Tidarfelagi.com

“ቤንዚን አይወጣበት-ነዳጅ አይቀዳበት-ነቲንግ!”

/እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በላይ ለሆኑ ብቻ/

ከጥቂት ጊዜ በፊት በዘመኑ የኣራዶች መስፈርት <ደረጃ 1> የሆነች አንድ ሞዴል ቺክ ጋር <ዴት> አደርግ ነበር…እንደዋዛ ተዋውቀን እንደዋዛ መገናኘቱን ደጋገምነውና ብዙም ሳንቆይ እንደዋዛ አልጋ ላይ ተገኘን…መቼስ በጊዜኣችን ፍቅሩም ፀቡም ስኬቱም ውደቀቱም እንደ መቶ ሜትር ሆኗል…የዘጠኝ ሰከንድ ዘመን!…ሩጫው ዘጠኝ ሰከንድ…እንግሊዝኛው በዘጠና ቀን…የስኬት ዘጠኙ መንገዶች…ሴትን ልጅ በዘጠኝ ደቂቃ የማማለል ጥበብ…የመሳሰሉት…ወዘተርፈ

እና በዚያ ሰሞን ካልኳችሁ ልጅት ጋር በሰላም አምሽተን እንዲሁ በሰላም አደርን…ጧት ስንለያይ የዴቲንግ ጉዳዮች ሃላፊዬ የሆነው ሊንከን ጋር ደውዬ ከልጅቷ ጋር ስላለፈው ምሽት እና አዳር አጭር ሪፖርት አቀረብኩ…ሊንከን በዴቲንግ ስነልቡና ላይ አ.አ.ዩ. አፕሩቭ አያርገው እንጂ የዶክትሬት ዲግሪ ያክል እውቀት እንዳለው ሁሉም የመሰከረለት ከባድ ጀለሴ ነው…በጥሞና ካዳመጠኝ በኋላ አንድ ጥያቄ ወረወረ…

<እኔ እምልህ…እና ነገርየው ተፈፀመ?>

<አይ የለም…አልተፈፀመም> ድምፄን አለሳልሼ መለስኩ

<ለምን?> ቁጣ ባዘለ ድምፅ ሌላ ጥያቄ ተከተለኝ

በዋዛ እንደማይለቀኝ ገባኝ…<ያው እንደምታውቀው እኔ ከጋብቻ በፊት እንዲህ አይነት ብልግና የማድረግ ፍላጎት የለኝም> ብዬ ላስቀው አሰብኩ…ያም ሆኖ ቁጣውን ለመስበር በቂ መልስ ሆኖ አላገኘሁትም…ትንሽ ቆይቶ ሌላ ሃሳብ መጣልኝ

<እሷ እንድናደርግ ፈልጋ ነበር በርግጥ>

<እና አንተ ምን ቆርጦህ ስታንኮራፋ አደርክ?>

<እ….ምን መሰለህ ሊንከን?…ፔሬድ ላይ ነበርኩ>

ስቆ ይፋታኛል ስል ቁጣው ብሶ አረፈ…ለምን መርፌና ክር ሳንሆን እንዳደርን እየደጋገመ ጠየቀኝ…ምክንያቶቹን በርግታ አንድ ሁለት ብዬ አስረዳሁት…ሊዋጥለት አልቻለም…<እማትረባ ነህ> አለኝ…የአለም ዋንጫ ላይ የመጨረሻው ጨዋታ የመጨረሻ ፔናሊቲን እንደሳተ ሰው ውሻ አረገኝ…ይሄኔ እኔም ብልጭ ብሎብኝ ያኔ መንግስቱ ሃ/ማርያም ስለ ኤርትራ መሬት ሲጠየቅ እንደመለሰው ያለ መልስ መለስኩ

<ጀለሴ አስገድደህ ድፈራት ነው እንዴ እምትለኝ?…አሁንስ አበዛኸው…ቆይ ይሄን ያህል የሷ ቀዳዳ <ቤንዚን አይቆፈርበት-ነዳጅ አይወጣበት-ነቲንግ!!!> >

እስኪ ዛሬ የጓድ በውቄን ሌጋሲ ለማስቀጠል ያስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እስኪነሳ ድረስ ስለ ወሲብ እየተማማርን እንቆይ…<ዊርድ> እሚሆንባችሁ ጀለሶቻችን ግድ የለም ስለ ትዳር እና ልጆች አስተዳደግ እስክንፅፍ ድረስ ጥቂት ዞር ዞር ብላችሁ ተመለሱ…እኔና ቤቴ ግን <ሰም አማውንት ኢዝ ሄልዚ> ብለን እናምናለን…አምነንም እነሆ እንፅፋለን!

<ወዳጅ ያዝናል እንጂ መች አብሮ ይሞታል?>

መፅሃፉ <ድሃ እንዳትሆን እንቅልፍን አትውደድ> ይላል…ሳስበው ሳስበው ቅዳሜ ቅዳሜ መለኪያዋን ይዤ <አለም ዘጠኝ ነው> እያልኩ ቁልጭ ብዬ እማነጋው ለዛ ነው መሰለኝ…በርግጥስ መፅሃፉን ካልሰማሁ ማንን እሰማለሁ?

ከበዙ ሸግዬ ቅዳሜዎች ባንዷ ቅዳሜ ቦሌ አካባቢ ባንድ <ዋሌት አራጋፊ> ክለብ ከጀለሶች ጋር አምሽተን ነበር…የቆምንበትን ቴብል እሚጋሩን የቦሌ ቀበጦች የሞቅታ ጣሪያቸው ላይ እስኪደርሱም ሁሉም ነገር ሰላም ነበር በ’ውነቱ…ኋላ ላይ ግን ከጀለሶቼ አንዱ እንዲያው ሳይቸግረው ካንዷ ባለ ጭን ጋር ግብግብ ነገር ጀመረ…ባላዬ ላሽ ማለቱ ሼም ሆኖብኝ ላገላግል በገባሁበት አንድ የነብር አራስ የሆነ መጠምሻ ጋርድ መሃላችን ላይ ተገኘ…ነገርዬው አላምረኝ ሲል በስልታዊ ማፈግፈግ ፕሪንሲፕል ለምን ሽንቴን ቼክ አላረግም ብዬ ወደ ቶይሌት ዞር አልኩ…በዚህ ቀውጢ ሰኣት በዚህ ኩንታል ጋርድ እጅ ብወድቅ በመዳፉ አሸት አሸት አርጎ እንደ ዝቃቅቤ ባፍንጫው ሊምገኝ እንደሚችል አውቃለሁ…ደግሞስ ሃይል የእግዚአብሔር አይደለምን?

የኋላ የኋላ ግን ዚፔን ከፍቼ እየዘጋሁ <አት ዘ ሴም ታይም> የጀለሴን እጣ ፋንታ ሳስበው ትንሽ አዘንኩኝ…የከሃዲነት ስሜት ሊወረኝ ስል ወዲያው የጥንቱ ባለ በገና የጋሽ ታፈሰ ግጥም ደረሰለኝ…ታፌ ማኛ <ወዳጅ ያዝናል እንጂ መች አብሮ ይሞታል> እሚሉት ነገር አለ…የሞተም የተረፈ እንዳለ ብዬ ወደ ሳሎን ተመለስኩ…ጀለሶቼም ጋርዱም በቦታው የሉም…ወደ ውጭ ወጣሁ…እንደበሰለ ቲማቲም ሊፈነዳ የደረሰ ፊት አየሁ…የባለ ጡንቻው ቡጢ ያረፈበት የጀለሴ መልክ ቻይና ሙድ እንደያዘበት የሸገር መንግዶች ተቦዳድሷል…ምንም እንዳላዬ ሰው ሆንኩና የሚይዘኝ ደግ ወዳጅ አላጣም ብዬ ያዙኝ ልቀቁኝ አልኩ…ዳሩ ግን በዚያ እኩለ ሌት በስፍራው እሚይዝም እሚለቅም የለም…ሳላስባንን ወደ ጀለሴ ተመልሼ ደገፍገፍ አርጌ ታክሲ ውስጥ ጨመርኩት…ወደ ማደሪያችን ስንሄድ ጀለሴ <በሴት የላከው ጅብ አይፈራም> ብሂል የደረሰበት ጥቃት አብግኖት እንዲህ እያለ ነበር

<ወይ ቀዳዳ…ለዚች ቀዳዳዋን ማንም ለሚሳለመው ቀጫጫ እንዲህ ጉንጬ ይቀደድ?…እስኪ ቆይ እኔ ምን ማድረግ ነበረብኝ…በዛ ቅፅበት <ሞደፊክ ሆል> አላሰራ…እኔ እድሜ ልኬን የህይወቴን ቀዳዳ ለመድፈን ስታትር የኖርኩ አመድ አፋሽ!>

እለቱን ስቄ አለፍኩት…የኋላ ኋላ ግን ሳስበው ሳስበው የቀዳዳ ነገር የዋዛ እንዳልሆነ ነው የገባኝ…በዙሪያዬ በሰራትሁ አንድ ጥልቅ ጥናት ጉዳዩ የሶስተኛው አለም ጦርነት መንስኤ እንዳማይሆን ማስተማማኛ እንደሌለ ሁሉ ደርሼበታለሁ…አንዳንዴ ውብ እንስት ሆኖ መገኘት የሚሊዮን ብር <አሴት> ሁሉ ይመስለኛል…ጨዋታን ጨዋታ ያነሳዋል…የሆነ ጊዜ ላይ አንድ የከተማችን ከበርቴ ጉራጌ አስገድዶ በመድፈር ወንጀል ፍርድ ቤት መጥቶ ነበር…ወራትን ከፈጀ ክርክር በኋላ ፍርድ ቤቱ ባለ ቂንጬውን የሞት ፍርድ ለቀቀበት…ሰውየው በጣም አዝኖና ልቡ ተሰብሮ ከችሎት ሲወጣና ሌላ ጉራጌ ጀለሱ ወደፍርድ ቤቱ ሲደርስ አንድ ሆነ…<ውይ ውይ ወንዴሜን ወንድሜን ምን ፈርደውብህ ነው እንዲህ አንገትህን የደፋህ?>…ጀለሱ ጠየቅ…እጁን በካቴና የታሰረው ፍርደኛ በሰለለ ድምፅ መለሰ

<ሞት>

<ውይ ተመስገን!ተገላከልካ ጠንክርዬ…እኔማ የገንዘብ ቅጣት ጣሉብህ ብዬ ከባድ ሃሳብ ገብቶኝ ነበር>

የወሲብ ተንከሲስነት በልጅነት ነው እሚጀመረው…ያኔ የወንደላጤዎች ዶርም በር ላይ ባለች ቀዳዳ አጮልቀን ስናይ ነው ያደግነው…ነገሩ ባይገባንም ድምፅና ጭንቀቱ እልህና ትግሉ ያዝናናን ነበር…ከሼቦቹ ጋር በጉዳዩ ዙርያ በሚደረጉ ልቅ ወጎች መሃልም ሳቅ የፈጠሩ የህፃናት መልሶች አሉ

<አቡሽዬ…አባትህ እናትህን ማታ ማታ ያረጋታል?>

<እና እራቷን በልታ ይቀርላታል?>

በሉ መልካም ቅዳሜን ተመኝቼ ልሸብለልላችሁ…ከዛ በፊት ሰሞኑን ሳይበር አካባቢ መጥፋቴ አሳስቧችሁ በኢንቦክስ በስልክ እና በአካል እየመጣችሁ <ጠፋህ..ምነው?> ያላችሁኝ እጅግ በርካታ ወዳጆቼ…/በርግጥ ወግ ለማሳመር ነው እንጂ አንድ ሰው ነው የጠየቀኝ/…ይሄው ተመልሻለሁ…<ቅዝምዝም እና ክፉ ጊዜን ጎንበስ ብሎ ነው ማሳለፍ> ይላሉ አበው…ከ1888ቱ በላይ ከባድ ውጊያ እሚነሳበትን የዘመናችንን የአድዋን የታሪክ ጦርነት ሽሽት ጠፍቼ ሰነበትኩ…ለማናቸውም ተመልስናል!

መልካም ቅዳሜ!

#ሰላም_ለሰው_ልጆች_ሁሉ_ይሁን!

It’s not about me! it’s not about my life situation either.It’s about life! And in life I trust!

One Comment

  • mekonnendawit5@gmail.com'
    Dawit Mekonnen commented on March 23, 2017 Reply

    Hey i Appreciate i like your way of Writing please keep it up & keep going!

አስተያየትዎን እዚህ ይስጡ

የኢሜል አድራሻዎ አይወጣም

Loading...