Tidarfelagi.com

ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦25)

እኝህ ሴትዬ መጥተው ተምድረ ገፅ ታይሰውሩኝ በፊት የማመልጥበት መላ ቢከሰትልይ ብዬ ታወጣ ታወርድ ቆየሁ። ትለ ባለቤቶ መፈታት ቲያወሩ ውስጤን ደስ ብሎት ትለነበር ይሆናል ታይታወቀይ ያመለጠኝ ልበላቸው አይ ይህም አይሆንም አንድ ግዜ አላልሁም ብያለለሁ አላልሁም በቃ በዚሁ ተመድረቅ ውጪ ሌላ ማምለጫም የለይ “ምን ብታፈገፍጊ ተግድግዳ አታልፊም” ያለው ማን ነበር እቴ ተነዚህ እርኩሶይ ወዴት ይሸሻል ወደ ግራም ወደ ቀኝም ቢዞሩ እነሱ ያበጁት የክፉ ሰዎይ ግድግዳ ነው ያለው ወደ ላይ ቀና ብሎ ለሱ ተመንገር በቀር መላም የለ።

መሂናቸውን እንዳስገቡ እግቢው ውስጥ ወዲያ አዲህ እየተንጎራደዱ ስልክ ቲያወሩ ቆዩና አቦሉ እንደፈላ ጨርሰው ወደ ቤት ገቡ።

እንደገቡ ተግር እስተራሴ በክፉ አይን እየተመለከቱይ …”ያንቺ ጉዳይ በይደር ይቆይ መጀመረያ እጄ ላይ ያሉትን ስራዎች ልጨርስ !”አሉና ወደ ምኝታ ክፍላቸው ገቡ።

እሱን ፈጣሪ ያውቃል እትዬ ደሞ ሰዋቹን ልጨርስና ተረኛዋ አንቺ ነሽ አይሉይም ተዛ ሌላ ምን ስራ አሎት አልሁ እንዳይሰሙይ ወደ ክፍላቸው በጎን እየተመለከትሁ።

አፍታም ታይቆዩ ልብስ ቀይረው ወደ ሳሎን መጡ።

አቦሉን ቀድቼ ትሰጣቸው ቡናውን ታይቀበሉይ ይዤ እንደቆምሁ ሽቅብ እየገላመጡይ ” ደላላው ጋር ደውያለሁ እንዳመጣልኝ አንቺን ወደ ምሸኝበት ሸኝሻለሁ !” አሉይ።

ቡናውን ሰጥቼ ትመለስ ወዴት እንደሚሸኙኝ አውቀውልለሁ እትዬ “እንዶድን በገርነቷ ወሃ ወሰዳት” አለይ እምዋ። ብቻ እንኳንም ግዜ ሰጡይ እንዢ አይድከሙ በቀላሉማ አይገሉይም።ታይሸኙኝ እኔ ሸኛት ይሆናል ማን ያውቃል። ተቅዴ በፊት ጨረሱይ  ብዬ ትሰጋ ግዜ ትለሰጡይ ፍርሀቴ ተውስጤ ጠፋ።

ተዛ በሃላ የሚጠራውን ስልካቸውን እየያዙ እሁንም አሁንም እየወጡ ቲያወሩ እኔን አባከና ታይሉኝ መሸ።

ስልክ ቲያወሩ በጨረፍታ እንደሰማሁት ተሆነ ያፈኗቸውን ሰዋይ ዛሬ ታያመጣቸው አይቀርም።

ወደ ምኝታ ክፍላቸው ገብተው ቲተኙ በልሁ የጠረጠረው ካሜራ ባይኖር ነው ዝም ያሉትብዬ እፎይ አልሁ።

ቆየት አልሁና ወደ ክፍሌ ገባሁ።እትዬ እውነት ደውለውላቸው ተሆነእነዛ ሰውና እቃ ለይተው የማያዩ ደላሎይ ቀጣይዋን ለትዬ መስዋእት የምትሆነውን ሰራተኛ እንደበግ ጎትተው ለማምጥት ተነገ አያልፉም።እትዬ ስራቸውን ዛሬ ተጨረሱ ዋጋን የለኝ። ታልፈጠንሁ እትዬ ይቀድሙኛል የያዙዋቸውን ሰዎይ ተበልሁ አጠገብ አስረው ማስቀመጣቸውንና በልሁ ታይገደል በሂወት ማደሩን አረጋግጬ ማደር ግድ ትለሆነብይ እንደባለፈው ትራሱን አስተኝቼ እትዬ ታያዩኝ ተክፍሌ ወጥቼ እላይኛው ክፍል ተደበቅሁ። የተደበቅሁበት ክፍል የግድግዳ ሰአት ስድስት ሰአት ላይ እንደጠቆመ ተግቢው ውጪ የመሂና ድምፅ ተሰማይ።ወድያው አፍታም ታይቆይ ተትዬ ክፍል ስልካቸው ቲያቃጭል ሰማሁ።አንስተውም ታያወሩ ቆየት ብለው ያንን አስፈሪ አለባበሳቸውን ለብሰው በመውጣት በፍጥነት የኔን ክፍል ተውጪ ቆልፈው በጠሎት ቤቱ ቁልቁል ወረዱ። ፈጣርዬ በልሁን እንዲያተርፍልይ አልቅሼ ለመንሁትና ቁልቁል ወደ ጠሎት ቤት ወረድሁ።ቁልቁል ትመለከት አይናቸው በጥቁር ጨርቅ እጃቸው የኋሊት የተጠረነፉ አንዲት ቆንዦ ሴትና አንድ ጎልማሳ ወንድ ያ ጥላሽት የመሰለ ሰውዬ እየገፈተረ እትዬ አጠገብ አቆማቸው።

የትዬን ሳቅ ስትሰማ ልጁቱበእልህ ተንጨረጨረይ። እንኳን ደና መጣሽ የኔ እመቤት ብለው አይኗ ላይ ያለውን ጥቁር ጨርቅ ተመፍታታቸው ቁና ሙሉ ምራቅ እፍታቸው ላይ ለደፈይባቸው። እንዲህ ያለች እለኸኛ ሴት አይቼ አላቅም። ምራቋንም ተፍታባቸው “አንቺ የዛ ስጋ ለበስ አውሬ ባለቤት እኔን ብትገይኝም ባልሽ ግን መቀመቅ ከመውረድ አይድንም ብላ ትትጮህ ” እትዬ ተተሰቀሉት ገጀራዎይ ተለቅ ያለውን በማውረድ ፊታቸው ላይ ያለውን ምራቅ እየጠረጉና በእልህ እየተንቀጠቀጡ ወደ ልጅቱ ተምዘገዘጉ አጠገቧ ደርሰው ታሁን ታሁን በያዙት ትልቅ ገዠራ አንገቷን ቀንጥሰው ጣሉት ብዬ ትሳቀቅ ቆም ብለው ትንሽ አሰቡና  ሁለቴ በጥፊ አልሰዋት ቀዩ መጋረዣ ወደ ተሰቀለበት ክፍል ገብተው አፍታም ታይቆዩ ወጡና ለሻንቆ ጠጋ ብለው በጆሮው ምን እንዳሉት እንጃ ተልጁቱ አጠገብ የቆመውን ሰውዬ ተሸክሞ ዘንዶው ያለበትን ክፍል በመክፈት ወደ ውስጥ ቲወረውረው ልጅቱ እሪታዋን አቀለጠችው እኔም ባለሁበት ወኔዬ ሁሉ ተውስጤ ተነነ..

…ይቀጥላል

አስተያየትዎን እዚህ ይስጡ

የኢሜል አድራሻዎ አይወጣም

Loading...