Tidarfelagi.com

እስቲ ስለ ራስሴ

እስቲ ስለ ራስህ ትንሽ ንገረኝ ባልሽኝ መሰረት ራሴን በትህትና እንደሚከተለው አስተዋውቃለሁ🙂

አነጋገሬ የሰለጠነ
አረማመዴ የተመጠነ

ስደሰት ፊቴ :የግዚሀር ባውዛ
ስስም ከንፈሬ : ያበባ ጤዛ!!

ካለት ያወጋሁ
ከንብ የተጋሁ
እንደ ዘንገና : ውሃ የረጋሁ
ከጎህ ቀድሜ : ባይንሽ የነጋሁ።

ባስብ በመላ-ብናገር እውነት
ባቅፍሽ ክንዶቼ -የሃር መቀነት።

ጣትሽ ደባብሶኝ : ጥፍርሽ ቢበጣኝ
ዘቢብ ነው እንጂ :መች ደም ሊወጣኝ።

ለምድር ቢቀርብ- ቁመቴ ቢያጥር
በጎልያድ ግንባር- የማነጣጥር
ልቤ በጣቱ -ሰማይ ሚነካ
ከነራስ ደጀን- ከንጦጦ የካ
ቁመት በኩራት- የሚለካካ

ብትደገፊኝ -የላባ ፍራሽ
ብትመገቢኝ- የመና ቁራሽ።

እንኳን በጃኖ: እንኳን በሱፉ
እንደ ቁጥቋጦው : ልክ እንደዛፉ
ቅጠል ለብሼ :የምሽቀረቀር
የተለጋ ልብ: ቀልቤ ማስቀር

ያንቺው በረኛ
ያንቺው ቁንን ነኝ :ያንቺው ጉረኛ።

Bewketu Seyoum (Ge’ez: በዕውቀቱ ስዩም) is an Ethiopian writer and poet from Mankusa, northwest of Addis Ababa.

አስተያየትዎን እዚህ ይስጡ

የኢሜል አድራሻዎ አይወጣም

Loading...