Tidarfelagi.com

ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦28)

ተሽጉጡ መሀል አንድ በቁመቷ ዘለግ ያለችውን መረጥሁ። አይኔ ሽጉጦቹ ታሉበት መሳቢያ ውስጥ ጥግ ላይ እተቀመጡት ነገሮይ ላይ አረፈ። ትዝ ይለኛል የዛሬ ሶስት አመት አከባቢ ታይሆን አይቀርም። ቡና እያፈላሁ ነበር ጋሼ እትዬን እንዲህ አላቸው ” ሀገሪቱ ውስጥ ያለው ሁኔታ ጥሩ ትላልሆነ እኔን ማጥቃት የሚፈለጉ ሰዎች አንቺን ሊጎዱሽ ይችላሉና እሄን ነገር ለጥንቃቄ እንዲሆንሽ ላሳይሽ” ብለው ለትዬ ትለሽጉጥ አጠቃቀም ቲያስረዷቸው ፈጣሪ ለዚህ ቀን ቲያሰናዳኝ ነው መሰል እኔም ተትዬ እኩል በትኩረት ነበር የተከታተልኋቸው። እቺን ነገር ምን ነበር ያሏት እቴ? አዎ ድምጥ ማፈኛ ነው መሰል ያሏቸው።ሽጉጡ ቲተኮስ ድምጡ ጎልቶ እንዳይወጣ ያደርገዋል እንዳሉዋቸው ትዝ ቲለኝ ተመሀል አንዷን አነሳሁና እሽጉጡ አፍ ላይ ከትቼ ታሽከረክራት ግጥም አለይ። በ…..ጀ ! አልሁና የሽጉጡን መሳብያ መልሼ ተላይ የቁም ሳጥን ግማሽ የሚያህለውን በር ትከፍተው በቴሌቭዥን ያየሁት አይነት የነጮቹ ብር እንደ ሀገሬ ተራራ ተቆልሏል። ኤድያ አልሁና መልሼ ዘጋሁት እንኳንስ እንዲህ በሞት እና በሂወት መሃል ሆኜ በደናውም ግዜ ቢሆን ደሀም ብሆን ሌብነትን እንድጠየፍ አድርጋ ነው ያሳደገችይ እምዋ። አይዞት እትዬ ገንዘቦትን አልነካም።

ደሞ ለጠቅሁና ሌላኛው መሳቢያ ትከፍተው መጠናቸው እና አይነታቸው ብዙ አይነት የሆኑ ጩቤና ሴንጢዎይ ተደርድረዋል። ተመሀል አንዷን አነሳሁና እጎኗ ላይ ያለውን እባጭ ጫን ትለው መጋዝ የመሰለ ክርክር ያለው ስለት ተውስጧ አፈትልኮ ወጣ መልሼ ትጫነው ወደ አፎቷ ተመለሰይ ይህቺ ለአያያዝም ምቹ ነይ አልሁና እሷንም ያዝኋት።

በስተግራ ጥግ ላይ ያለውን መሳብያ ትከፍተው መድኒት ይሁን መርዝ በየአይነቱ በብልቃጥ ፣ ሲርንጆይ፣ ፋሻ እና አልኮሎይ ተሰግስገዋል ተመሀል አንድ ጥቅል ፈሻ ወሰድሁና መልሼ ዘጋሁት ተመሳቢያዋቹ ተላይ ያለች ክዳና በብረት የተሰራችው ግን ትጎትታት አልከፈት አለችይ። ተዛ እጄ ላይ ታሉት ቁልፎይ መሀል እየቀያየርሁ ትሞክር አንደኛው ቁልፍ ከፈተልይ። ውስጧ የሀገሬ የወርቅ መጋዘን እስትትመስል ድረስ በተለያዩ የወርቅ ጌጦይ ተጨናንቃለይ መልሼ ዘጋኋትና ሁሉንም ነገር መልሼ እንደነበረው ታስተካከልኩ ቡሃላ ያወጣሁትን ሽጉጥ ሴንጢ እና ፋሻ እጠረቤዛው ላይ አኑሬ በፍጥነት ወርጄ ቁልፉን ላሻንጉሊቷ መለስሁ።

መልሼ ሽቅብ ወጣሁ። ተንበረከክሁና  ጠሎት ጀመርሁ።ፈጣሪዬ ሰው መግደል ሃጥያት ነው እንዳልህ አውቃለሁ። ግን እንደኔ አረዳድ ተሆነ ሰው ሰውን የገደለው ጦር ሜዳ ተሆነ ተሀጥያት አይቆጠርም ለምን ታልከኝ ጦር ሜዳ ሰው መግደል ስራ ትለሆነ። እይህ ቤት ውስጥ እየሆነ ያለው ነገር ደግሞ ተጦርነትም በላይ ነው። ምህንያቱም እኔና በኔ ወገን ያሉ ሚስኪኖይ ትለ ጦርነቱ ታናውቅ ፥ታንሰናዳ፥እንደነሱ ታንታጠቅ ድንገት እጦርነቱ መሀልገብተን መውጫ እና ማምለጫ ትላጣን ላለመሞት እይ ለመግደል ትለማንዋጋ ለኔ ይህ ተጦርነትም የከፋ ነው። ትለዚህ ፈጣሪዬ የኛን የኔን የበልሁንና የልጁቱን ነብስ አተርፍ ዘንፍ እኔ ሃይልና ጉልበት ባይኖረይም ለወገኖቼም ለሀገሬም ጠንቅ ተሆኑት ተነዚህ አውሬዎይ መሀል ቢያንስ አንደኛቸውን እንኳን ተምድረ ኢትዬጲያ ታልቀንሳቸው እንዳልሞት እርዳኝ!። በነዚህ ሰዎይ በሚስኪኖይ ላይ የሚደርሰው ስቃይ እና ሞት በኔ እና በበልሁ እንዲበቃ አንተ ተከተለኝ።

ተፊቴ ላይ እንባዬን እየጠራረግሁ ፋሻውን ተግራ እጄ ክንድ ላይ ጠቀለልሁና ሴንጢዋን ወትፌ ልብሴን ሸፈንሁት።ሽጉጡን አነሳሁ። እትዬ ስራዬን ልጨርስና አንቺን እሸኝሻለሁ ነበር ያሉኝ ዛሬን በሂወት ታደሩ ልክ ኖት። ዛሬን ታለፉ እንኳንስ ለበልሁ ልተርፍ እኔም ያበቃልያል።አሁን ሸኝው ማን እንደሆነ ይለያል፣ስራዎን ጨርሰው ወደ ክፍሎት ገብተው እነደተኙ ሁሉም ነገር ያበቃለታል። እትዬ ተታች ወጥተው እስቲመጡ አድፍጬ ትጠባበቅ ልክ ተለሊቱ 8 ሰአት ላይ በጠሎት ቤቱ ብቅ አሉ…….

ይቀጥላል

አስተያየትዎን እዚህ ይስጡ

የኢሜል አድራሻዎ አይወጣም

Loading...