Tidarfelagi.com

ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦27)

እህን ግዜ እራሴን መቆጣጠር ተስኖይ ጩሂ ጩሂ ትላለኝ አፌን በሁለት እጄ ግጥም አድርጌ ያዝሁት። አጣብቆ ተያዛት ግድግዳ ላይ ትንፋሽ አጥሯት አይኗ እስቲገለበጥ አቆያትና ተላይ አንገቷን ባንድ እጁ እንዳነቃት ተስር ሁለት እግራን ባንድ እጅ ጠርንፎ ሽቅብ በማንሳት እትከሻው ላይ ቲሸከማት እሷንም ለዘንዶ ወረወራት ብዬ በድንጋጤ ልቤ ባፌ ልታመልጠይ ደረሰይ። ተሸክሞ እዛው እክፍሉ ውስጥ ተበልሁ በስተቀኝ ታለው አልጋ ላይ ወስዶ አጋደማት። እህን ግዜ አይኔን ጨፈንሁ።

እትዬ ያንን ለዦሮ የሚሰቀጥጥ ሳቃቸውን ቲለቁት አይኔን ገልጬ ቁልቁል ትመለከት።ልጁቱ በጀርባዋ እንደተንጋለለይ ታለቅሳለይ። ሻንቆ እሆዳ ላይ ተቀምጦ ፊቱን ወደ እግሮቿ በማዞር ሁለት እግሮቻን በርግዶ ታልጋው ግራና ቀኝ ብርት ጋር ጠረነፋቸው።እማደርገው ባጣ ጠሎት ዥመርሁ።ታሰራት ቡሃላ ተላይዋ ላይ ወርዶ እልጅቱ ላይ ለመስፈር የትዬን ፍቃድ እየጠበቀ ነው መሰል እጆቿን ቁልቁል ወጥሮ እንደያዘ ጥግ ላይ የኤሌትሪክ ምድጃ ለኩሰው ብረት ወደ ሚያግሉት እትዬ ይመለከታል። እትዬ ደሞ ብረቱን የሚያግሉት ምን ሊያረጉ ነው? ለሷ ነው ወይስ ለበልሁ ኧረ ፈጣሪዬ ተው አንድ በላቸው!።እትዬ ብረቱ ቀይ እስቲሆን ታጋሉት ቡሃላ አንስተው ግራ ገብቷት መጮኋን አቁማ በፍርሃት ቁልጭ ቁልጭ ወደ ምትለው ልጅ እየተጠጉ ” ስሚ አንቺ ድመት ሞትስ አንድ ነው አስከፊ እሚያረገው አሟሟቱ ነው ክክክክክ ጣርሽን የሚያበዛው ምላስሽ ነው። ምላስሽን ሰብስቢና የምትባይውን አድምጪ!ያለበለዚያ ግን…” አሉና ያጋሉትን ብረት ወደ ልጅቱ ጡት እያስጠጉ “መጀመሪያ እሄ የሚንጣጣውን ምላስሽንና የሚጮኸውን ላንቃሽን በዚህ በጋለ ብረት ስራዉን እንዲያቆም አደርገዋለሁ ከዚህ ትምህርት ወስደስ ጠባይሽን ካላሻሻልሽ ደሞ እዛ ጋር ያለው ትልቅ ጀሪካን ይታይሻል? ውስጡ ምን እንዳለ ታውቂያለሽ  እንኳን አንቺን ስጋ ቢስ ዘጠና ኪሎ ግራም የሚመዝን ጠብደልን አሟምቶ ወደ አምስት ኪሎ ግራም የሚቀይር ምርጥ አሲድ ነው ያንን አሲድ በትንሹ አርከፈክፍብሽና ለቀብር የማይስቸግር የስጋቤት ቅንጥብጣቢ  ካደረኩሽ ቡሀላ በፌስታል ጠቅልዬ ቀብርሻለሁ “። በማለት ተሻንቆ ጋር እየተያዩ ክክክክክክክሃሃሃሃሃሃ ተንከተከቱ!። ልጅቱ መልስ ሳትሰጥ ዝም ብላ ሽቅብ እያየቻቸው እንባዋ ይረግፋል።ሻንቆ እትዬ ምልክት ቲሰጡት ተላይ የለበሰችውን የልጁቱን ልብስ በረጨቀው። ” እሺ ምን አርጊ ነው እምትሉኝ?” አለይ የኔ ሚስኪን ሁኔታቸው አስፈርቷት እየተርበተበተይ። አዎ እንደዛ ነው እሚባለው አሉና እኩል አሽካኩ።

“እሁን የምነግርሽን በጥንቃቄ አድምጪ! ዝግጁ ነሽ?” መልሳ ዝም አለይ። ” ዝግጁ ነሽ ወይ !” አለና ጮኸባት ያን አስፈሪ ፊቱን ወደ ፍቷ እያስጠጋ። ልጅቱ ቃል ታይወጣት መስማማቷን በምልክት ገለጠይ። ይህን ግዜ እትዬ ፍም የመሰለውን ብረት እንደያዙ እያስካኩ ወድ ልጅቱ ቲጠጉ … እኔ ግን ታቅሜ በላይ ሆነብይ ተዚህ በላይ የልጅቱን ስቃይ ማየት ተሳነይ። የነኝህ አረመኔዋይ ድርጊት ተዚህ በላይ ተተመለከትኩ የማብድ ትለመሰለይ ቢሆንልይም ባይሆንልይም አደርገዋለሁ ላቀድሁት የመጨረሻ የሞት አልያም የነፃነት እና የድህነት እርምጃዬ የሚሆኑኝን ነገሮይ ለማሰናዳት ወሰንሁ። ተነስቼ ተጠሎት ቤቱ ወጣሁና ወደሳሎን በማምራት እትዬ ቁልፍ ቲደብቁበት ያየሁትን አሻንጉሊት ተሶፋው ላይ አነሳሁ።

እሳቸው ቲያረጉ እንዳየሁት እሆዱ ላይ ጠጉር የሸፈናትን ዚፕ ከፈትሁና እጄን ወደ ውስጥ ትልክ ቁልፉን አገኘሁት። ቁልፉን አውጥቼ ሽቅብ ደረጃውን በመውጣት እግድግዳው ላይ የተሰቀለውን ስእል አወረድሁት ተዛ ተግድግዳው ጋር የሚመሳሰል ቀለም ያላትን ፕላስተር ፈልጌ ተግድግዳው ላይ ትገሸልጣት ቁልፍ ማስገቢያዋ ታየችይ።ቁልፉን ዶልሁና ዘወርሁት ተበረገደ።ማሳቢያውን ትስበው ውስጡ ያለው የሽጉጥ አይነት አይን አዋዥ ሆነብይ….

ይቀጥላል

አስተያየትዎን እዚህ ይስጡ

የኢሜል አድራሻዎ አይወጣም

Loading...