ፍርሀቱ አፌን አሰረኝ ፣እንዳልሮጥ ድንጋጤው ጉልበቴን ከዳኝ ትንሽ ቆይታ ልቤም ተወችኝ..

ይቀጥላል

ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦ 6)

 

አስተያየትዎን እዚህ ይስጡ

የኢሜል አድራሻዎ አይወጣም

Loading...