Tidarfelagi.com

ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦ 10)

ሻወር ቤት ውስጥ ሆኜ ያለሁበት ክፍል ውስጥ ዘው ብለው ቲገቡ እኔኑ የተከተሉኝ መስሎኝ  ወደ ውስጥም ወደ ደጅም ትንፋሽ ማውጣት ተስኖኝ ፀጥ አልሁ።

እሳቸው ግን እክፍሉ እንደገቡ ግድግዳዉ ላይ የተሰቀለውን  ትልቅ ስእል  ተግድግዳው ላይ አወረዱ። ደሞ ቀጠሉና ቀለሙ ተግድግዳው ጋር የሚመሳሰል  እንደ ፕላስተር የመሰለ ነገር ተግድግዳው ላይ ገሽልጠው  ቲያነሱ አይኔ የሚያየውን ነገር ማመን ተስኖት  መርገብገቡን  አቋረጠ።

እትዬ ፕላስተር  የመሰለውን ነገር እንደላጡት ግድግዳው ላይ የቁልፍ ማስገቢያ ቀዳዳ አየሁ።

ቁልፉን ከተቱና ቃ….ቅቃ  አድርገው  በመክፈት ጎተት ቲያረጉት  ተከፈተ።

እህን ግዜ  እንደ ቁም ሳጥን በተከፈተው ግድግዳ ውስጥ ያየሁት ነገር ሁለመናየን ከፋፍቶት መደበቄንም አስረስቶ ምራቄን አስዋጠኝ። እንኳን በውኔ በህልሜ እንኳን አይቼ የማላውቀው የብር አይነት እና መአት ትመለከት ያለሁበት ቦታ ባንክ ቤት ይሁን መኖሪያ ቤት ተምታታብኝ።

ደሞ ቀጠሉና እንደ መሳቢያ የመሰለ ብረት ተውስጥ ጎትተው ውስጡ  ተተሰደሩት ሽጉጦች እያነሱ ቲያማርጡ እሄ ነገር በፊልም ይሁን በገሀድ እትዬ ቤት  በራሳቸው  በትዬ እየሆነ ያለው  ነገር  ይበልጡ  ግራ ገባኝ እኝ ሴትዬ ምንድን ናቸው? ….የቤት እመቤት ናቸው ወይስ ነብሰ ገዳይ ማፍያ  አልሁ ለራሴ።

ተዛ ቀጠሉና ተሽጉጡ መሀል  አንዱን መርጠው  እካፓርታው የውስጥ ኪስ  ተሸሸጉ ቡሀላ አንድ ትልቅ ስሪንጅ ተነ መርፌው እና ፈሳሽ የያዘ  ትልቅ ብልቃጥ አወጡ ።ትለ  ስሪንጁ  ተጠየቃችሁኝ እኔ ገጠር እያለሁ ከብት ቲወጋበት ታየሁት ስሪንጅ ጋር አንድ አይነት ነው። ተዛ ውጪ ታምሜም የታመመ ላስታምምም እሆስፒታል ታንዴም በላይ ሄጃለሁ  በይህ አይነት መርፌ ሰው ቲወጉ አይቼ አላውቅም። የሚፈልጉትን ነገ በሙሉ ተያዙ ቡሀላ እንደነበረው መላልሰው ተክፍሉ ቲወጡ እንደው የሚሰለቡብኝ መስሎ ትለተሰማኝ  ቀልቤን መግዛት ተስኖኝ ደረጃውን ወርደው ታይጨርሱ ተመታጠቢያ ቤቱ ወጥቼ ተከተልካቸው  እና በር ላይ ቆሜ ቁልቁል ቲወርዱ ተጀርባ ሆኜ እያየኻቸው ሰተት ብለው ወደ ጠሎት ቤቱ ገቡና  ጠሎት ቤቱ ውስጥ ያለውን ወፍራም የወለል ምንጣፍ በጥንቃቄ እየጠቀለሉ ጥግ አስያዙት ።ተዛ በርከክ ብለው ተወለሉ ላይ አንድ ነገር ሳብ አደረጉና ጫን ቱሉት ወለሉ ላይ የለው በርና  የኔው  አፍ እኩል ተከፈቱ ።

ቁልቁል በተበረገደው በር እግራቸውን አስቀድመው  እይኔ እያየ ሁለመናቸው ወደ ውስጥ ቲገባ  የተከፈተውን አፌን መዝጋት ተስኖኝ ፈዝዤ   ደንዝዤ   ለደቂቃዋች አፍጥጬ ተቆምኩ ቡሀላ

ነብሴ መለስ እንዳለችልኝ እራሴን አበርትቼ ተቀስታም በተንቀረፈፈ አካሄድ  ድምጤን አጥፍቼ  ቁልቁል ደረጃውን ወርጄ እንደ ጨረስሁ  ወደ ጠሎት ቤቱ ተጠጋሁ ።  ልቤ ድብደባዋን አናረችው  ተጠጋሁ  ።በሩ ላይ ደረስሁ በርከክ አልሁና ወደ ውስጥ ተጠጋሁ  ወደ ውስጥ ለማየት ግን ፈራሁ እንደምንም   ጥላዬ እታች እንዳይታያቸው  መላ አካሌን እወለሉ ላይ አስተኛሁና  በትንሹ  በትንሹ ብቅ ብዬ ቁልቁል ትመለከት..

እታች ባለው  ቤት  ውስጥ  እትዬ የብረት ፍርግርግ ውስጥ በኩራት ለተጋደመው ዘንዶ ቲሰግዱ  እየሁ  ።ትንሽ ፈቅ ብሎ ደሞ  ሰውነቱ በሙሉ  ልብስ መቆንጠጫ በሚመስሉ ትንንሽ ብረቶች  የተወረሰው  በውስጥ ሙታንታ እንደቆመ  እግርና  እጁ ጥግና ጥግ ተቆመ ብረት ላይ ታስሮ  አፉ እንደተለጎመ ቁልጭ ቁልጭ እያለ የሚመለከታቸውን  የኔን ሚስኪኑን በልሁን ታየው እዛው በተኛሁበት እራሴን ስቼ ቁልቁል  ….ይቀጥላል

አስተያየትዎን እዚህ ይስጡ

የኢሜል አድራሻዎ አይወጣም

Loading...