Tidarfelagi.com

ቲቸር ጥጋቡ

አበበ በሶ በላ ….ጫላ ጩቤ ጨበጠ …ቲቸር ጥጋቡ …… ››

የአስራ ሁለተኛ ክፍል ስፖርት አስተማሪያችን ጋሽ ጥጋቡ እንደዛን ቀን ተበሳጭቶ አይተነው አናውቅም ! ሁልጊዜ ሰኞ በመጀመሪያው ክፍለጊዜ ‹‹ስፖርት ›› ነበር የምንማረው ! ታዲያ ወንዶቹ ሁላችንም ደስተኞች ነበርን ! ሴቶቹ ግን ክላሱን አየወዱትም ! ምክንያቱም ቅዳሜና እሁድ ፀጉራቸውን ተተኩሰው ጥፍራቸውን በጥፍር ቀለም አስውበው ‹‹ዩኒፎርማቸውን›› አጥበውና ተኩሰው ሰኞ አበባ መስለው የሚመጡት ሴቶች እዛ ሜዳ ላይ ‹‹ተኙ ተንከባለሉ ሩጡ ዝለሉ ›› ሲባሉ ውለው ፀጉራቸው ተንጨባሮና ሳርና ሌላም ሸቀጥ ተሸክሞ ላብ በላብ ሁነው ሰኟቸውን መጀመር አስከፊ አይፈልጉም ነበር !
እንደውም አንዳንዴ ስፖርት ላለመስራት ‹‹ቲቸር ማንስትሬሽን ላይ ነኝ›› ብለው የሚያስፈቅዱ ሴቶችን ‹‹አ……ይ በየሰማንቱ ነው እንዴ የእናተ ….›› ብሎ ይቆጣቸዋል ! በእርግጥ ቲቸር ጨካኝ አልነበረም ግን የሴቶች ስፖርት መጥላት ያበሳጨው ነበር! አንድ ቀን ታዲያ ‹‹ እራስን ከአደጋ መከላለከል ›› የሚል የማርሻል አርት አንድ ክፍል የሆነ ትምህርት እያስተማረን ነበር…. ትምህርቱ ስለሚያዝናና በተለይ ወንዶቹ ደስ ብሎን ነበር የምንሰራው ! ተሰልፈን ያ….. ሄይ….. ሁ እንላለን ! ሴቶቹም ድምፃቸውን ቀንሰው ኤጭ ! ይላሉ !
‹‹ ለምሳሌ ጩቤ የያዘ ሰው አይኑን አፍጥጦ ሊያጠቃችሁ ፊት ለፊታችሁ ቢቆም ምን ታደርጋላችሁ ›› ብሎ ጠየቀን ቲቸር
‹‹መጀመሪያ አማትባለሁ ›› አለ ፍቅረ ማርቆስ ሁላችንም ሳቅን
‹‹ደህና ድንጋይ ፈልጌ እፈነክተዋለሁ ›› አለ ታደሰ የሚባል የክላሳችን ልጅ
‹‹ አግሬ አውጭኝ ብሎ ፈትለክ ነው ወደኋላ ›› ይላል ሌላው ! ቲቸር ግን እንዴት ጩቤውን አንደምናስጥለው በምሳሌ አንድ ልጅ ወደፊት አስወጥቶ አሳየን ! ቲቸር ‹‹ለምሳሌ የሚሆን አንድ ሰው ወደፊት ይምጣ እስኪ ›› ሲል ሁላችንም ፈርተን ዝም ነበር ያልነው ቲቸር ራሱ አንዱን ጠራው እና ተማሪውን እስክርቢቶ እንደጩቤ አስይዞ አንዴት ማስጣል እንደሚቻል አሳየን !
‹‹ በመጀመሪያ ሊያጠቃችሁ የመጣው ሰው እንኳን ጩቤ ጎራዴ ቢየዝ እንዳትፈሩ እንዳትደነግጡ ተረጋግታችሁ አያያዙን ተመልከቱ ‹ አያያዙን አይተህ ጭብጦውን ቀማው › አይደለ ተረቱ ….ከዛ እንዲህ እጁን አንጓው ላይ በፍጥነት ትይዙና ወደግራ እጁን ጠምዝዛችሁ …..ልክ እንደዚህ ያ …ሁይ ›› ብሎ ለምሳሌ የወጣውን ልጅ መሬት ላይ በጀርባው ዘረጋውና እና የያዘውን ቢክ እስክርቢቶ አስጣለው ! ቲቸር ጎበዝ ነበር ! (‪#‎በነገራችን‬ ላይ ዱርየወች ቲቸርን ማታ ላይ በጩቤ አስፈራርተው ላፕቶፑን እንደቀሙት ቆይቶ ዩኒቨርስቲ ከገባን በኋላ ሰምተናል ‹የአህያ ባል ከጅብ አያስጥልም› )
ቀጥሎ ሴቶች እራሳቸውን ከጥቃት እንዴት እንደሚከላከሉ ማስተማር ጀመረ
‹‹ ሊሊ ››
‹‹የስ ቲቸር ›› አለች ሞልቃቃዋና ቆንጆዋ የክላሳችን ልጅ ›› የሊሊ ቁንጅና መቸም ተአምር ነው በቃ ተአምር !
ቲቸር ቀጠሉ ‹‹ለምሳሌ አንድ ወንድ አስገድዶ ሊደፍርሽ ቢሞክር እንበል ….››
‹‹ኦ ማይ ጋድ ›› አለች ሊሊ ቲቸር ሳይጨርሱት ቀድማ !
‹‹ ምሳሌ ነው …እንዴት እንደምትከላከይው በምሳሌ እናያለን ….›› ብሎ ሊሊን ወደፊት አስወጣትና ወደእኛ ዙሮ ‹‹ እስቲ አንድ ወንድ እንደሊሊ ደፋሪ ሁኖ ምሳሌውን የማሳይበት ሲል ›› ሁላችንም ወንዶቹ እጃችንን አውጥተን ወደፊት ተንደረደርን ! እንዴ ሊሊ ጋር ለምሳሌም ቢሆን መደፋፈር ፅድቅ ነበር ለእኛ ! ሊሊ እኮ ነች ! በተለይ እንዲህ ጥብቅብቅ ባለ ታይትና በጃፖኒ ቁማ ጡቶቿ ተቀስረው አስተማሪው ‹‹ኑ ድፈሯት ›› ሲል ማን ሞኝ አለ አርፎ የሚቆም ዘራፍ ! ምን ያደርጋል ‹‹ ተውት በቃ እራሴ አሳያችኋለሁ ›› አለና ኩም አደረገን ቲቸር !እግዜር ይይለት ! ‹‹….ምን አይነት ነገር ነው ተማሪ ተኮር ነው ትምህርቱ አልተባለም እንዴ ሁሉን ነገር አስተማሪው ብቻ ….›› ብያለሁ በሆዴ !
ቲቸር ሜዳው ላይ በጀርባው ተኛና ..‹‹ አሁን እኔ ደፋሪ ነኝ አንች ነይ እግርሽን ክፈችና ከላየ ሆዴ ላይ ውጭ ›› አላት
‹‹ እንዴ ቲቸር አልወጣም !›› አለች ሊሊ ፊቷን አጨፍግጋ !
‹‹ለምንድነው የማትወጭው››
‹‹ ከመቸ ወዲህ ነው ሴት ከላይ ሁና የምትደፈረው ›› አለች ሊሊ
‹‹ነይ ዝም ብለሽ ውጭ ››
‹‹አልወጣም ››
‹‹ ነግሪያለሁ ውጭ ››
‹‹እኔም ነገርኮዎት አልወጣም ቲቸር ደግሞ ከላይ ሁኖ መደፈር አለ እነ….ዴ …… ሆሆ ››
‹‹ከላይ ሆንሽ ከታች ምን ለውጥ አለው ››
‹‹ ከላይ ከሆንኩማ ‹ኦልሬዲ› እራሴ ፈልጌ ነው ማለት ነው !! ምኑን ደፈራ ሆነ ቲቸር አልወጣብወትም ›› ብላ ቲቸር እንደተንጋለሉ ትታቸው ወደቦታዋ ተመለሰች !
ቲቸር በጣም ስለተበሳጩ ሊሊን ወላጅ አስጠሯት ! ወላጆቿ ቲቸርና ሊሊ የትምህርት ቤታችን ርእሰ መምህር ጋር ቀረቡ
ቲቸር የሊሊን ጥጋብና አስተማሪ መናቋን አስረዱ ….ሊሊ በበኩሏ ‹ሴት ከላይ ሁና ስትደፈር ታይቶም ተሰምቶም እንደማይታወቅ አስረዳች › የሊሊ ወላጆች ግራ ተጋብተው ዝም አሉ ….በመጨረሻም ርእሰ መምህሩ ውሳኔያቸውን አሳልፉ !
‹‹መምህር ጥጋቡ…. መቸም አንተ ምስጉን መምህራችን መሆንህን ማንም ያውቃል….. በሙያህም ጣልቃ መግባት የለብኝም ቢሆንም ተማሪወችን በሚወዱት መንገድ ማስተማር የተሸለ ትምህርቱን እንዲረዱት ያደርጋልና ካሁን በኋላ ከላይ ሁነህ በመድፈር አስተምራት …አንችም አርፈሽ አደፋፈሩን ተማሪ አንድ ቀን ይጠቅምሻል ›› ሲሉ ሸኟቸው !!

አስተያየትዎን እዚህ ይስጡ

የኢሜል አድራሻዎ አይወጣም

Loading...