የመጨረሻው የአድዋ ውሎ

እየቆየ ዝነኛ የሆነውና በኢትዮጵያም ታሪክ ውስጥ ምናልባት ከሁሉም የላቀው የአድዋ ጦርነት የተጀመረው በመጋቢት 1 ቀን 1896 ዓ.ም (እ.ኤ.አ) ከማለዳው ላይ ነበር። በዚህ ጦርነት የተሰለፉት ዋና ዋና ጀግኖች ራሱ ንጉሠ ነገሥት ምኒልክ፣ ንግሥት ጣይቱ፣ ፊታውራሪ ገበየሁ፣ ንጉስ ተክለ ሀይማኖት፣ ራስ ወሌ፣ ራስ ሚካኤል፣ልዑል ራስ መኰንን ፣ ራስ መንገሻ ዮሐንስ ፣ራስ አሉላ፣ ራስ ሐጎስ ፣ዋግሹም ጓንጉል፣ ራስ መንገሻ አቲከም እና ሌሎችም ነበሩ።

በጣሊያን በኩል ጦሩን በዋናነት ይመሩ የነበሩት ጄ/ አሪሞንዲ፣ ጄ/ ዳቦርሚዳ ፣ ጄ/አልቤርቶኔ ፣ ጄ/ ኤሌና እና ጄ/ ባራቲየሪ… … ነበሩ።

ውጊያው ከጠዋቱ በ11 ሰዓት ከ32 ደቂቃ ላይ የጄኔራል አልቤርቶኒ ክፍለ ጦር በፊታውራሪ ገበየሁ በዋግሹም ጓንጉል፣ በራስ ሚካኤልና በራስ መንገሻ ጦር ላይ በሰነዘረው ጥቃት ተከፈተ።የንጉሰ ነገስቱ ሠራዊት የመሃል ጦር አዛዥ ፊታራሪ ገበየሁ በዚህ ከጣሊያኖች ጋር በተደረገው ጦርነት የተመሰከረለት ጀግና ነበር።

ጎራዴውን መዝዞ በዋናው የትል አውድማ ላይ ተወርውሮ ገባ። በዚህን ጊዜ በጠመንጃ ጥይት ተመትቶ ህይወቱ አለፈ። የኢትዮጵያውያ ወታደሮች የመሪያቸውን ሬሳ ይዘው ወደኋላ አፈግፍገው የነበረ ቢሆንም ወዲያው ተረጋግተው አልቤርቶን እንደገና ገጠሙ። በ4 ሰዓት አካካቢ አልቤርቶኔ አብዛኛዎቹን መኮንኖቹን አጥቷል። አልቤርቶኔም ራሱ ተማረከ። የኢትዮጵያ ወታደር በሽሽት ላይ ያለውን የጀ/ አልቤርቶኔን ወታደሮች ሲያሳድድ የጄ/አሪሞንዲ ጦር ገጠመው። በዚህ ሰዓት ቀጥታ በንጉሠ ነገሥቱ የሚመራው ጦር ከውጊያው ገባ። በኢትዮጵያ ልምድ መሰረት ምኒልክ እንደ አንድ ተራ ወታደር ለብሶ ከተዋጊዎቹ መሃል ይገኝ ነበር። ወዲያው የኢትዮጵያ ወታደሮች የአሪሞንዲን ጦር ከበቡት። የጄኔራል ኤሌና ተጠባባቂ ጦር ጣልቃ በመግባቱ የጣሊያኖች ድል መሆን ለአጭር ጊዜ ሊዘገይ ችሏል። በዚህ ውጊያ ራስ መንገሻ ከፍ ያለ ሚና ተጫውቷል።

አሪሞንዲ በጥይት ተመቶ ወደቀ እናም በመጨረሻ ሞቷል። ጀ/ ኤሌና እና ጀ/ባራቲየሪ የትግሉን አውድማ ጥለው ሸሹ። በመጨረሻም በኢትዮጵያ ወታደሮች ተማርከዋል። ጄኔራል ዳቦርሚዳም በሽሽት ላይ ሳለ ሞተ። መሪዎቹን ያጣው የጣሊያን ጦር ስልት የሌለው ማፈግፈግ መፈርጠጥ ጀመረ። በመጋቢት 1 ቀን 1896 ምሽት ላይ በኢትዮጵያውያኑ አንፀባራቂ ድል የአድዋ ጦርነት ተጠናቀቀ። የጄኔራል ባራቲየሪ ወራሪ ጦር ድራሹ ጠፋ።

(በዚህ ጦርነት ድሉ የኢትዮጵያውያን ቢሆንም ብዙ ደም ተከፍሎበታል። ፊታውራሪ ገበየሁን ጨምሮ ልዑል ዳምጠው፣ ደጃዝማች መሸሻ፣ ደጃዝማች ጫጫ፣ ቀኛዝማች ታፈሰ፣ ቀኛዝማች ገነሜ እና ሌሎችም የታወቁ አያሌ የኢትዮጵያ ጦር መሪዎች ከጦርነቱ አውድማ ላይ ቀርተዋል። ብዙዎች ቆስለዋል።)

ምንጭ፡- የኢትዮጵያ ታሪክ
ከመጀመሪያው እስከ አሁኑ ዘመን
በአንድርዜይ ባርትኒስኪ
ዮዓና ማንቴል-ኒየችኮ
(ትርጉም፡- ዓለማየሁ አበበ)

ነፃነታቸውን በምስር ወጥ መለወጥ የሚዳዳቸው አንዳንዶች የምታቀሉትና የምታጣጥሉት ድል ይሄ ሁሉ ደም ተከፍሎበታል። ምንጭ– እኔ)

One Comment

  • Anonymous commented on March 8, 2017 Reply

    critical point

አስተያየትዎን እዚህ ይስጡ

የኢሜል አድራሻዎ አይወጣም

Loading...