Tidarfelagi.com

ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦18)

እትዬ ተጣጥበው እና ተኳኩለው እንደጨረሱ ተላይኛው ክፍሎች ባንዱ ውስጥ ገቡ። ወድያው አንድ የመሂና ታርጋና መፍቻ ይዘው በመውጣት መሂናቸው ላይ የነበረውን ታርጋ ፈተው ቀየሩት። ተዛ የቀየሩትን ወደ ቤት አስገብተው የጎንዬሽ ገርመም አርገውይ ነይ የውጭውን በር ክፈች አሉይ። የከፈትሁበትን ቁልፍ ተቀብለውይ ተውጪ ቆልፈው ቲሄዱ…
የባእድ አምልኮ ማድረሻ “አቴቴዋን” ተሙዳይ ውስጥ አውጥታ በመጣል ተፈጣሪዋ ዘንድ እንደታረቀይ የቤት እመቤት የሆነ ጋኔን ተላዬ ላይ የወረደ መሰለይ። ትከሻዬን ቲቀለይ ትለታወቀይ እኝህ ሴትዬ ማ እርኩስ መንፈስ የተጠናወታቸው ናቸው አልሁና…በጥድፊያ ምንም ነገር ተማረጌ በፊት ምን ማረግ እንደሚሻለይ እና ምን ማረግ እንዳለብይ ተቀምጬ በጥሞና ታሰላስል ተቆየሁ ቡሀላ…
የመጣው ይምጣ እይ የዛሬውን እድል ተዚህ ሞት ሞት የሚሸት ቀፋፊ ቤት ለማምለጥ ታልተጠቀምሁበት ተበልሁ ቀጥሎ ሞቴን የምጠባበቅ ተንቀሳቃሽ ሙት መሆኔን መቀበል ነው። አልሁና እበልሁ ዘንድ ወርጄ ሀሳቤን ታማክረው ተተቀበለይ ሽቦ ባልተደረገበት እመውጫው በር ስር ተቤት ውስጥ ያሉትን ወንበሮች ፣ ኩርሲና፣ ደንበርካዎይ የተመቸንን ደርድረን በሩ ላይ በመውጣትና ቁልቁል በመዝለል ብንፈረከስም ብንከሰከስም የተረፈውን አካላችንን ይዘን ማምለጥ።በቃ ተይህ በላይ ጥሩ አጋጣሚ ፈጣሪስ ተየት ያምጣልን።አልሁና በተለመደው መንገድ በጠሎት ቤቱ ቁልቁል ትወርድ …
በልሁ ቅድም ያጠጣሁት ውሃ ነብስ ዘራበት መሰል እዛው እታሰረበት ቦታ እጅና እግሩ እንደተወጠረ ሽቅብ ጣራ ጣራውን እያየ ቲያወራ ተመለከትኩ። ድምጡ ግን አልተሰማይም። ወንድሜን እየጠለየ ነው መሰል አልሁና ጠጋ ብዬ በልሁ ትለው…
እንባው ተአይኑ ላይ እየረገፈ በመርፌው ምህንያት የጀመረው ለሀጩ እየተዝረበረበ እንዲ አለይ”አንቺ ነሽ እናት አለም ተላይ በሩ ቲከፈት እንደሰማሁ እኛ እርኩስ ሴትዬ መስለውይ ፈጣሪዬን በኔ ታይበቃ ልኔ ስትል ደግ በሰራች ስለምን እህቴን ታውሬዋቹ እጅ ታልህብይ እያልሁ ወቀሳ ይሉት ልመና ለኔም ታይገባኝ ትለፈልፍ ነበር። እሄን ሰሀን ተሄድሽ ቡሀላ ታየው አንስቼ አልደብቀው ነገር እጅና እግሬ ተጠርንፎ አላላውስ ቢለይ ሽቅብ ማልቀስ ጀመርሁያ ምን ላርግ አምጥተሽ የዘነጋሽው አንቺም አይደለሽ የኔ አለም!” ተተወለድኩ ተሰምቶይ ያላየሁት ሶስት አይንት ስሜት ተሰማይ… የሚያስብልይ ሰው መኖሩ ፣የመበደል እና የስቃይ ስሜት ባንድ ግዜ ውስጤን ተታች ወደለይ ቲገለባብጠው ምን እንደገፋይ እንጃ ተፈናጥሬ እበልሁ አንገት ላይ ተጠመጠምሁበትና አዋ ወንድሜ እኔው ነይ ብትበላልይ ብዬ አምጥቼው ቲያጣድፉኝ እዚሁ ዘንግቼው የሄድሁት እኔም ታሁን ታሁን ገብተው አዩት እያልሁ ትጨነቅ ነው የዋልሁት እትዬ ግን ወዲህ ታይመጡ እጠበቃው ዘንድ ሄደዋል።
ይልቅ አሁን እንድ ነገር ልጠይቅህ በጄ በለኝ የኔ አንበሳ ትለው
“ምንድን ነው? ሰንዬ!” አለይ። ተያይዘን ተዚህ ቤት እንጥፋ አልሁት “አይ ሰንዬ! እነዚህን ሰዎይ ጠንቅቀሽ ያወቅሻቸው አይመስለይም!” እስቲ አይኖችሽን ተኔ ላይ ንቀይና ያለንበትን ክፍል ዙርያ ገባውን በወጉ ተመልከችው ” አለይ።
ታንተ ጀርባ እኮ ጨለማ ነው በልሁ ምኑን ልየው? ትለው እክፍሉ ውስጥ ያለውን ማብሪያ ማጥፊያ በአይኑ ጠቆመይ።አበራሁት። እቤቱን ተጥግ እስተ ጥግ ተመለከትሁና አፌን ይዤ ቀረሁ።እይህ ቤት ውስጥ ትንሽ ቢያስቀምጡይ ማንም ታይነካይ በፍርሃት እንደምሞት ታወቀይ። ቤልሁ ቤቱ በትልቭዥን ያየሁትን ከብቶቹ የሚታረዱበትን ቄራ ይመስላል ልበል ትለው “ልክ ነሽ የኔ አለም ግን ይሄ የከብት ታይሆን ሰዋች የሚሰውበት የሰዋች ቄራ ነው!…..

ይቀጥላል

አስተያየትዎን እዚህ ይስጡ

የኢሜል አድራሻዎ አይወጣም

Loading...