Tidarfelagi.com

ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦29)

ቁልቁል እየተመለከቱ ሽቅብ ቲወጡ የልቤ ትርቷ ተመቅፅበት እጥፍ ሆነይ። ተጦሎት ቤት ወጥተው ወደ ምኝታ ክፍላቸው እስቲገቡ ቸኮልሁ።እትዬ ተዛ ድብቅ ዋሻ ወጥተው እንዳበቁ የጠሎት ቤቱን ድብቅ የወለል በር ዘግተው ተመሄድ ይልቅ አፋፉ ላይ ተገትረው ቁልቁል ቲመለከቱ ይህቺ መሰሪ ሰትዬ ምን ሆና ነው ተገትራ የቀረችው? ብዬ እንዳፈጠጥሁ ትጠብቅ  በጠሎት ቤቱ የወለል በር የሻንቆ ጭንቅላት ወደ ላይ ብቅ ቲል ሰው ታይሆን ጅብ ተጉድጓድ ውስጥ የመጣብይ ነው የመሰለይ።እቆምኩበት ውሃ ሆንኩይ። መላ አካላቱ ሽቅብ ወጥቶ እስቲያልቅ እያየሁት ማመን ተሳነይ። ወይህ ቤት አንድም ቀን መጥቶ የማያውቀው ሌላኛው አውሬ ሻንቆ ዛሬ ምን ሊሆን እንደመጣ ግራ ገባይ ዛሬ የዚችን እርኩስ አሮጊት እስትንፋስ ልቋጨው በቆረጥሁበት እለት እሄ እንኳን እኔ የያዝሁት ሽጉጥ በመድፍ ቢመቱት የሚሞት የማይመስል የሰማይ ስባሪ የሚያህል ሰውዬ ምን ሊሆን በዚህ ውድቅት ለሊት እትየን ተከትሎ መጣ? እሄማ የሚያመልኩት አጋንንት እጅ አለበት እንጂ አጋጣሚ የተፈጠረ ነው ብዬ ማመን አልችልም።ሆን ብሎ የትዬን ህይወት ለማትረፍ እሱን ወዲህ እንዲመጣ ያነሳሳው እሱ ታልሆነ በቀር ሌላ ማን ይሆናል? አሁን ሳሎን ሊተኛ ነው  እሄ ዳውላ እንደዛ ተሆነ ተሱ ተመጀመር ውጪ አማራጭም የለኝ ? እያልሁ ትጨነቅ ተያይዘው እየተሳሳቁ ወደ እትዬ ክፍል ቲገቡ በድንጋጤ ደርቄ ቀረሁ።ድሮስ ታንቺ ምን ይጠበቃል አንቺ የተረገምሽ ሴትዬ ባልሽ እስር ቤት ተገባ ሶስት ወር ታይሞላው ተሌላ ወንድ ጋር ልትጋደሚ እግዚኦምን አይነታ የሰው ዝቃጭ ነሽ ጃል በስንቱ ሀጥያት ውስጥ ተነክረሽ ትችይዋለሽ ክፋታችሁ እና ሃጥያታችሁ የበዛው ድሮም አንድ አይነቶይ ትለሆናችሁ ነው በህውቴ እንደዚች አይነቷን የሰው ከንቱ አይቼ አላውቅም!።

እክፍላቸው ተገቡ ቡሀላ እትዬ ተመልሰው ወጡና የኔን ክፍል ከፍተው ልብሳቸውን ቀይረው ውስኪና በርዶ ይዘው ገቡ።

ሊጠጡ መሆኑን ትረዳ ወኔዬ ዳግም ተነሳሳ። ፈጣሪዬ አንድ ትጠይቅህ ሁለቱን አከታትለህ ያመጣህልይ ለበጎም ታይሆን አይቀርም። ብቻ እስቲሰክሩ ተግተው ይተኙልይ እይ መጀመሪያ ይሄን ጠረንገሎ ሽጉጡን ወደ ግንባሩ አስጠግቼ ተገላገልሁት የትዬ “እዳው ገብስ ነው”።

ጠጥተው እስቲዘረሩ አይኔን ታልነቅል እያቁለጨለጭሁ እትዬ ተባላቸው መታሰር ቡሃላ አርገው የማያውቁትን ድንገት ብድግ ብለው የምኝታ ቤታቸውን በር ደርግመው ቆለፉት። ይህን ግዜ ተሆዴ ውስጥ የሚያቃጥል ነገር ተሰማይ። ፈጣሪ በቁሞ ልሳኖትን ይዝጋው እሄን በር ትለዘጉ ሃጥያቶትን ተሰው ሸሸጉ እንዢ ተፈጣሪ እይታ አያመልጡ ይድፋዎት። ንዴቴ ትላየለብኝ እራሴን መቆጣጠር ተስኖኝ ጠጉሬን በገዛ እጄ እየነጨሁ እያለቀስሁ ወደ ክፍሌ ታመራ ቲስቁ ድምጣቸውን ትለሰማሁ አዞረኝ ተመውደቄ በፊት ዦሮየን በሁለት እጄ ደፍኜ ወደ ክፍሌ ገባሁና በሩን ዘጓሁት።

አልጋዬ ላይ በሆዴ ተደፍቼ ትንሽ እራሴን ታረጋጋሁ ቡሃላ እንቅልፍ ይዟቸው ተሆነ እበልሁ ዘንድ ልሄድ አሰብሁና የክፍሌን በር ከፈት ታረግ ተጣራ በላይ እያወሩ ተጣራ በላይ ይስቃሉ። አፋችሁን ይዝጋው! አልሁና መልሼ የክፍሌን በር ዘጋሁት። እሄ ያንተ ስራ ነው አንተ የተረገምህ ሰይጣን ዋና ስራ አስፈጣሚህን ተሞት ለመከላከል ሌላ ሀጥያት እንድትሰራ በባሏ ላይ ክህደት እንድትፈጥም አነሳስተህ ተሻንቆ ጋር እንድትዳራ አደረግሃት። ውሽማ እንደሁ ቢያድር እንዢ አብሮ አይኖር እስቲ ያንተ ሀይል እኔ ተማመልከው ፈጣሪ ይበልጥ እንደሆን እንተያያለና! ሻንቆ እንደሁ እኝህን እርጉም ሴትዬ በጥዋት ጥሏቸው መሄዱ እሳቸውም ተክፍላቸው መውጣታቸው አይቀር ቲነጋ እንገናኛለን  ገድያቸው እሞት እንደሁ እንጁ ወደ ኋላ እንደማልል እወቀው!።

እክንዴ ላት ፋሻው መሀል የሻጥሁትን ሴንጢ እና ሽጉጥ ሻንጣዬ ውስጥ ደብቄ ቁጭ ብዬ ትብሰቀሰክ ቆየሁና ጋደም እንዳልሁ….

ይቀጥላል

አስተያየትዎን እዚህ ይስጡ

የኢሜል አድራሻዎ አይወጣም

Loading...