Tidarfelagi.com

“ስለ ቅዳሜ ሲባል ስለ ‘ሁድ ካወራን ተሳስተናል!”

እኔን መምከርና መርገም አሪፍ የስተርጅና ጊዜ መደበርያ ከሆነለት ከፋዘር ጋር እንደተለመደው ሶስት ከባድ የምክር እና የተግሳፅ ሰኣታትን አሳለፍኩ።እንዳረዛዘሙ አመታትን ብል ይቀለኛል ለነገሩ።የማዘርን ጉሽ ጠላ በላይ በላይ እየነፋ፣የአተላውን ግርድፍ በላዬ ላይ እየተፋ መጠጥ እርም እንድል ካልተሳሳትኩ ለመቶ አስራ ሰባተኛ ጊዜ ዛሬም መከረኝ።ዛሬ ግን እንደወትሮው ልቤ አልደነደነም።የፋዙ ልመና ተሰማኝ መሰለኝ፣ከሱ ስፋታ ከባባድ የቅዳሜ ጀለሶቼን አገኘኋቸውና

<<ኧረ እናንተ ልጆች ጨጓራና ብራችን በቢራ አለቀ።የማዘርን ሻሜታ እየነፋን ፍራንክ እንቆጥብ።እቁብ እንጣል።ብሎልን ቤት እንኳን ባንሰራ ቢያንስ ለጂም እንኳን ከፍለን እስኪ ፑሽ አፕ እንስራ>>…አልኳቸው።

በአድናቆት አጨብጭበው…

<<ኤላ ማኛ¡እልል ያለ ፀዴ ሃሳብ አመጣሽ…<ቢራ እናቁም፥ገንዘብ እንቆጥብ> አሪፍ!..ግን ለምን ይቺን ጉዳይ በሰፊው ጃምቦ እየነፋን አንወያይባትም?>> ብለው አፋፍሰው ካዛንቺስ ወሰዱኝ።አንድ ሁለት መባል ተጀመረ።ሰአቱም ነጎደ።ጢምቢራችን ዞረ።ሃሳብ እና ቤት ተቀየረ።
.
ለምን እንደሆን ባላውቅም ከስድስተኛ ጃምቦ በኋላ እንግሊዝኛ ኑሮ እና ጅንጀና ይቀለኛል።<You know what…>…እያልኩኝ አፌን እከፍታለሁ።ለኔ በፈረንጅ አፍ ለሌላው <ለሚሰማኝ> እንደ ፓስተር ዳዊት በልሳን አወራለሁ።

“Who cares after 6 beer?”

ኦንሊ ዘ ዌይተርስ!…ካላችሁ…ትክክል ናችሁ!
.
የቺክም ነገር እንዲሁ ነው።አንድ ሁለት ካልኩ በኋላ አደገኛ <ፕላይ ቦይ> እሚወጣኝ ነገር አለ።እትት ብትትው ይሆንለኛል።

አሁን መች ‘ለት…

ዲያስፖራ፣ነጭ እና ዲታ በማይጠፋበት ባንድ የቦሌ ማምሻ እኔና ጀለሶቼ ዘጠና ዘጠኝ ነጥብ ዘጠኙን ቺስታ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ወክለን ተሰይመንላችኋል።ከጎኔ በስፋት የማዘርን ምጣድ እሚያስከነዳ ፒዛ የያዘች እኔ ነኝ ያለች ብራንድ ቺክ ተቀምጣለች።እነ ታዴ በጥቅሻ አቀሳሰሩኝ እና ወሬ ጀመርኩ።

<Hey,ቆንጆ,whatsup?>

ከግር እስከራሴ በመጠየፍ ተመልክታኝ ባላዬ ላሽ አለች።በልቧ

<ደሞ ይሄ የማን ወጠጤ የድሃ ልጅ ነው ባካችሁ?> ያለችም መሰለኝ።

<ማነው ወጠጤ?ማነው የድሃ ልጅ አንቺ?>

ሳላስበው ካፌ አመለጠኝ።ሞቅ ሲለኝ እንደ ደብተራና ጠንቋይም ይሰራራኛል።ወዲያው ወደግራዬ ግድም ከበድ ብሎኝ ቀና ብል ምን እሚያክል ወመኔ ነጭ ቆሞ እያየኝ ነው።

<ዋው ፈረንጅ!>

<Who the fu*k is this fu*ked up guy baby?>

ጠየቀችው። ምንም አልመለሰም። የደረትን ኪሴን ብቻ በሁለት ጧቱ ይዞ አነሳኝና እንደ አሎሎ ወርዋሪ ከጀለሶቼ ጋር ደባለቀኝ።ቤቱ በእልልታ ደመቀ። ከትንሽ እስከ ትልቁ ሁሉም አጨበጨበለት። ጀግና ጀግና አሉት። እኔ ያገራችሁ ልጅ ግን ወዲያው በማንነታችን ላይ የተቃጣ ብሄራዊ የመደፈር ስሜት ወረረኝ እና የቢራ ጠርሙስ ይዤ ያዙኝ ልቀቁኝ አልኩ።ከየት ተወርውሮ እንደደረሰ መድሃኔኣለም ይወቅ። ገላጋዮቼን ሁሉ ገነጣጥሶ መጣና ከፊቴ ቆመ።በሸሚዜ ኳሌታ ወደ ላላላላላይይይይይ ካንጠለጠለኝ በኋላ

“What the fu*k do you want from me?” አለኝ።

ሲር ሲር በሚል ድምፅ መለስኩለት።

“please ground me ground me sir, can we talk?”

“What for bitch?” አምባረቀብኝ።

እንደምንም አጣጥሬ መለስኩ።

“I want to improve my English language”

ቤቱ በሳቅ ፈረሰ። እግዜር ይስጠውና እሱም ከዚ በላይ አልጨከነብኝም። እኔን መሬት አውርዶኝ ሲያበቃ ያገራችንን ቆንጆ ይዞ ከቤቱ ወጣ።

የተጨማደደ ሸሚዜን እያስተካከልኩ ቀና ስል አይኔ ዲያስፖራዎቹን እሚያጫውት አንድ አዝማሪ ጋር አረፈ።
ተቀበል አልኩት። ተቀበለ።

<አንቺም ሂጅ ግድየለም ወደ ፈረንጆቹ
ለኛም እግዜር አለን ለጥቋቁሮቹ>

ድገመው!
ድገመው!
ድገመው በናትህ!
.
እንደሆነው ሆኖ ይነጋል።ጀሴሶቼ ሼም አልባ ናቸው።በጧት ወደ ቸርች <እጠበኝ ቆሽሻለሁ>ን ከፍተው ስፒከሩን እያስጮሁ እንሄዳለን።ነጭ ከለበሱ ምዕመናን ጋር ተቀላቅለን እንገባለን።ስንወጣ ይስቃሉ።

<ምን ተገኘ?> ስላቸው

<በቃ ያደረው ሃጥያት ሁሉ ፎርማት ተደርጓል። ዛሬ አዲስ ቀን ነው። ፈታ በል ይሉኛል።>

ድምፄን ከፍ አድርጌ <ፈታ!> እላለሁ።
.
የቴዲ አፍሮን ሰምበሬን ከፍተን ሰፈር ወዳለችው ግሮሰሪ ሩጫ። ምላስ ሰምበር ይታዘዝና እንበላለን። የጀበናውን ቡና እንደቀመስኩ ዞር ስል ጃምቦው መጥቷል።

<ጠጣ!ዛሬ አዲስ ቀን ነው> ይሉኛል።

<አይሆንም> እላለሁ።

ወዲያው ጥላኝ ስለኮበለለችው ልጅ እያነሱ ብሶቴን ይነካካሉ። ጀለሶች አይደሉ….ደካማ ጎኔን ያውቋታል።ያኔ <ጃምቦ ይቅርብን፥አልኮል ካልሆነ> እላለሁ።
.
ወደ ኮማሪው ዞር ብዬም ሙዚቃ እመርጣለሁ።

<ስለ ቅዳሜ ሲባል ስለ ‘ሁድ ካወራን ተሳስተናል>
.
በሉ ይመቻችሁ!
መልካም ቅዳሜ!
መልካም እሁድ!

It’s not about me! it’s not about my life situation either.It’s about life! And in life I trust!

One Comment

  • ture commented on September 2, 2017 Reply

    Keep up the good work!!!!

አስተያየትዎን እዚህ ይስጡ

የኢሜል አድራሻዎ አይወጣም

Loading...