Tidarfelagi.com

ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦17)

እሳቸው ቲጮሁ እኔ እንደፈዘዝሁ በልሁ ጋር ትለረሳሁት ሰሀን ታስብ መላሽ ትላልሰጠኊቸው በሽቀው… ወደ እኔ ይበልጡን በመጠጋት “ያን ሁሉ ሳንኳኳ ምን ስትሰሪ ነበር እያልኩሽ እኮ ነው ብለው ቲያፈጡብኝ ተሄድኩበት ሀሳብ ባነንሁና የባለፈውን እንደመብረቅ ልብ የሚያቀዘቅዝ ጥፊያቸውን ታያልሱኝ በፊት…
ወደ ላይም ወደ ታይም ሲሎት ግዜይ እንደው ቢያረጋጋሎት ብዬ ተሽሮ ፍትፍት ጋር ደባልቄ ፍቱን መፍሀኒት ልቀምምሎ አሰብሁና ለክፍ ቀን ቢሆን ብዬ ማድቤት ቋጥሬ ያስቀመጥኋቸውን ፌጦና ሌሎይ ቅመማቅመሞይ ወየት እንዳስቀምጥኊቸው ትለጠፍቡይ ፍለጋ ትንጎዳጎድ ነው ቲያንኳኩ ያልሰማኆት።ትላቸው…
“ኧረ ባክሽ እውነትሽን ነው ሽሮ ፍትፍት ልታዘጋጂ …ያባቴ አምላክ ይፈትፍትሽ እና…”
የርሶን አምላህ አውቀዋለሁ ያባቶ ደሞ ማን ይሆን “ያባት እዳ ላልጅ” አለች ያገርቤታ ጎረቤቴ።አልሁ በሆዴ መቸም ሆድ በነገር አይሞላ።ቀጥለዋል እትይ…
“አንቺ ምናምንቴሽን ፈትፍተሽ ስትሰጭኝ አምኜ የምቀበልሽና የምበላ ጅል እመስልሻለሁ ”
እህህህም ማመን ትላቆሙ ነው ለካ ተቅርብ ግዜ ወዲህ ምግቦትን እራሶ ማዘጋጀት የዥመሩ “ሌባ እናት ልዧን አታምንም ” አሉ እብዬ ደጉ።
“ምን?ምን?……..ምናልሽ?”
እሺ ይቅርታ ነው ያልሁት እትዬ ሌላ ምን እላለሁ።
ሳሎኑ መሀል ቁጭ ብለው አይናቸውን ወደ ጠሎት ቤቱ ግድም በወረወሩ ቁጥር ቀልቤ አብሮ ቲወረወር ሰቀቀኑ ታይገለኝም አይቀር።
እንዲህ ድፍንፍን ያለ ጭንቀት የወረሰኝ እለት እምዬ ነች ውል የምትልብይ …
“ሰንዬ የኔ ልዥ ታላንቺ ማን አለይ
ያንቺን ክፉ ነገር ቆሜ ተሚያሳየይ
ክፉሽን ያርቀው ወይ እኔን ይውሰደይ።”
ትል ነበር እምዋ ጠጉሬን አልሰራ ብዬ ታስቸግራት እኔን ትታባብለይ ታንጎራጉርልይ ነበር።
እንዬ ዛሬስ እንዣ ተኝህ ክፉ ሰትዬ ማምለጫም የለይ!። ሁሉን ነገር ተደረሱበት መቸም አይኔ እያየ ባውሬ ተምበላ ተያይዘን እናልቃለን እትዬ።
አይ እትዬ እንደው ምን ይሆን እንዲህ ክፉ ያደረጎት ? ነው ሀብት ቲመጣ ክፋትን አስከትሎ ይሆን እንዲያ ተሆነማ ዘንዳ ሁሉም ሀብታም ክፉ በሆነ ነበር።እንደው እኔ ተዚህ ቤት በሰላም ብወጣና ተላይ ተፈቅዶልይ ቢያልፍልይ ክፉ ልሆን ?
” ሰላሳ ቢታለብ ፥ እኔ በገሌ” አለች ውርዬ። ተተፈቀደልኝ በላይ ላልበላና ላልኖር ምን ክፉ አስሆነኝ አረ አልሆንም!።
የትዬ ስልክ አቃጨለ “ሆሎ እሺ እንዴት ነህ ? የፍርድ ቤት ውሎ እንዴት ነበር እዛ አከባቢ ማየት የማልፈልጋቸው ሰዎች ስላሉ ነው ያልመጣሁት። ዛሬ ለምን ምሳ እየበላን አንጨዋወትም? በርግጥ ምሳ ሰአት አልፏል። እሺ በቃ ቁጥር ሶስት። ጠብቀኝ እሺ የኔ ጌታ።”
እትዬ ተቤት የሚወጡት እሄንኑ መከረኛ ጠበቃ ማግኘት ቲፈልጉ ነው።ገና ስሙን ቲጠሩ ነው ተጭንቄ የገላገለኝን ፈጣርዬን ማመስገን የዥመርሁት ነብስያዬ መለስ አለች። ተጭንቄ ብገላገልም ስልኩን ቲዘጉ “የኔ ጌታ” ማለታቸው ግን አብሽቆያል እኝህ አስመሳይ። እኛን ቤተ መቅደስ እንደገባይ ውሻ እያካለቡና ተቆሌያችን እያራራቁ ተሚሆኖት እና ታምሳያዋት ቲያወጉ ሰው አክባሪ ይመስላሉ።
“መሰል መሰሉን ነው ሰው ሁሉ ሚያከብረው!
ቡቱቶ ለባሹን ምንስ ተሰው ለየው?!
መኖሪያችን እንጂ መግቢያችን አንድ ነው!!!
አለች እምዋ!…

ይቀጥላል

አስተያየትዎን እዚህ ይስጡ

የኢሜል አድራሻዎ አይወጣም

Loading...