Tidarfelagi.com

ሠማየ ውድውድ (ምዕራፍ፡፩)

ሥሙ፥ከቤቱ፡የወጣ፡ሰው፥የሕይወቱ፡አግጣጫ፡የሚያመራበትን፡በኩል፥እርሱ፡እራሱ፡ባለቤቱ፡እንኵን፥ሙሉ፡ለሙሉ፡ያውቀዋል፡ለማለት፡አያስደፍርም።
`ዝና`፡እና፡`ተዐዋቂነት`፥በምንም፡ዓይነት፥ሰበብ፡እና፡አስባብ፡ረገድ፡ቢመጡም፥የሚደርሱበት፡ደረጃ፡ከደረሱ፡በሗላ፥ከተጠሪው፡ግለሰብ፡አቅም፡እና፡ቁጥጥር፡ውጪ፡እንደሚጕዙ፥
ቀድመው፡የሚረዱት፥ማስተዋልን፡የታደላቸው፥ጥቂት፡በለስዎች፡ብቻ፡ናቸው፡~*ዦሮ፥ለባለቤቱ፡ባዳ፡ነው*፥እንደ፡አሉን፡ሁሉ፡አበው።

ታድያ፡ነገር፥እኔም፡ደማሙ፡ወገናችሁ፥ይኸንኑ፡መሰል፡ሕይወት፡መግፋት፥ዕጣዬ፡ሆኖብኝ፥እንደ፡አቅምኪ፥በደራሲነት፡ሙያዬ፥በጀርመን፡ራዲዪ፡በማስተላልፋቸው፡ተረክዎቼ፥
በኢትዮጵያውያን፡አድማጮቼ፡ዘንድ፥መጠነኛ፡የሆነ፡ዝናን፡በማትረፌ፥ኣሜሪካን፡ሐገር፡ነዋሪ፡በሆነችው፥የወጣትነት፡ዘመን፡ሴት፡ፍቅረኛዬ፥በ፡`ትታገሥ~ገብረ፡እየሱስ`፡በኩል፥
አለሁበት፥እንግሊዝ፡ሐገር፡ድረስ፡የተላከ፡~`ወደ፡ስዊዘርላንድ፡ሐገር፥ለዕረፍት፡ብትመጣ፡ፈቃደኛ፡ነህ፡ወይ*`፡የሚል፤የአክብሮት፡ግብዣ፡ጥሪ፡ደረሰኝ። ጋባዤ፡ወይዘሮም፥የ፡
`ትታገሥ፡የልጅነት፡ጕደኛ፣የልብ፡ወዳጅ፡እና፡የወርቃማው፡ዘመን፤የቀኃሥ፡ቲኣትር፡አባል፡ተዋናይ፡የነበሩ፡አንዲት፡እመቤት፡ልጅ፡ስትሆን፥ጽኑ፡የኪነ~ጥበብ፡ፍቅር፡እና፡አድናቆት፡የአላት፡
~`ሄለኒት~ደርቤ`፡የተሰኘች፡እመቤት፡ነች።

`ትታገሥ፡ገብረ፡እየሱስ`፥ወደ፡ኣሜሪካን፡ምድር፡ከመሰደድዋ፡በፊት፤ቀደም፡ብለው፡ኢትዮጵያ፡ውስጥ፡አብረው፡በአሳለፉት፥ዘመን፥ኪነትን፥በጋራ፡የማድነቅ፡እና፡የመኖር፣
ከ፡ከካያኒዎች፡ጋርም፡በመዋል፡የአዳበሩት፤የግል፡ትውፊት፡ነበራቸው። ከእዚሁም፡አንዱ፡~የእኔውኑ፡የራዲዮ፡ተረክዎች፡በቴፕ፡እየቀዱ፡ማዳመጥ፡እና፡መተቸት፡እንደነበር፥`ትታገሥ`፡
አብስራኝ፡አለች።

በእርግጥም፥`ሄለኒት`ን፡በግል፡አግባብ፡እና፡በግጻዌ፡ተገናኝተን፡ባላውቃትም፥በመደጋገም፡ስልክ፡እየደወለች፡በአደረግነው፡ጭውውት፥ስለ፡ኪነ~ጥበብን፡እና፡በተለይም፡ሥነ~ጽሑፍን፡
አጥብቃ፡እና፡አበክራ፡እንደምትወድ፡ተረዳሁኝ።ለግብዣው፡የአቀረበችልኝ፡የማግባብያ፡ቍንቍዋ፡እራሱ፥ከምን፡መሰል፥የተውኔት፡ትውፊት፡እንደ፡ፈለቀች፡ለመረዳት፥ብዙም፡አስቸጋሪ፡
አልሆነበኝም።

በኣውሮጳው፥የእረዥም፡ዘመን፡ኑሮዬ፥ለእረፍት፡ወደ፡ሌላው፡ሐገር፡መሄድ፥እጅግም፡አስደናቂ፡እና፡አጕጕ፡ባሆንብኝም፡ቅሉ፥በግል፡ውል፡ከሌለኝ፡ሴት፡ለቀረበልኝ፡ማራኪ፡ጥሪ፡ስል፡
ብቻ፥ብድግ፡ብዬ፡መሄዱ፥የቀላል፡ውሳኔ፡አልሆነም።

በነገሩ፡ጥቂት፡አስቤበት፣ይሁንታውን፣ኣንድምታውን፡አብላልቼ፡ሳበቃ፡~`መቼም፥ለምን*፣እንዴት*፡ወደዳችሁኝ፡የማይባልበት፡አግባብ፡በመሆኑ፡~`ከልብ፡ምሥጋና፡ጋር፥
ግብዣውን፡ተቀብየዋለሁ፥ሆኖም፡ግን፥ትቻት፡ልመጣ፡የማልችለው፤ፍቅረኛዬ፥`ኒኒየትዬ`፡አብራኝ፡ስለ፡አለች፥ከአለ፡እርስዋ፡መንቀሳቀስ፡ያዳግተኛል`፡በማለት፥በደማም፡አነጋገር፡
እየተግደረደርኩኝ፥አስታውቅሗት። ወይዘሮ፡`ሄለኒት`ም፤ሳታመነታ፡~`አንተን፡ደስ፡እንደ፡አለህ*~እግዚኣብሔር፡ይመሥገን፡ትድረታችን፡ሰፊ፡ነው~የማረፍያ፡ችግር፡የለም`፡ስትል፤
በቸር፡አንደበት፡አግባባችኝ።

`ትታገሥ`ም፡ይሄንን፡ብስራት፡እንደሰማች፤ከ፡ኣሜሪካ፡ወድያው፡ስልክ፡ደውላ፤በፍሱህ፡መንፈስ፡~`ማር~ጽዮንዬ`፤ምንም፡አታስብ፥እኔ፡ሄጄ፡ባላየውም፡ቅሉ፥ትድረትዋ፡
ሰፊ፡እና፡ብዙ፡ወገኖችንም፡የምታስተናግድበት፡ዠማ፡ሕይወት፡እንደሆነ፡አውቃለሁ፣አታስብ*~እሰየው፡~`ኒኔትም`፡አብራህ፡መሆንዋ፥በጣሙን፡የሚያስደስት፡ነው`፡አለችኝ።

ነገሩ፥በእዚሁ፡ተወስኖ፥ከ፡`ኒኒየት`ም፡ጋር፡በአደረግነው፡ውይይት፡~`እኛንም፥የበጋው፡ወቅት፡ዕረፍት፡ስለሚያሻን፥ጥሩ፡አጋጣሚ፡መሆኑን፡ተስማምተንበት፥በረራው፡
ለሣምንት፡እንዲሆን፡ወስነን፤ሳናመነታ፤ወድያውኑ፡የኣውሮፕላን፡መሳፈርያ፡ቢጣቃችንን፡ገዝተን፤ሁሉም፡በቀና፡ዘልቆ፥በሣምንቱ፥`ስዊስ~ኣየር`፡በረራ፡ላይ፡ዋልን፡ማለት፡ነው።
ከ፡`ኒኒየትዬ`፡ጋር፤ምቹው፥የስዊስ፡ኣውሮፕላን፡ውስጥ፡ሆነን፡እየተጨዋወትን፡ነው፡~`ማር~ጽዮንዬ`፡እስቲ፡ንገረኝ~~ምኑን፡ይአክል፡የተመቻት፡እመቤት፡ብትሆን፡ነው፥
ሁለት፥የማታውቃቸውን፡እንግዶች፡ጋብዛ፡ለማስተናገድ፡የምትደፍረው~ነው፡ወይስ፥በራዲዮ፡ከሰማችው፡ድምጽህ፡ጋር፡ፍቅር፡አስይዘሃት፡ይሆን*`።

`ኒኒየት`፡የ፡ስኮትላንድ፡ተወላጅ፡ነች።የእረዥም፡ግዜ፡ጕደኛዬ፡ሆና፡አብራኝ፡ስትኖር፥ብዙ፥የ፡`ኣበሽኛ`፡ባህላችን፡እና፡አስተሳሰባችን፡ግር፡ይላታል። በተቻለኝ፡ሁሉ፥በትዕግሥት፡
ማስረዳቱ፡ሃላፊነቴ፡ሆኖ፡ኖሯል።

እናም፥ከ፡`ታትገሥ`፡የሰማሁትን፡መረጃ፡ሁሉ፡እየ፡አከልኩበት፡ስለ፡`ሄለኒት`፡አኗኗር፡ረገድ፡ማስረዳት፡ጀመርኩኝ፡ማለት፡ነው፡~`ባለ፡ቤትዋ~`ኧርኒ`፡የተሰኘ፥የስዊስ፡
ዜጋ፡ሲሆን፥በውጭ፡ድርጅት፡ሃላፊነት፥ኢትዮጵያ፡ውስጥ፡ለእረዥም፡ግዜ፡ሲያገለግል፡ከመኖሩም፡በላይ፤ውልደቱ፥ከ፡ዕውቅ፡የ፡`ሥዊስ`፡መሳፍንት፡ቤተሠብ፡የሚቆጠር፡በመሆኑ፤ቅድመ፡
ኣያቱም፥በቀደመው፡ታሪካችን፡ውስጥ፤የ፡`ዐፄ፡ምኒሊክ`፡ባለውለታ፡የነበረ፥`ኢልግ`፡የተሰኘ፡መሀንዲስ፡እንደሆነ፡እና፥ምቹ፡ኑሮ፡እንደሚኖሩም፡እንደተነገረኝ፡አስረዳሗት።
~~~*~~~

( ከ፡~ጃህእርሥዎ፡ሞትባይኖር፡ኪሩብ፡ዔል)

(የ፡ምዕራፍ፡፩፡ማብቅያ።ምዕራፍ፡፪፡ይቀጥላል)

አስተያየትዎን እዚህ ይስጡ

የኢሜል አድራሻዎ አይወጣም

Loading...