Tidarfelagi.com

በኅዳር ውስጥ እኔን

(የነፍሴ ክስ)

ተወው!
ቆሻሻህን ተወው 
ከሳቱ ዳር እራቅ
ጭለማን ልበሰው
ጥቁር ካባ ደርብ
ዓይንህ ይጨልመው።

ግዴለህም ተወው
እቤትህ ግባና
ዓይንህን ጨፍነህ
ስላሳመምካቸው
ስላቆሰልካቸው
ነፍሳት አስብና
ራስህን ክሰስ
ራስህን ውቀስ
ራስህን አጥን
ተረማመድበት በንፁሀን ፋና።

የነፍስህን እድፍ
የውስጥህን ጉድፍ
ከዓመት እስከ ዓመት ውስጥህን በክሎት
ዙሪያህን አውኮት
ከዓመት እስከዓመት ተጠራቅሞ እያየህ
ምን ለማቃጠል ነው
በማን ለመታየት
ኅዳርን ለማጠን እደጅ መገኘትህ።
….
ማጠን እራስን ነው
መንፈስን ለማንጻት
ልቦናን ለማጽዳት
ቅዱስ ሰው ለመሆን
እኩይ ምኞቶችን ማቃጠል በእሳት።

የለበስነው ያልፈተልነው
የለቀምነው ያልዘራነው

አለ … አለ…አለ
ይኼንን ነው ማጽዳት
ይኼንን ነው ማንጻት።

(እንዳለጌታ ከበደ፣ልብ ሲበርደው፣2000)

አስተያየትዎን እዚህ ይስጡ

የኢሜል አድራሻዎ አይወጣም

Loading...