Tidarfelagi.com

ሆሆ

“ወንድ ሆኖ የማያመነዝር ፤ ወታደር ሆኖ እማይሰነዝር ፤ ነጋዴ ሆኖ እማይዘረዝር የለም ! “ይላል ምኡዝ።
እውነቱን ነው፤ከጥቂቶቻችን በቀር ብዙ ወንድ በህይወቱ ቢያንስ አንዴ በትዳሩ ላይ ያድጠዋል። ድርያ በአርቲስት ላይ ይጋነናል እንጂ ፊትና ጭን ከተሰጠው፤ ገበሬ ነጋዴ ፓስተር ሼህ የንስሃ አባት ሳይቀር እንደሚወሰልት እናውቃለን። መቸም የሴት ገላ ማቀፍ እንዴት እንደሚጥም የቀመሰ ያውቀዋል፤ ግን የሚያስከፍለው ዋጋ ከደስታው ጋር አይመጣጠንም፤ አንድ ጣሳ ደስታ ይሰጥህና አንድ በርሚል ጣጣ ያሸክምሃል!!

1
የሆነ ጊዜ ላይ አሜሪካ ውስጥ ባንድ ከተማ የተከሰተውን ዜና በራሴ መንገድ ስተርተው ይሄን ይመስላል፤
ሰውየው ሚስቱ ማታ ለስራ በሄደችበት ውሽማውን አምጥቶ በተቀደሰው አልጋ ላይ ይፈትጋታል፤ በፍትጊያ መሀል ኮቴ ሰምቶ ቀና ሲል ሚስቱን አያት፤ ውሽምየዋ እንደስፓይደር ውመን በመስኮት ዘልላ ነካችው፤ ባልየው ብቻውን ከሚስቱ ጋር ተፋጠጠ፤ ሚስትዮዋ ለሰይፍ ሩብ ጉዳይ የቀረው ቢላዋ ይዛለች፤ ባሉካ ለመሮጥ ተመኜ ፤ግን እግሩ ቀጤማ ሆነበት፤ በወዛደር አማርኛ እንግለፀው ከተባለ እድሩ የቡልዶዘር ጎማ ሆነበት፤ ሚስትየው ምንም አላለችም፤ አልጋው ላይ እመርር ብላ ወጣችና አገር አማን ነው ብሎ ቆሞ የሚጠብቀውን ብልቱን ጨብጣ ከስሩ መተረችው፤ ከዛ እንደ ቀይ ስር በቁንጮው አንጠልጥላው ወጣችና በቤቱ ጉዋሮ በሚገኘው ዱር ውስጥ ወርውራው ተሰወረች፤

ብዙ ሳይቆይ አምቡላንስ ስልቡን ሰውየ ይዞ ወድ ሆስፒታ መረሸ፤ ያሜሪካ ፖሊስ በቦታው ደርሶ ፤ ከሲአኤ ጋር በመተባበር አካባቢውን በብረት ለበስ መኪና አጥሮ ተቆርጦ የተጣለውን ወሸላ ፍለጋ ተሰማራ፤፤ ከላይ በሂሊኮፍተር ከታች በአነፍናፊ ውሻ የታገዘ ሰአታትን የፈጀ አሰሳ በሁዋላ የተቆረጠው ብልት የጉንዳን መንጋ ወርሶት ተገኘ፤፤ በመጨረሻ ዶክተሮች ወደ ስልቡ ባል ቀርበው፤ “የጠፋብህ ብልት ይሄ ነውን?” ብለው’ በመስቀልኛ ጥያቄ መርምረው አረጋግጠው፤ በቀዶ ጥገና ተከሉለት፤ትንሽ ከመንሻፈፉ በቀር በድሮው ቦታ ተተከለ ፤እረ እንዴውም ከዱሮው ሳይሻል አይቀርም፤ ሚስት ተብየዋን ደስ አይበላትና ሀኪሞች ፤ እንደ ክንዱ በፈለገ ጊዜ የሚዘረጋውና የሚያጥፈው አድርገው ተከሉለት፤

2
ይሄ ደሞ ባልንጀራየ የነገረኝ ነው፤

ዲሲ ውስጥ የሚኖሩ ባልና ሚስት ኢትዮጵያውን የተጋቡበትን አስረኛ አመት በማክበር እየተዝናኑ አመሹ፤ከዚያ ሚስትዮዋ” ቤብ፤ በፍቅራችን ላይ ቅመም የሚጨምር ነገር ላሳይህ ” አለችና ከራቫቱን ፈታችለት፤ አያ ‘ቤብ ‘ ክራቫቱን እያስፈታ ፤ ከታች ስራ እንዳይፈታ፤ ቀበቶውን ፈታ፤

ከጥቂት ደቂቃ በሁዋላ አንድ የትራፊክ ፖሊስ መንገድ ዳር ቆሞ ቫይብሬት የሚያደርግ መኪና ስለተመለከተ ጠጋ ብሎ መስኮቱን አንኩዋኩዋ!
“is there any problem ? officer? “ አለ ባልየው ትንፋሹ እየተቆራረጠ።

“መኪና መሳረር ህገወጥ ስለሆነ ልቀጣችሁ ነው” አለና ፖሊሲ ባልየውን መቶ ዶላር ቀጣው፤ ሚስቲቱን ግን ሁለት መቶ ብር ቅጣት ጣለባት፤

ባልየው ትንሽ ቆይቶ ስለከነከነው ፖሊሱን ተከትሎ ደረሰበትና፤

“ቅጣቱስ ይሁን! ይበለኝ፤ የግሬን ነው ያገኘሁት፤ ግን በምን ምክንያት ነው እኔን መቶ ብር ቀጥተህ ሚስቴን ሁለት መቶ ቀጣሃት?’

ፖሊሱ እንዲህ መለሰ፤
“እ ሷ መኪና ውስጥ እንዲህ አይነት ነገር ስታደርግ ያገኘሁዋት ለሁለተኛ ጊዜ ነው፤ ለዝያ ነው እጥፍ ያስከፈልኩዋት”

ባልየው በድንጋጤ ታሞ ይሄው በጎፈንድድሚ እያስታመምነው እንገኛለን፤

Bewketu Seyoum (Ge’ez: በዕውቀቱ ስዩም) is an Ethiopian writer and poet from Mankusa, northwest of Addis Ababa.

2 Comments

  • ዳagami commented on August 17, 2019 Reply

    ባatma ጋrmi
    ላላ ናው

  • yonasbirhanu17@gmail.com'
    yonas birhanu commented on September 20, 2022 Reply

    ፈጣሪዬ አስካገባም፡አግብቼም፡እንዳያድጠኝ እርዳኝ! የዘመኑን ሴቶች በሙሉ አይኔ ውበታቸው ያየሁ እንደሆነ ተከመር ተከመርባቸው ያሰኘኛል፡ ሃሃ

አስተያየትዎን እዚህ ይስጡ

የኢሜል አድራሻዎ አይወጣም

Loading...