Tidarfelagi.com

ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦24)

አረ ምንም አላልሁም እትዬ ምን እላለሁ ብለው ነው።

“ቆይ..ቆይ ቆይ ቆይ … እሄን ሁሉ አመት ሰናይት ብለው ሲጠሩሽ አቤት ሲያዙሽ እሺ ከማለት ውጪ ድምፅሽ የማይሰማ ልጁ ዛሬ እንደማይረባ ከሰል እላዬ ላይ የምትንጣጭብኝ ምንድን ነው ሚስጥሩ ለመሆኑ? እ ንዴ: ማን ነው ፈቶ የለቀቀብኝ ባካችሁ ?”

ማ…ማን…ተ…ተየት ነው እሚፈታኝ እትዬ ወይኔ እምዬ  ታይታወቀኝ ጉድ ሆኛለሁ አልያም እየቃዥሁ ነው መሰል… አልሃቸው  ባፍዝ አደንግዛቸው ተራሴ አረሳስተው አስረው የለቀቁይ መስሎይ…

“እንዲህ ነሽና …ምናልሽ አንቺ  እኔ ላይ እየቀለድሽ ነው?”

አረ አልቀለድሁም እትዬ።

“ታድያ እየቃዠሁ ነው እምትይው እያላገጥሽብኝ ካልሆነ በቁምሽ መቃዥት ጀምረሽ ነዋ “አሉ ይበልጡን ያን አይናቸውን ተማደሪያው ጎልጉለው እያወጡ..

እትዬ ምን ላርግ ማን ነው ፈቶ የለቀቀብኝ ቲሉ ግዜ እኔም ታስሬ ነበር እንዴ ብዬ እኮ ነው!።

“ምናልሽ አንቺ ሙትቻ እ..እኔም ታስሬ ነበር …ወይይ !?

እዚህ ቤት ሌላ የታሰረ ማንን ታውቂያለሽ እና ነው እኔም ታስሬ ነበር ወይ የምትይኝ! ”

እኔም አልሁ እንዴ ኧረ አላልሁም ባኮት እትዬ እኔ ነው ያልሁት እይ መች እኔም አልሁ?

“እሄማ ጫን ያለው ነው ወይይይይ ጉድ በቀላሉ አንላቀቅም ነይ ነይ ነይ ውጪ ነይ ወደ ሳሎን !” አሉይና አራስ ነብር  እንደሆኑ ቀድመውይ ሄደው እሶፋው ላይ ተቆለሉ።

ዛሬስ አበቃልኝ ምን ትል እሄን ቃል ታፌ እንዳወጣሁት ግራ ገባይ “አፍ ቲከዳ ተሎሌ ይብሳል “አለች እምዋ ፈጣሪዬ የዛሬን አውጣኝ እይ ሁለተኝ ተኝህ አሳሳች ሴትዬጋ አፌን እልካፈትም።

“ነይ ወደ እዚህ ከፊቴ ቁሚ!” አሉይ አይናቸውን እኔ ላይ ጣታቸውን ደሞ ወደ መሬቱ ቀስረው እምቆምበትን ቦታ እያመላከቱይ። ተጠግቼ ቆምሁ።

“ዛሬ ሌላ ጠንቅ ሳይከተልሽ እኔም ታስሬ ነበር ወይ ያልሽው ምን ለማለት ፈልገሽ እንደሆነ ተናገሪ!”

ኧረ እትዬ እባኮትን ይመኑይ እኔኮ  ያልሁት እኔ ነው አልሆት ይህችን …ም..ያሏትን  ፊደል ፈጥሞ አልጠሯኋትም።

“ጠራሻት ወይ አላልኩችም ምክንያቱን ተናገሪ ሌላ እርምጃ እንድወስድ እትገፋፊኝ ብዬሻለሁ ሰናይት!”

እትዬ ይተው እንጂ እንደው ታልጠፋ መጣያ ሰበብ ይቺ ህጣን ልጅ ተወረቀት ላይ በላፒስ በሚያጠፋት  ባንድ ፍደል እንጣላ?ደሞ ጠርቻት ቢሆን በጀ።

“ፍደሏ ሳትሆን መልክታ ነው ከባድ አንቺ ደነዝ ያልሽው : እኔ : ሳይሆን : እኔም : እንደሆነ በገዛ ጆሮዬ ነው የሰማሁሽ !”

እትዬ ይመኑይ ይቺ …ም…የተሰኘይ ጠንቀኛ ፊደል እኔ ተተናገርሁ ቡሀላ እጆሮዎ ቲደርስ ጅኒ ይጨምራት ሰይጣን እንዣ እንጂ እኔ አልጠራኋትም።

ይህን ግዜ የትዬ ቁጣ ቅጥ አጣ ተተቀመጡበት ተነስተው በጥፊ ቲመርጉብይ ተምን ውስጥ እንደነቃው እንጃልይ ብቻ ተሆነ ነገር ውስጥ ነቅቼ ወደ ራሴ ተመለስሁ።

“አንቺ ብጣሻም ደሃ በቀላሉ አንላቀቅም መኪናዬን ላስገባት። አሁኑኑ ቡና እፈልጋለሁ።የትኛው ጂኒ ወይም ሰይጣን ካንቺ ወሬ እየተቀበለ ለኔ እየጨመረ እንደሚነግረኝ ትነግሪኛለሽ። ደሞ ሰይጣን እሚያጣላው ሰው አጣና ነው እኔን የተከበርኩ ሴትዬ ከእንዳንቺ አይነቷ ምናምንቴ ጋር ለማጣላት ስራ ሚፈታው : ከግር ጥፍርሽ እስከ እራስ ፀጉርሽ ፈታትቼ ያልበታተንኩሽ እንደሆነ እኔ አይደለሁም!” እያሉ መሂናቸውን ተደጅ ሊያስገቡ ደንዝዤ እቆምሁበት ጥለውኝ ትሄድ ተከትያቸው ወጣሁና እግቢው መሀ መሀል ቆምሁ በሩ ተጥግ እስተ ጥግ ተበርግዷል ወደ ውጪ ትመለከት ድምጣቸው ሳይሰማ በግራቸው ለመግባት ቲሉ መሂናቸውን ተግቢው ፈንጠር አርገው ነው ያቆሟት ተመመለሳቸው በፊት ተግቢው እንደእብድ እየሮጥሁ ወጥቼ ልጠፋ አሰብሁና ፈራሁ በልሁም ፊቴ ድቅን ቲልብኝ ተመልሼ ወደ ቤት ገባሁ። የሆነውን ሁሉ ታስበው እውነትም ዛሬ ምን ሆኛለሁ ታለወትሮዬ ተሳቸው ጋር ሰጣ ገባ የገጠምሁት ግራ ገባይ። እዛ አስርቱ ትዛዛት እተጣፉበት እጋኔኑ ክፍል ውስጥ የገባሁ ግዜ ተለክፌ ይሆን?። አበጄ ነበር? ባላብድማ እንዲህ ባልለፈለፍሁ “እብድና ዘመናይ የልቡን ይናገራል “አለይ እምዋ….

ይቀጥላል

አስተያየትዎን እዚህ ይስጡ

የኢሜል አድራሻዎ አይወጣም

Loading...