Tidarfelagi.com

ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦13)

ደምስሮቼ ሁሉ ስራቸውን አቁመው ማን እንደነካኝ ለማየት  አንገቴን ወደ ጀርባዬ ማዞር  ተሳነኝ። የሞትኩ ያህል ትንፋሽና ድምጤን አጥፍቼ  በፍርሀት ተውጬ ትጠባበቅ  ተውሃላ የነካኝ ነገር እዛው እነካኝ ቦታ እንደተጫነኝ አልንቀሳቀስ ቲል  የሞት ሜቴን ዘወር ብዬ ታይ። ተደነገጥኩት ባልተናነሰ ባስደነገጠኝ ነገር በሸቅሁ። “ፍርሀት እና ጭንቀት ቀልቡን የነሳው ሰው  ደንብሮ ይሮጣል ጥላው ቲከተለው።” አለች እምዬ።

እንዲህ ነብስ  እና ስጋዬ እስቲላቀቅ ያስደነገጠኝ ለካ ቁልቁል እያየሁ እትዬ ታሁን ታሁን በልሁ ላይ ተኮሱ አልተኮሱ ገደሉት አልገደሉት እያልሁ  ጭንቅ ይዞኝ ትፈራገጥ በሩን ወድሮ የያዘውን ታኮ በግሬ መትቼ አሽቀንጥሬው ኖሯል በሩ ሊዘጋ ቲጣደፍ መሀል ላይ መቀመጫዬ እንቅፋት ሆንበት እዛው ተደግፎኝ የቀረው። ድንጋጤዬ ታይለቀኝ የትዬ ስልክ አንቃጨለ  “ሁለት ደቂቃ ጠብቀኝ እደውላለሁ ” አሉና እበልሁ አፍ ውስጥ ድምጥ ማፈኛ ብረቱን አስገብተው ወደ ላይ ለመውጣት ቲሰናዱ ተነስቼ ወደ መደበቂያዬ ወደ ላይኛው ክፍል በረርሁ። ቁልቁል ትመለከት እትዬ ወጡና የጠሎት ቤቷን ጉድ ምንም እንዳልተፈጠረ እንደነበረች ሸፋፍነው እንዳበቁ ስልክ እየመቱ ወጡ።

የደወሉለት አነሳው መሰል ሃሎ ” እያሉ የኔን ማደሪያ ገልመጥ  አርገው ወደ ሳሎኑ መሀል እየተጠጉ  “ሻንቆ  ተሳክቷል ታልከኝ ወዲህ መቸስ ችግር ተፈጥሯል አትለኝም” አሉና አይናቸውን አፍጠው ቲያደምጡ ተቆዩ ቡሀላ ምን እንዳለቸው እንጃ ፊታቸው በደስታ እንደ ጠሀይ ሲያበራ አየሁ።  ትገምት  ግን  ጥዋት ባልቸው ላይ  የሚመሰክሩ  ሰዋችን  ሻንቆ እስተ ማታ አንቆ አንደሚያመጣላቸው  ቲያወሩ ነበር ታይሳካላቸው አልቀረም። ተዛ ” ምን ላርግህ የኔ አንበሳ  ክክክክክ  በል ጉራው  ይቆይህና  አሁን የምነግርህን በጥንቃቄ ተግብር።”አሉና “ሰዎቹን ለመያዝ የተጠቀምክበትን  የፓሊስ ልብስና መታወቂያ አቃጥለው፣ አሀኑኑ  ነብሮ  እና  ተኩላ  መኪና  ይዘው  ወደ ሚጠባበቁህ መጋዘን  ውሰዳቸውና  ሴቷን ለነብሮ  ወንዱን ለተኩላው ስጣቸው፣  ለነብሮና  ለተኩላው  መስካሪ ተብዬዋቹ ከአዲስ አበባ  ውጪ የወሰድናቸው  እንዲመስላቸው  እጅና እግራቸውን በገመድ  እንዲሁም አፍና  አይናቸውን በጥቁር ጨርቅ ካሰሩ ቡሀላ እመኪናው ውስጥ በጥንቃቄ በመደበቅ  በተለያየ አቅጣጫ  ቢያንስ እስከ  150  ኪሎ ሜትር ወስደው  በማሳደር  የሄዱበት አቅጣጫ እስኪዞርባቸው ድረስ አዙረው  የት እንደሆኑ  እንዳያውቁ ነገ  ከለሊቱ  ስድስት ሰአት   ያዲስ አበባ ታክሲ ወያሎች  እስቴድየም፣ ሜክስኮ፣ ፕያሳ ፣ አራት ኪሎ  እያሉ የሚያሰሙት ጥሪ ፀጥ ረጭ እንዳለ  ይዘዋቸው  እኔ ጋር እንዲመጡ ጥብቅ ትዛዝ አስተላልፍ ጨርሻለሁ” አሉና  ስልኩን ዘግተው  የኔን  ማደሪያ  ክፍል ከፍተው  ወደ  ምኝታ  ክፍላቸው ገብተው  ተኙ።

ቆየት አልሁና ድምጥ ታላሰማ ወደ ክፍሌ ገብቼ  ተጋደምሁ እንደው እናንተዬ መስካሪዋቹንስ  ባላቸውን ለማዳን ያጥቋቸው  የኔና  የበልሁ  ነው እይ ትርጉም የለለው ሞት። ሁሉን ነግር ታስበው  ጨነቀኝ። የብር ደሀ ብንሆን  የሰው ደሃ አልሆንን  የትና ማንጋ  እንደተቀጠርን  አንድም ሰው  ታያቅ በማናውቀው ደላላ  እንደ በግ እየተጎተትን ታውሬዋቹ ቤት ገባን ዛሬ ማን? የት ? ብሎ ይታደገናል ፈጣሪዬ እባክህ  ተተደገሰልን  ሞት በማውጫህ አውጣን ላንተ የሚሳንህ የለ!

ዛሬ ቀን ቲጥለኝ የረሳኝ መስሏቸው
የዛሬን እያዩ   እንዲህ መክፋታቸው
ቀን ያስታወሰኝ ለት  ፥ የት ይሆን  መግቢያቸው!” አለች የኔ  ደጓ ናት እምዬ  ሆዷን  ሆድ  ቲብሰው …

ይቀጥላል

አስተያየትዎን እዚህ ይስጡ

የኢሜል አድራሻዎ አይወጣም

Loading...