Tidarfelagi.com

ማንንም ለመማረክ የማትፈልግበት ደረጃ ስትደርስ

“ዌን ዩ ካም ቱ ኤ ፖይንት ዌር ዩ ሃቭ ኖ ኒድ ቱ ኢምፕረስ ኤኒበዲ”

ከወደ ውስጥህ ያለው ኣንዱ የነፍስያህ የነፃነት በር ሰዎችን ለመማረክ ጥረት ማድረግህን ባቆምክበት አፍታ ወለል ብሎ ይከፈታል…ጎበዝ ተማሪ…ጠንካራ ሰራተኛ…መልከ መልካም…ደግ አዛኝ ሩህሩህ….ከበርቴ ባለሃብት በመባል ከይሲ ፍላጎትህ ላይ ስትሰለጥን ራስህን በራሱ መንገድ ላይ የራሱ በሆነ እርምጃ ሲሄድ ታገኘዋለህ…ያደግክበት ሁኔታና የኖርክበት ባህል ኤምቲቪ ስታይ ኤሚኒየምን ቢቢሲ ስትከፍት ትራምፕን የመሆን ጉጉትን ይጭንብሃል…/ምናልባት ኢቢሲን ስትከፍት ደግሞ <አንዳንድ ‘ያዲሳባ ከተማ ኗሪዎችን>..ሎል/…ወደህ እኮ አይደለም…ዱንያ <የሞላላቸው> አጎንባሽ <የደላቸው> አሸርጋጅ ስትሆን አይተህ ነው…በዚህ የሰራዊት እና የአንዱኣለም የተቀናጡ ማስታወቂያዎች <ሃብታም መሆን ወይም ሞት> ሊያስብሉህ ይችላሉ…በአር ኤንድ ቢ ደሞ ፊፍቲ <ጌት ሪች ኦር ዳይ ትራይንግ> ይረፕርብሃል

ከልጅነት ማዘር እንዲሁ በቅንነት የጡት ወተት እና <ኢጎ> ትመግብሃለች…እንደ አያ እከሌ ልጅ በትምህርትህ ሰቅለህ <ስሟን እንድታስጠራ>…ሃብት አግኝተህ <እንድታኮራት>…እንደ እንትና ልጅ አንተም ወልደህ <አይኗን ባይኗ እንድታሳያት> ትመክርሃለች…በሰፈርህ ደሞ አንድ <ስመ-ጥር> አይጠፋም…መንደሬው ሁሉ እሚያወራለት…ሁሉም መሆን እሚፈልገው አይነት ሰው…መቼስ የደላውን ማን ያማል?…ሁሉም ስሙን እያነሳ ስለ ቅድስናው ይሰበክልሃል…ከፍ ስትል አብሮ አደግህ በሆነ ቀዳዳ አልፎ ዲታ ሆኖ ይጠብቅሃል…ቴሌቪዥን ስትከፍት የቤትና የመኪናው ማስታወቂያ ናላህን ያዞረዋል…ፌስ ቡክ ስትገባ ሁሉም የራሱን ስኬት ሊያሳይህ ሲውተረተር ታገኘዋለህ…እምታየው ሁሉ <ኤክስትራ ኦርዲናሪ>…ያኔ <ዋት’ስ ሮንግ ዊዝ ሚ?>…ትጠይቃለህ

አዳም ጆንሰን(?) መሰለኝ…<ጎበዝ እና ሃብታም ከመሆን ጀርባ በጉብዝናና በሃብት ከሰው ሁሉ በላይ ከፍ ብሎ የመታየት ከይሲ ፍላጎት /<ኢጎ>/ አለ> ይላል…አይዞህ እኔ ለኑረትህ እንደ ዲዮጋን የቀፎ አልጋ እና አንድ ውሻ ብቻ ይበቃሃል አልልህም…በርግጥ ቁስ ዴንታውም ያልሆነበት የፈላስፋው /የባህታዊው ልበል መሰል/ ሰብዕና ይማርካል…ከመፅሃፉም <የሚያስፈልገው አንድ ወይም ጥቂት ነው> የሚለው የክርስቶስ ቃል ይመስጣል

ዳሩ ግን ስኬት እሚጠላ ነገር አይደለም…/ለነገሩ ነው ብልስ ማን ይሰማኛል? 🙂 /…<ዲፕ ዳውን> ከስኬት እና ምኞት ጥማታችን ጀርባ ስላለው የፍላጎታችን <ሩት ኮዝ> ግን ማሰብ ያለብን ይመስለኛል…የመሻታችን ፍፃሜ የምኞታችን መደምደሚያ ምንድን ነው?…ምኞትህ በአደባባይ እንዳይገለጥ ሆኖ ቢፈፀምልህ ምን ያህል ትወደዋለህ?…የቆንጆ ሚስት/ባል፣የሌተስት መኪና፣የግድንግድ ቤት የስልጣንና ዝና ህልምህ በሰዎች ዘንድ ሊሚያሰጠኝ ይችላል ካልከው የከበሬታ እስር ምን ያህል ተላቋል?…አስፈላጊ ጥያቄ ነው

የሃሳቤ መንደርደሪያ አንድ ቦታ ያየሁት የነጮች ጥቅስ ነው…እንዲህ ይነበባል

<<When you come to a point where you have no need to impress anybody your freedom begins>>

ይሉኝታ በሚያጠቃው ማህበረሰብ ውስጥ እንደመኖራችን መግባት መውጣታችን ሳይቀር ለሌሎች በሚሰጠው ትርጉም ልክ ይቀነበባል…ባህላችንን <መንጋነት> ያጠቃዋል…ስታንዳርዳችን <እነ እንትና> ናቸው…ሃሳብ እና ድርጊታችን እገሌን የማስደሰት አሊያም የማብሸቅ አንዱን የመማረክ ሌላውን የማስቀናት እርሾ አይጠፋውም…<ናሽናሊስቲክ ፓትሪዮቱ> ጠጠር ባላቀበልክበት ሲሆን ሲደረግ ባላየኸው የአገርህ ድልና ስኬት እንድትኩራራ ነው እሚነግርህ…በምንም መንገድ ይገለፅ የመኩራራትና የደስታ ምንጭህ ውስጥ <እኔ/እኛ ብቻ> ከገባበት ያላረከው እና የሌለህ በሚበዛበት በዚ ሰፊ አለም ራስህን ለስቃይ እያመቻቸህ ነው

እውነታው ቢሊዮኖች ሴትና ወንድ ደግ እና ክፉ ሃብታምና ድሃ ሆነው ባለፉበት ምድር ራስን ሆኖ በማንም ስታንዳርድ ውስጥ ያልታጠረ የራስን ጠጠር ጥሎ ማለፍ ነው…ነፃነትህ ምንም ጠጠርን እስካለመጣልም ይደርሳል…ከኑረት አላማህ ጋር ማንንም የማስደሰትና የማስደነቅ ሃላፊነት አልተገመደብህም /<ኢንክሉዲንግ ዩር ሰልፍ>/..ልማድ ይተብትበው እንጂ በነፃነት ተፈጥረሃል…በርግጥ ልማድ ቀላል ነገር አይደለም…ማር ይስሃቅ <ከሰይጣን ይልቅ ልማድህን ፍራ> ይላል…ያም ሆኖ ኑረት ጉዞ ነው…ጉዞው <ዘፀኣት> ነው…መውጣት!…ከሌሎች <ኤክስፔክቴሽን> እና <ስታንዳርድ> ባርነት ራስን ነፃ ማውጣት…የተረፈውማ ጠቢቡ እንዳለው ነው…<ከፀሃይ በታች እንደሁ አዲስ ነገር የለም>…በምትኖርበት ዘመን ልኬት ጫፍም ወጣህ ስምጥ ገባህ አዲስ ነገር የለውም…ከጫፍ እስከ ጫፍ ያለውን የስሜት ዥዋዥዌ ከኛ በፊት ቢሊዮኖች ቁጭ ብድግ ብለውበታል

ያም ሆኖ የትላንቶቹ ዛሬ ላይ የሉም…አንተም የሆነ ቀን እዚ የለህም…የመሻገሪያህ ዋዜሜ ላይ ከአጅሬው ሞት ጋር <ዴዝ ቤድ>ህ ላይ መፋጠጥህ አይቀረም…ያኔ ሁሉም ተጨምቆ ሳይደፋ እንደማይቀር ይገባሃል…ጭንቀትና ውጥረትህን ዞር ብለህ ታያለህ…በርግጥ ሁሉም ታሪክህ ነው…ህይወት መውደቅ መነሳት ነው…ያም ሆኖ ሰዎችን ለመማረክ በቆምክበት መሬት በተጓዝከው መንገድ መሳቅህ/መሳቀቅህ አይቀርም…ዞር ስትል ላገኘኸው <ባለ-ህይወት> ትመክራለህ…<ማንም ሞትክን ላይሞትልህ ህይወትን አትገብርለት>

ሸጋ ቀን ወዳጄ!
#ሰላምለሰውልጆችሁሉ!

It’s not about me! it’s not about my life situation either.It’s about life! And in life I trust!

One Comment

  • yonideme@gmail.com'
    Yonas commented on April 17, 2017 Reply

    Kulech yale ewnet neger gin manim(kedeferew) besteker kelemadu melakekin teto tor fit megafet yekelewal….bezihu/bebelete yeketil…min albat bante andebet yetegeletse yene felagot(ego??)..selehone des belognal…melakek gin yechal yehone?…melakekin meshat rasu bariya ayregegnem…min yeshalal?

አስተያየትዎን እዚህ ይስጡ

የኢሜል አድራሻዎ አይወጣም

Loading...