Tidarfelagi.com

ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦ 11)

እንዳልፈጠፈጥ ፈራሁ ቀና ብዬ እራሴን ለማረጋጋት  ሞከርሁ። ጥጉን ይዤ  እምዬ እሄን ጉዴን አላየሽ  እስተዛሬ ታውሬ ጋር አብሬ  ነው የኖርኩት አልሁ ለራሴ።  ትንሽ ተቀመጥሁና  ትንፋሽ ወስጄ መልሼ በሆዴ  ተኝቼ ቁልቁል ትመለከት  የበልሁ ሁኔታ አንጀቴን አላወሰው። እትዬ የ ባእድ  የአምልኮ ጠሎታቸውን ጨርሰው ተነሱ።

በበልሁ ዙርያ እንደ ጦስ ዶሮ እየተሽከረከሩ ….”ስማ አንተ ድሀ ”  አሉና  ታቀረቀረበት በያዙት ሽጉጥ ተአገጩ ወደ ላይ ቀና አደረጉት።

ወይ ወንድሜን አፉ ውስጥ እንደ ጋሪ ፈረስ ብረት ዱለውበታል በንዴት የወንድነት ወኔ እና እልሁ ፊቱ ላይ እየተንቀለቀለ ቲነድ አየሁት።

“እኔ ቤት ከገቡ ሰዋች ለብዙ አመት በሂወት የኖርከው አንተ ብቻ ነህ።ይህ የሆነው ደሞ በጠባይህ እንጂ የዚህን ቤት ብዙ ሚስጥር እንደምታውቅ ስለምናውቅ የኔም የሻንቆም አይን አንተን ከመከታተል  ባዝኖ አያውቅም ሰማህ?”

አንተን ለዚህ ዘንዶ እንዳልገብርህ እንዳንተ አይነቱን ነጫጭባ  አይፈለግም መሰለኝ አላዘዘኝም።

ትናንት ከሰናይት ጋር  ቀኑን ሙሉ ምን ነበር የምታወሩት  እኔን ያናደደኝ ፖሊሶቹ ቤት  ይፈትሻሉ  እናንተ  ቤቱን ጥላችሁላቸው የራሳችሁን  ወሬ  ታወራላችሁ። ይታይሀል  እሄ ከፉትህ እምታየው  ዘንዶ እስካለልኝ  ድረስ  ምንም  እንደማልሆን እወቅ። ስለዚህ ዘንዶ እምታውቀው ነገር አለ ? እ..ምን ታውቃለህ?”  አሉና እንዲናገር አፉ ላይ ያለውን ብረት ቲያነሱለት…

የመናገር እድል የተሰጠው በልሁ እንዲ ብሎቸው እርፍ….

“ቀን  የጣለው  አንበጣ ፥ ይሆናል ፌንጣ”  አለ  ያ…..ገር…ሰው”  እርሶም  ነገ ቀን ጥሎት ፌንጣ  ቲሆኑ  በዛ ሽመል ክርኖን  ብዬ ታልጣልሆት  እኔ በልሁ አይደለሁማ!

እትዬ በበልሁ ንግግር ተናደው  ሽጉጡን አውጥተው አናቱ ላይ እንደመብረቅ ቲያጮሁበት በድንጋጤ ተኝቼ ቁልቁል ተማይበት ተፈናጥሬ ተግድግዳው ጋር  ተላተምሁ። አይ በልሁ እስቲ በይህ ግዜ እንዲህ  ይባላል  ይተረታል  ነው ወይስእትዬን አበሳጭተህ  ተመሰቃየት ቶሎ ለመሞት  መርጠሀል ማለት ነው የኔ ጀግና! እባክህ ክፍ አትናገራቸው   እኔ እህትህ ተዚ ጉድ አወጣሀለሁ ተስፋ አትቁረጥ ወንድሜ ተስፋ አትቁረጥ!  እስቲበቃኝ አልቅሼ  ቁልቁል ትመለከት  በልሁ እና እትዬ ተፋጠዋል። እትዬ ምራቃቸውን እፊቱ  ላይ ለደፉበትና ” ስማ አንተ ብጣሻም ደሃ እኔን ስታየኝ ቀን የሚጥለኝ እመስላለሁ?  እድሜ ለጌታዬ  አሉና ወደ ዘንዶው  ዞረው በመንበርከክ.. ፋብሪካዬ  ስራውን እንዳያቆም የመረጠውን ሰው እገብርለታለሁ ፣የተመረተው ምርት ገበያ ላይ ፈላጊ እንዳያጣ …እሄን በይ ፣እሄን ግደይ፣ እሄን ፍለጭ፣ እሄን ቁረጭ  የሚለኝን ሁሉ አጉድየበት አላውቅም ፣ እሄው እንደምታየኝ በጌታዬ ፍቃድ ተዝቆ የማያልቅ ሀብት  አፍርቻለሁ” አሉና ተዘንዶው ላይ  ፊታቸውን መልሰው  ወደ በልሁ ቲመለከቱ…

በልሁ ቁልቁል እያያቸው …

“የማይበሉት እህል ታፈር ይቆጠራል”  አይበሏትም እትዬ እችን በደሀ ደምና በሰይጣናዊ መንገድ ያከማቿትን ሀብት አይበሏትም ታፈር ቢቆጥሩት  ይሻሎታል  እንዳፈር ይቁጠሩት።”  ቲላቸው መሞት እንደፈለገ ትለገባኝ ውስጤ ክፉኛ ሀዘን ገባው…

እትዬ በንዴት ተተንበረከኩበት ተነስተው ያንን ስሪንጅ ክንዱ ላይ ቲሽጡት በልሁ በሀይል ጮኸ!! ይሄኔ  ቲጮህ እተከፈተው  እበልሁ አፍ ውስጥ የያዙትን ሽጉጥ  እስተ ወገቡ ዶሉት…

ይቀጥላል

አስተያየትዎን እዚህ ይስጡ

የኢሜል አድራሻዎ አይወጣም

Loading...