እኛ፣ሾፌሩና አውቶብሱ

‹ዛጎል› ልቦለድ ውስጥ የምናገኘው ዮናስ የተባለው ገጸ ባሕርይ እንደሚከተለው ያስባል፤ያምናል፤ይናገራልም! ‘በእኛ ፈቃድ አይደለም ነገሮች የሚከወኑት። እግዜራችን ነው ሾፌር። እሱ ነው ፈላጭ ቆራጭ! እሱ ነው የእኛ ሃይል። በየትኛው ጊዜ – በየትኛው ቦታ – እኛን ከመኪናው ማውረድ እንዳለበት የሚወስን። እኛ ‘ወራጅ አለ’ማንበብ ይቀጥሉ…

ብርሃን ፍለጋ

ወይንሸት የመጀመርያ ልጅ ነች። ዕድሜዋ አስር ሆኗል። እኩዮቿ ከክፍል ወደ ክፍል በተዘዋወሩ ቁጥር እሷ ግን ታናናሾቿን በመሸከም ነው ከዓመት ወደ ዓመት የምትሸጋገረው! ወላጆቿ ሞግዚት የመቅጠር አቅም የላቸውም፤ ለዚህም ነው ወይንሸትን ወደ ፊደል ገበታ ያልሰደዷት። አባቷ ‘ሰርቶ በይ!’ የሚል ድምፅ ወደሰማበትማንበብ ይቀጥሉ…

በውበት ሳሎኑ ውስጥ – 3

ውድ አንባብያን! <ያልተቀበልናቸው>የተሰኘው አዲሱ መጽሐፌን በየመጻሕፍት መደብሩና በየአዙዋሪዎቹ እጅ ታገኙታላችሁ።መጽሐፉ በእጃችሁ እስኪገባ፣አሁንም አንድ ቁንጽል ጻሪክ ከመሐፉ ልጋብዛችሁ።  በውበት ሳሎኑ ውስጥ – 3 ——- የተቀመጥኩት መግቢያው በር አጠገብ ነበር። የሆነ ሰው፣ እጀርባዬ እንደቆመ ትከሻዬ ነግሮኝ ቀና አልኩ። ቀና ስል፣ ከዚህ ቀደምማንበብ ይቀጥሉ…

ባይተዋሩ ግመል

አንዳንድ ድምጻውያን አዲስ አልበም ሊያወጡ ሲሉ ነጠላ ዜማቸውን ቀደም ብለው እንደሚለቁት፣ከአዲሱ ‹ያልተቀበልናቸው› ከተሰኘው መጽሐፌ ከአንዱ ወግ ቀንጭቤ ጀባ ልላችሁ ወደድኩ።  ባይተዋሩ ግመል (….) ግመሉ የተገለለ ነው – ከወንዙ ተነጥሎ፣ ከወገኑ ተለይቶ፣ ለተሻለ ኑሮ፣ ወይም ለተሻለ የመንፈስ ፀጥታ፣ ወይም ለተሻለ ዕውቀትማንበብ ይቀጥሉ…

እንግዶቹ

“… ዓይን ወረተኛ ነው ያመጣል እንግዳ’’ የሚል ስንኝ ያለበት የባላገር ዘፈን አውቃለሁ፤ በርግጥ ዘፈኑ እንደሚነግረን ዓይን ብቻ አይደለም አዲስ ለምዶ እንግዳ ይዞ የሚመጣው፤ ጆሮም፣ ልብም፣ እጅም፣ እግርም መጠናቸው ይለያይ እንደሆነ ነው እንጂ፣ ከአዲስ ነገር ጋር አስተዋውቀውንና አላምደውን እንግዳ ይዘውብን ይመጣሉ።ማንበብ ይቀጥሉ…

ኢትዮጵያ በአማልክት እና በተከታዮቻቸው ዓይን

“… እናቴ ሆይ በዚህች በምባርካት አገር በኢትዮጵያ የሚኖሩ ሰዎችን እስከ ዓለም መጨረሻ ድረስ አሥራት ይሆኑሽ ዘንድ ሰጥቼሻለሁ። እናቴ ሆይ አሁንም ወደዚያች አገር እንሄድ ዘንድ ተነሺ። ደሴቶችና የተቀደሱ፣ ወንዞችዋ ያማሩ፣ ውሃዎችዋ የጠሩ፣ ዛፎችዋና ተራራዎችዋ የተዋቡ ናቸውና አሳይሻለሁ አለኝ።” ይላል አንብር መስቀልየማንበብ ይቀጥሉ…

Loading...