Tidarfelagi.com

ኢትዮጵያ ቅኝ ገዢ፤ ኤርትራ ነፃይቱ ምድር¡

ትልቅ ስላቅ ነው። ኢትዮጵያን የኤርትራ ቅኝ ገዢ አድርጎ መሳል ከጥንት እስከ ዛሬ ድረስ ያለህን የታሪክ፣ የማህበረሰብ፣ የባህል፣ የሀይማኖት፣ የስነልሳን ሕብረቀለማትን መካድ ነው።

Why we buried the distant history we lived in?

ጥንት፡-
ደአማታውያን፣ አክሱማውያን ሀገርን በሚመሩበት ዘመን “ባህረ ነጋሽም (የአሁና ኤርትራም) የታላቋ ኢትዮጵያ የመሬት እና የውሃ አካል ነበረች።

ህዝቦቻም የጥንቷ ኢትዮጵያ (በተለይም ደግሞ ደጋማው ክፍል ውስጥ) በሀወርታዊ የተገነባ ነበር። ዛሬም ይህ እውነት አብሮ ከኛ ጋር ነው። ቤጃው፣ አገው፣ ትግረ፣ አዳሉ፣ ወሎው እና በሌላው የተገነባ ነበር።
ባህረ ነጋሽም የዳአማታውያን፤ የአክሱማውያን ማዕከል ነበረች። የያኔው የንጉሳውያን የፓለቲካ፣ የኢኮኖሚ እንብርት ነበረች። በተለይም ደግሞ ነገስታቱ ከባህር ማዶ የሚያስገቡትን እቃዎች የሚያስገቡበት በር፣ ወታደራዊ ግዳጅም የሚወጡበት ምድር እና ውሃ ነበረች። እንዶቻቸውን ተቀብለው (በተለይም ሮማውያን እና ፋርሳውያን) እንደ ሀገር ሰው ይራመዱበት ነበር።

ባህረ ነጋሽ (የአሁና ኤርትራ) ከማዕከላዊው መንግስት “ልዩ” አስተዳዳሪ ይመደብላት ነበር። የጥንቶቹ ኢትዮጵያውያንም ((አቢሲንያውያንም) )ሥዩመ ባህር ይሉት ነበር።

የመሬቱን፣ የውሃውን፣ የህዝቡን፣ የፀጉረ ልውጡንም ዳና “በጥበብ” እንዲመሩ። የጥንቱ ባህረ ነጋሽ ወዳጅ ብቻ ሳይሆን ጠላትም የሚገለፅበት ምድር ነው። አረቦቹ፣ ግብፃች፣ ቱርኮች ምድሩን እና ውሃውን የራሳቸውን ለማድረግ ብዙ ለፍተዋል። ጦር ሰብቀው፣ የመርከብ መልህቁን ሊጥሉ ታትረዋል። ድል በብዙ ለኢትዮጵያውያን ብትገብርም።
የያኔው ዘመን ህዝብም ከመሀል አገር ወደ ባህረ ነጋሽ በንግድ፣ በጦርነት እና በባርያ ንግድ ምክንያት ይጋዝ ነበር። ንግዱ እና ለጦርነት የተመመው ህዝብም ኑሮውን በኤርትራ አድርጎ ህብረ-ብሄራዊነትን በባህረ ነጋሽ እንዲመሰረት ምክንያት ነው። ኤርትራም የኢትዮጵያ የብዝህነት ናሙና አድርጋታል።

ስለዚህ በሀገረ መንግስት ግንባታው ውስጥ የኢትዮጵያዊነት ማህፀን አንዱ ክፍል ኤርትራ ነበረች። ኢትዮጵያም አንገታን ለ 1889 አመታት በክብር ጠብቃለች።

ባህረ ነጋሽ ወደ ኤርትራነት ተቀየረች፡-
ጣልያን የቅኝ ግዛት ረሀባን ምላሽ ለመስጠት ወታደራን፣ የእሳት ጥይታን አርግዛ ከቀይ ባህር ደረሰች። ዳህላክ ደሴትን ብቻ፣ የኢትዮጵያን ሰሜናዊ ጫፍን ያዘች። መረብ ምላሽ በጣልያኖቹ አስተዳደር ወደቀ። በመሀል ሀገር በተለይም በሸዋው፣ በትግሬው እና በጎጃም አስተዳዳሪዎች መሀከል የነበረው የስልጣን ትግል ለዳር ሀገሩ፣ የኢትዮጵያ አንገት በጠላት ጎራዴ እንዲመታ ምክንያት ሆነ።

ጣልያንም ባህረ ነጋሽን ስሙን ቀይሮ “ኤርትራ ኮሎኒ” ብሎ ጠራው። ከሶማሊያ፣ ከሊቢያ ግዛቱ ጋር ደምሮ በአፍሪካ ምድር ሶስት ሀገራትን ለመግዛት አለመ። ሀገረ ኢትዮጵያን ለመቆጣጣርም መንደርደሪያውን ከባህረ ነጋሽ ሊያደርግ አሰበ። ኤርትራንም ለስራ አጥ ጣልያኖች መኖሪያ፣ በሶማሊያ እና በሊቢያ ለሚኖራው የጦርነት አዋጅ ምልምሎች የሚያገኙበት ምድር ነበር።

ይኽ እውነት ለ 50 አመታት ታይታል። ከዚያም በእንግሊዝ የ 10 አመት የሞግዚት አስተዳደር ስር “የእናት ኢትዮጵያ አንገት” ኤርትራ (ባህረ ነጋሽ) አንቀላፍታለች። ((The conspiracy of the center to periphery politics was visible at that time))
ፋሽሽቶቹ ቅኝ ገዢዎች በዚህ ዘመን ክርስቲያን ሙስሊም፣ ደገኛ ቆለኛ እያሉ ሊያለያዩት ሞክረዋል።
እንግሊዞቹ ደግሞ የራስህ ባንዲራ አለህ እና ሀገር አለህ ብለውታል ከእናት ሀገሩ እና ከራሱ ጋር እንዲጣላ። ይህ ሁሉ ቅስቀሳ ቢኖርም ከእንግሊዝ የሞግዚት አስተዳደር ብኃላ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት አማካኝነት የተቆጠረው ህዝባዊ ድምፅ በፌዴሬሽን እና በአንድነት እንኑር ያለው ህዝብ ከመቶ ብዙ እጅ ነበረው። (ያ ሁሉ ታሪክ ሆናል))

በኢትዮጵያ የተፈፀመው፣ በኤርትራ አንድ ናሙና ነው፡-
ንጉሶች ሀገሩ፣ ህዝቡ፣ ንብረቱ የራሳቸው ነበር። ሥዩመ እግዚአብሄር ነን ብለው በደሉን አዝንበውታል። የወደዱትን ሹመዋል፣ የጠሉትን ቆርጠዋል። ሰለሞናዊው፣ ሶሻሊስቱም (ህብረ ብሄራዊ እና የአንድነት ሀይሎቹ) በህዝቡ ላይ የእሳት አሩር አዝንበዋል። ህብረ ብሄራዊነት ተዘንግታል፣ አሀዳዊ መንግስት ነግሳል፣ ህዝብ ለመንግስት እንደ አንድ ንብረት ነበር። ነገስታቱ፣ መኳንንቱ፣ ምስለኔዎቹ ማር፣ ወተት እና ጮማ በልተዋል፤ ጠጥተዋል። ህዝብ ተርባል፣ የጦርነት ማገዶ ሁናል፣ ቀንበር በህዝብ ላይ ሁናል። ስለዚህ ጠላትነቱ ከአስተዳደሩ ጋር ነበር ማለት ነው። ((በደሉን በጋራ ከተጋሩት አንዳቸው በሌላቸው ላይ አዛዥም፤ ታዛዥም አልበሩምና))

ሁሉን እናፍርስ ያሉት ልጆች፡-
በኢትዮጵያ የጭቆና ዘመን እንዲያልፍ አዲስ “ህብረ ቀለም” ያላት ሀገርን ለመገንባት ብዙ ተብላል። ብዝህነትን ያማከለ እና ህዝቦች ራሳቸውን እንዲያስተዳድሩ “ህብረተሰባዊ መፅሀፎች” እንደ ዳዊት ተደግመዋል።
ህብረ ብሄራዊ ድርጅቶች፣ ብሄርተኛ ንቅናቄዎች በመሬት ለአራሹ፣ ራስን በራስ ከማስተዳደር ዘይቤ እና ከኤርትራ ጉዳይ ጋር ተያይዞ ብዙ ወረቀቶችን ፈጅተዋል። ብዙ ድምፃችም በአደባባይ ተለፍፈዋል።

የአንድነት ሀይሎቹ “የኢትዮጵያ ብሄሮች” ጥያቄ ሲፈታም የኤርትራም ጥያቄ አብሮ መልስ ያገኛል። የነፃነት፣ የዲሞክራሲ እና የወንድማማችነት (የእህትማማችነት) ፀሀይ ለኢትዮጵያ ሲወጣ፣ ለኤርትራም አብረው ይወጣል ብለዋል። ችግሩን አብረው ተሸክመው ለኢትዮጵያ እና ለኤርትራ ሁለት ድስት መጣድ አስፈላጊ ነው ብለው አላመኑም።

ብሄርተኞቹ ቡድኖች ግን “ኢትዮጵያ” ብሄረሰቦችን የገዛች የቅኝ ግዛት ኢምፓየር አድርገው ያስቀምጣታል። ሀገር አሀዱ ተብሎ ሲገነባ የነበረውን ምድር ቅኝ የተገዛ ነው ብለው ይፈተፍታሉ። በባህል፣ በቋንቋ፣ በኑሮ፣ በስብጥር በአንድ ደጅ የሚውለውን ህዝብ “ገዢ እና ተገዢ አድርገው” ይሄትታሉ። ከታሪክ እና ከእውነት ጋር ስታጋጭ ራስህን ትክዳለህ። ጀብሃ፣ ሻዕቢያ፣ ህወሀት፣ ኦነግ የዚህ ትርክት አቀንቃኝ ናቸው። (ሀገሬ ሆይ ክፉ ልጆች ከተወለዱ ቆዩ! የኔ ዘመን ልጆች ግን ከታላላቆቹ ይብሳሉ።))
ኢትዮጵያን፣ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እና “አማራነትን” ጠላት አድርጎ የተነሳው “አብዮታዊው ትውልድ” ብሄርተኛ ትርክትን አስቀደመ። politically constructed reality. Where is the objective reality? It sediments deep into the history we passed on.))
ለዚህ አላማው በርሃ ወረደ፣ አመታትን በመታኮስ አሳለፈ፣ ማዕከላዊ መንግስትንም አሸነፈ፣ በልጅነት የተማረከበትን እውቀት በፌዴሬሽን፣ በዲሞክራሲያዊ እና ፕሮለተሪያት ህብረተሰባዊነት መልስ ለመስጠት አላማረጠም። እንኳን ኢትዮጵያና ኤርትራ ቀርቶ ኬንያ፣ ጅቡቲ፣ ሱዳን፣ ሶማሊያ ጭምር የአፍሪካ ቀንድ አንድ ሀገር መሆን ያስችላቸዋል። ንግዱ፣ ጦርነት፣ ህዝባዊ እንቅስቃሴዎች ተመሳሳይ ነገዶችን፣ ጎሳዎችን፣ ህዝቦችን እንዲጋሩ በአይን የሚታይ እውነት ይዛልና።

ከእናት ሀገር ኢትዮጵያ ጋር ካለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዋሀዳለን ያሉት፣ ከኢትዮጵያ ጋር በፌዴሬሽን እንኖራለን የሚሉት አማራጮች አልተነበቡም። ከነፃነት እና ከባርነት የሚለው “የፓለቲካ አንኳሳ ምርጫ” አሸነፈ። ሀቲንግተን እንደሚለው የፓለቲከኞች ፍቃድ ሀገርን ይሰራል ያለው ሀሳብም በኢትዮጵያ ምድር ሁለት ሀገራት እንዲኖር አደረገ። የነፃነት ቀንም እያሉ አከበሩ። ከታሪክ፣ ከህዝብ ጋርም ተጣሉ።

“መለሎ ቁመና ሸንበቆ አንትሽ፣
ከቶ ወዴት ገባ ያ ሰውነትሽ?”

ዛሬ፡-
ኢትዮጵያን የብሄር ብሄረሰቦች እስር ቤት ነው ያለው ሀሳብ ሀገሩን አሰፍስፎ ሊበላው ጭራውን እና ቀንዱን በአደባባይ ያሳየናል። ትናንት ልጅ ከእናታ ተለይታብናለች። ዛሬ ልጆች በእናታቸው ላይ ተነስተዋል።
ይኽን ሀገር አፍራሽ ሀሳብ ማሸነፍ አለብን። ከሀገር የበለጠ አንድም ሀብት የለንም። ዘፋኙም ሀገር ያህላል ከፍ ያለ ፍቅር ብላል። ህዝቦቻ በአንድነት፣ በእኩልነት፣ በፍትህ የሚኖሩባትን ሀገር ለመስራት እናልም።
አለምም ካለ መኖር ወደ መኖር የመጡ በመሆናቸው። ሀገርም ከሀሳብ የተወለደ የሰው ስራ ስለሆነ፣ ሀገር ለመስራት እንነሳ። ኢትዮጵያ የተስፋይቱ ምድር እና ዮቶጵያዊነታን እንድትገልፅ እኛ ልጆቻ “በዘመነ” መንገድ እንጓዝ።

አስተያየትዎን እዚህ ይስጡ

የኢሜል አድራሻዎ አይወጣም

Loading...