Tidarfelagi.com

”በሥጋና በግብረስጋ ቀልድ የለም”

ዜና እናሰማለን፤ ዜናውን ከማሰማታችን በፊት ኣካባቢውን በስጋት ዞር ዞር ብለን እናያለን!
ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ለሚያደርጉት ጉብኝት ጥንቃቄ ሲባል የቦሌና ያካባቢው ነዋሪዎች ሽሮሜዳ እንዲሰፍሩ ተደረገ፡፡
President Barak Obama, welcome to the land of fair and free erection!
ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የሸገር ቄራዎች ድርጅት ዋና ስራኣስኪያጅ ኣቶ ተክለማርቆስ ፤ ሰሞኑን የተከሰተው የስጋ እጥረት በቂ ቢላዋ ባለመኖሩ የተከሰተ መሆኑን ገለጹ፡፡ ኣያይዘውም፤ ኣርብቶ ኣደሩ የተትረፈረፈ ከብት በማምረት ያሳየው ትጋት ፤ ቀጥቃጮች በቂ ቢላዋ በማምረት እንዲደግሙት ኣሳስበው፤እስከዛው ድረስ ግን የኢትዮጵያ ህዝብ ከሃይማኖት ኣባቶች ጋራ በመተባበር ተጨማሪ ጦም እንዲያውጅ ኣሳስበዋል፡፡
ለማንኛውም ቶሎ ቶሎ ብላችሁ ችግሩን ይቅረፍ ፡፡ በሥጋና በግብረስጋ ቀልድ የለም፡፡ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ስጋ ጠግቦ ሳይበላ በትራፊክ ኣደጋ መሞት የለበትም፡፡
ጎበዝ ኣማራጭ የፖለቲካ መስመር ባይኖረን እንኳ ኣማራጭ ምግብ ይኑረን እንጂ፡፡እዚህ ውሃ ልማት ግድም“ ኣሹ ስጋ ቤት” እንደሚባለው ሁሉ፤” ኣሹ በያይነቱ ቤት- ስንግ ቃርያም ይገኛል” የሚል ምግብ ቤት ለማየት እናፍቃለሁ፡፡“በእውቄ በጣም ስለማከብርህ የባቄላ ንፍሮ ልጋብዝህ እፈልጋለሁ” ብሎ የሚደውልልኝ ሰው ማግኘት እመኛለሁ ፡፡

ያገራችን ሰው ለጥራጥሬ ያለው ጥላቻ በጣም የከረረ መሆኑን የምታስረዳ ተረትና ምሳሌ ኣለች፡፡እንዲህ ትላለች፤
ከቤት ክፉ ሰቀላ
ከሰው ክፉ ዲቃላ
ከእህል ክፉ ባቄላ
እኒህና መሰል ኣባባሎች በኛ ቬጂተርያኖች ላይ ሲደርስ የነበረውን ግፍና ጭቆና ማሳያ ናቸው፡፡ይህ ጭቆና ካልተሻሻለ ጥቅል ጎመናችንን ይዘን የራሳችንን መንግስት ለመመስረት እንገደዳለን ፡፡ካርታችን ከካዛኪስታን እስከ ካዛንችስን የሚዘረጋ ቢሆንም እንደጠላቶቻችን ድክመትና ጥንካሬ እየታየ ሊሰፋም ሆነ ሊጠብ ይችላል፡፡
2
የሚከተለው ኣንቀጽ” ግብረስጋና ትጥቅ ትግል“ ከሚለው የጓደኛየ የምኡዝ ማስታወሻ የተቀነጨበ ነው፡፡
የኢህኣሠ ወታደሮች በሰሜን ኢትዮጵያ በምትገኝ ባንዲት ገጠራማ መንደር ውስጥ ከላይ የደርግ ኣረር ከታች የወያኔ ጥይት ሲያንገበግባቸው ውለው ሲመሽ ወደ ኣንዱ ገበሬ ቤት ጎራ ብለው ጥገኝነት ይጠይቃሉ፡፡ገበሬው ተቀብሎ ስምንት ታጋዮችን እንደ እንቁላል በጭድ ጉዝጓዝ ላይ ካስተኛቸው በኋላ ወደ ምኝታ ቤቱ ይገባል፡፡ገና ከመግባቱ ኣጓዛ የለበሰ መደብ ላይ ሰፍራ ያገኛትን ሚስቱን እንደጠመዥቆሎ ያሻት ጀመር፡፡ኣይ ኣበሳ!
የኢህኣሠ ታጋዮች ከዚያኛው ክፍል የሚመጣውን የማቃሰት ድምጽ ሲሰሙ፤ ከካርል ማርክስ ትንተና ያመለጠ የመደብ ትግል እየተካሄደ መሆኑን ገምተዋል፡፡ሳቃቸውን ለማፈን ሲገላበጡ፤
”ጓዶች ኣልተኛችሁም እንዴ?“ኣለ ገበሬው ስርያውን ኣቋርጦ፡፡
ጭጭ ኣለ ያትውልድ፡፡
”እንግዲህ ኣይካፍሉት ነገር፤ምን ማድረግ ይቻላል?“ ኣለና ወደ ወዘፈው ስርያ ተመለሰ፡፡

Bewketu Seyoum (Ge’ez: በዕውቀቱ ስዩም) is an Ethiopian writer and poet from Mankusa, northwest of Addis Ababa.

11 Comments

 • ዘበርጋዉ commented on December 20, 2015 Reply

  በጣም አሪፍ

 • ሚኪያስ ወጋየሁ commented on June 11, 2016 Reply

  በጣም አሪፍ አሪፍ ቀልድ ነዉ፡፡

 • Abate commented on July 15, 2016 Reply

  ቆንጆ ነዉ በጣም ይመቻል

 • www.yodnegu@gmail.com'
  yeabtsega negash commented on July 30, 2016 Reply

  የበዕዉቀቱ መድብሎች በትንሹ ቀልድና በብዙ ቁም ነገር የታጀቡ ናቸዉ በአካል ባገኝህ ደስ ሊለኝ ይችል ነበር በጣም በርታ

 • ከድር commented on March 15, 2017 Reply

  ዋዉ፡

 • fikadezerga@gmail.com'
  fikade commented on March 24, 2017 Reply

  ይመችህ ይመቻል

 • dagi commented on May 19, 2017 Reply

  ምርጥ ነዉ በጣም አስቂ አድርገዉ

 • endala commented on July 16, 2017 Reply

  እንዳሌ

 • አለማየሁ ፍቅሬ commented on July 23, 2017 Reply

  ጥሩ ነው

 • shark commented on June 6, 2018 Reply

  dena kelde atekel dum

 • TETEKA commented on September 13, 2019 Reply

  ጥሩነዉ

አስተያየትዎን እዚህ ይስጡ

የኢሜል አድራሻዎ አይወጣም

Loading...