Tidarfelagi.com

በባህሩ እና “በባህር ዳር”መካከል…

በባህሩ እና “በባህር ዳር”መካከል…
(የዘረኝነት መንቻካ ልብሶችን እናጥባለን!)

ባህሩ ውስጥ ነኝ:: እልፍ ሰዎች ከባህሩ ወጥተው ዳር ላይ ተኮልኩለዋል:: ጥንት ዳሩ መሀል ነበር:: አሁን ዳሩ ወደ መሀል ገብቷል!
ባህሩ ሰውነት ነው:: የባህሩ ዳር ዘረኝነት- የሰውነት ደረቅ መሬት!
ባህሩ ውስጥ ነኝ:: ባህሩ ደስ ይላል! ቡዙዎች ከባህሩ ወጥተዋል:: ባህሩ ዳር ውሃ አጥተው ደርቀዋል:: “ኑ ከባህሩ እንውጣ” ተባብለው የሚጠራሩ ሞኝ አሶች!

አንዳንድ አሶች አዳብቴሽን ላይ ጥሩ ናቸው:: ከዳሩ አየር ተስማምተው “ኑ እዚህ ደስ ይላል”ሲሉ ይቀሰቅሳሉ:: (ያልዳኑ ሰባኪዎች! መጀመሪያ ይድኑ ዘንድ በባህሩ ይጠመቁ- በሰውነት ፀበል ይንፁ!!)
እነሱ ግን ይህን አይደፍሩም:: ከዛ ይልቅ የኛ የባህርተኞች ሰላም ያበሽቃቸዋል:: ድንጋይ እየወረወሩ እርጋታችንን ያንቦጫርቁታል:: ያንቦጫርቃቸውና!
አሁን ለባህር ድንጋይ ምኑ ነው?

ባህሩ ደስ ይላል! ከባህሩ ዳር ጭቅጭቅ ይሰማኛል::
ባህሩ ጠበበን ብለው ከባህሩ የወጡ “የባህር ወንበዴዎች” ናቸው:: ጭቅጭቁ ደስ አይልም! ድርስ ከሰውነት ወጥቶ ሰውነት ደስ ሊል ነው?

ጥጃዋ ገመዱን በጠሰች:: የራሷ ጉዳይ በራሷ አሳጠረች:: ከባህር የወጡስ ማንን ጎዱ? …………..ተመልሷል!

እኛ ባህር ነን:: ከባህራችን የትም አንሄድም:: ዳር ዳር አንልም:: ዘረኝነት ይጠበናል! ኸረ ቀድሞውንም አንለካውም!!

እነሆ ልብሳችሁ በዘረኝነት ምንችክ የመነቸከባችሁ ሆይ ልቡሱን ወደ ባህሩ ጣሉት!
አምጡት በባህሩ እንጠብላችሁ::
እናንተ ሰውነታችሁ የቆሸሸ ወደ ባህሩ ኑ!

የራስ ናቸው፡፡ የማንንም ሃሳብ ለመፃፍ አልተከፈተም! የሚያስማሙንን ሃሳቦች እዚህ ካገኛችሁ እሰየው፡፡ ለመስማማት አንፅፍም፣ ለመፃፍ አንስማማም፡፡ ወዘተ

አስተያየትዎን እዚህ ይስጡ

የኢሜል አድራሻዎ አይወጣም

Loading...